የጤና ሚኒስተሯ ዶር. መቅደስ ዳባ #ምን ሊያሳኩ ይሆን ሚዲያ ላይ ከች ያሉት። #አልገባኝም።
•
የሚገርመው ከቃለ ምልልሱ ዜናው። «መንግስት የጤና ባለሙያወችን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ #በትኩረት እየሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስተሯ ዶር. መቅደስ ዳባ ከ EBCጋር በነበራቸው ቆይታ ገለጹ።» "መልከ ጥፋን በሥም ይደግፋ" ዓይነት ዜና። የትኛውም የማህበረሰብ ንቅናቄ የፋክት መልስ ነው የሚሻው። የት ላይ ይሆን በትጋት እዬተሠራበት መሆኑ የተገለጸው? ፍዝዝ ያለ ቃለምልልስ ነው ያዳመጥኩት። ፈጽሞ የጤና ባለሙያወች ሰላማዊ ንቅናቄ የዶር መቅደስ ዳባ፤ የእራሳቸው በኽረ ጉዳይ ስለመሆኑ ሚኒስትሯ አልገለፁም።
#አላስጠጉትም። ጠያቄዋም በዚህ ዙሪያ ያለችው የለም። ይህ የጤና ባለሙያወች ከራህብ ጋር፤ ከመኖር ዋስትና ጋር፤ ከዘላቂ ተስፋ ጋር የቀረበን #ብሄራዊ #ሰላማዊ ንቅናቄ በዚህ ውሽልሽል ሁነት የሚገኝ የፖለቲካዊ ትርፍ የለም። የጤና ባለሙያወች ፋክት ገብ ጥያቄ በፍጹም #ፕሮፖጋንዳም አያስፈልገውም የዳቦ ጥያቄ ነውና።
ምን አልባት እኔ እምጠረጥረው፤ ንቅናቄው ቆይቶ ሲጠነክር እንደ ተለመደው ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ #መፍትሄ እና መንገድ እኔው ነኝ ብለው ሊወጡ ይችሉ ይሆናል። እሱን ልጠብቅ እንጂ ቀጥታ ኃላፊነት ያለው የሚኒስተር መ/ ቤቱ ግን ጉዳዬ አላለውም። ወይንም እንደ ተለመደው የስሻሊዝም ቅኝት ከፖለቲካ ጉዳዮች ጋር አጋብቶ አዲስ ትረካም እጠረጥራለሁኝ።
የሆነ ሆኖ አጭርም ስለሆነ ደግሜ አዳምጫለሁኝ። ምንም #የረባ ፍሬ ነገር የለውም ቃለምልልሱ። 445 ላይክ አለው። የማይገባ ኩነትም ገባኝ የሚል ማህበረሰብ ማግኜቱ ሌላው ግራሞቴ ነው። ጥያቄ ጊዜን፤ ሁኔታን፤ ቦታን አስተውሎ በጊዜ መልስ ካልተሰጠው ሲሞላ ይፈሳል፤ ሲከር ይበጠሳል ይሆናል። ለትውልዱ አብነት ያለው ሥልጡን አመራር መስጠትም ይገባል። በዬክስተቱ ማቄን ጨርቄን ማለት አይገባም።
ቃለ ምልልሱ አሁን ካለው ወሳኝ የሃኪሞች ጥያቄ ትኩሳት ጋር የሚገናኝ አልነበረም። አራባ እና ቆቦ የሆነ ጉዳይ ነው።
የህክምና ባለሙያወች ሊቃውንቱ ጥያቄያቸውን ዘርዝረው አቅርበዋል። መልሱም በዛው ልክ አንድ፤ ሁለት እዬተባለ ሊሰጥ ይገባል። እንዲህ #በልሙጡ አላዬሁህም አልሰማሁም ቢባል ነገ ሌላ ነገር ሊያስከትል ይችላል። ንፁህ ጥያቄ ነው። ፍጹም ሰላማዊ ነው። ታጋሽም ነው። ንጹህ መልስ በአክብሮት እና በትህትና ሊሰጥበት ይገባል።
ሌላው ልጅ ተክለሚኬኤል አበበ (ጠበቃ) ዩቱብ ላይ ሳዳምጥ የጤና ባለሙያወች ታካሚወቻቸው ታክመው መዳህኒት መግዣ ሲያጥራቸው በሰውኛ #ርህራሄ እገዛ የማድረግ የፈቃድ ግዴታ ውስጥ እንዳሉም አዳምጫለሁኝ። ታካሚወቻቸው የመዳህኒት መግዣ አጥተው ለባሰ ችግር እንዳይጋለጡም የተከደነ የምግበረ ሰናይ ቅዱስ ተግባር እንደሚከውኑም ካገኛቸው ባለሙያወች እንዳደመጠ ጠበቃ ተክለሚኬኤል አበበ ሲገልጽ አዳምጫለሁኝ። የማይገኝ ልዩ ሰብዕና እኮ ነው የህክምና ባለሙያ መሆን።
