የጤና ሚኒስተሯ ዶር. መቅደስ ዳባ #ምን ሊያሳኩ ይሆን ሚዲያ ላይ ከች ያሉት። #አልገባኝም።
• "የቤትህ ቅናት በላኝ።" የሚገርመው ከቃለ ምልልሱ ዜናው። «መንግስት የጤና ባለሙያወችን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ #በትኩረት እየሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስተሯ ዶር. መቅደስ ዳባ ከ EBCጋር በነበራቸው ቆይታ ገለጹ።» "መልከ ጥፋን በሥም ይደግፋ" ዓይነት ዜና። የትኛውም የማህበረሰብ ንቅናቄ የፋክት መልስ ነው የሚሻው። የት ላይ ይሆን በትጋት እዬተሠራበት መሆኑ የተገለጸው? ፍዝዝ ያለ ቃለምልልስ ነው ያዳመጥኩት። ፈጽሞ የጤና ባለሙያወች ሰላማዊ ንቅናቄ የዶር መቅደስ ዳባ፤ የእራሳቸው በኽረ ጉዳይ ስለመሆኑ ሚኒስትሯ አልገለፁም። #አላስጠጉትም ። ጠያቄዋም በዚህ ዙሪያ ያለችው የለም። ይህ የጤና ባለሙያወች ከራህብ ጋር፤ ከመኖር ዋስትና ጋር፤ ከዘላቂ ተስፋ ጋር የቀረበን #ብሄራዊ #ሰላማዊ ንቅናቄ በዚህ ውሽልሽል ሁነት የሚገኝ የፖለቲካዊ ትርፍ የለም። የጤና ባለሙያወች ፋክት ገብ ጥያቄ በፍጹም #ፕሮፖጋንዳም አያስፈልገውም የዳቦ ጥያቄ ነውና። ምን አልባት እኔ እምጠረጥረው፤ ንቅናቄው ቆይቶ ሲጠነክር እንደ ተለመደው ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ #መፍትሄ እና መንገድ እኔው ነኝ ብለው ሊወጡ ይችሉ ይሆናል። እሱን ልጠብቅ እንጂ ቀጥታ ኃላፊነት ያለው የሚኒስተር መ/ ቤቱ ግን ጉዳዬ አላለውም። ወይንም እንደ ተለመደው የስሻሊዝም ቅኝት ከፖለቲካ ጉዳዮች ጋር አጋብቶ አዲስ ትረካም እጠረጥራለሁኝ። የሆነ ሆኖ አጭርም ስለሆነ ደግሜ አዳምጫለሁኝ። ምንም #የረባ ፍሬ ነገር የለውም ቃለምልልሱ። 445 ላይክ አለው። የማይገባ ኩነትም ገባኝ የሚል ማህበረሰብ ማግኜቱ ሌላው ግራሞቴ ነው። ጥያቄ ጊዜን፤ ሁኔታን፤ ቦታን አስተውሎ በጊዜ መልስ ካልተሰጠው ሲሞላ ይፈሳል፤ ሲከር ይበጠሳል ይሆናል። ለ...