የሆነ ሆኖ የሚሊዮን ኢትዮጵውያን ህይወት መዳፋቸው ላይ የሚገኜው #ሰባዕውያን የኢትዮጵያ የሃኪሞች ጥያቄያቸውን በሚመለከት የሰናፍጭ ያህል አትኩሮት በሚኒስተሯ በዶር መቅደስ ዳባ ቃለምልልስ ውስጥ የለም። እጅግ አዝናለሁኝ። ሪፖርት አይሉት ሪፖርት፤ እራስን ማስተዋወቅ አይሉት እራስ ማስተዋወቅ ቅጥመጠኑ የማይታወቅ ቃለ ምልልስ ነው እኔ ያዳመጥኩት። በቅጡም የተሰናዱበት አይመስለኝም። የዚህ ቃለ ምልልስ ፎርማት የጤና ጥበቃ ሚኒስተሯን ገጽ ለማያውቅ ምንአልባት ይረዳ ይሆናል።
የሊቀ ሊቃውንቱ #ከውስጥ መከፋት እንዲህ እንደ አልባሌ የሚታይ ሊሆን አይገባም። የት ይደርሳሉም ማለትም አይገባም። ሊቀ ሊቃውንታት በተግባራቸው ውስጥ ቅንነት፤ ርህርህርና በአደገ መልኩም ቅድስና ስላለ እግዚአብሄር አላህ ይረዳቸዋል ብዬ አስባለሁኝ።
ስለሆነም ከገዢወች #ያስተዋለ መፍትሄ፤ የተደራጄ የመፍትሄ አቅጣጫ ሊተለም ይገባል። አንድ ሃኪም "ባለቤቴን #በሽሮ አረስኳት ሲል፤ ሌላው ሃኪም #ሃኪምነትን #በመምረጤ አፍራለሁ" ሲል ለአንድ መንግሥታዊ አስተዳደር ግምት ላይ የሚጥል ክስተት ነው።
ስለዚህም ለመፍትሄው መጣደፍ ይገባል። ጥያቄውን አቃሎ ማዬት፤ ጥያቄውን ላለመመለስ ሌላ #ትወና ማቀድ አያስፈልግም።
ዜግነት በውኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ትርታው ካለ፤ የወገን #ውስጥ #ሲጎዳ ቀርቦ ጉዳትን አዳምጦ፤ የጉዳቱን ማስተካከያ በሥርዓት መከወን ይገባል። ትልቁ ኃላፊነት ያለበት የአብይዝም መንግሥት ላይ ነው። ለሪዞልት፤ ለኮሪደር ልማት፤ ለሌሎች የግብረ ሰላም ጉዳዮች የሚጣደፋውን ያህል፤ መዋለ ንዋይ የሚያፈሰውን ያህል፤ የመንፈስ አቅርቦትን በገፍ የሚለግሰውን ያህል ለዚህ መሰል ወሳኝ ጉዳይም በቂ ትኩረት እና እንክብካቤ ለጥያቄው ሊሰጥ ይገባል።
ሃኪሞች ሥራ ስለአቆሙ ይህን ያህል ወገን ህይወቱ አደጋ ላይ ሆነ #ግራጫማ ዜና ካልናፈቀው የአብይዝም ሥርዓት ለመፍትሄው ቢያስፈልግ #አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባ ጠርቶ #ሊመክርበት ይገባል። ለህሙማን ለመድረስ የኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ጉባኤ ሊሰበሰብ ይገባል።
ሃኪም ህይወት ነው። የሃኪም ፈገግታው፤ የሥራ ትጋቱ የሚናፍቅ። ራህብ እና ሃኪም ለኢትዮጵያ ታሪክም ጠቃጠቆ ነው።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ማህበረ ቅንነት ደህና እደሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
14/05/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ዕውነት ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልገውም።
ቅን፤ ሩህሩህ የሆነው የህክምና ሙያ ይከበር!
"የምሽት 2 ሰዓት አማርኛ ዜና … ግንቦት 04/2017 ዓ.ምETV | EBC | EBCDOTSTREAM"
68 like
«ሃኪሞች በመንግስት ወጪ የሚታከሙበት ሥርዓት ተዘርግቷል ፦» የጤና ሚኒስትር ዶር መቅድሰ ዳባ ETV | EBC | «EBCDOTSTREAM 445 like #ህም
'ባለቤቴን በሽሮ ነው ያረስኳት'፡ የጤና ባለሙያዎች እና ለምሬት የዳረጋቸው ኑሯቸው»
«የጤና ባለሙያዎች የጠሩት ከፊል የሥራ ማቆም አድማ መጀመሩን ተናገሩ»
"ሐኪም በመሆኔ ያተረፍኩት ድኅነትን ነው" የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች እሮሮ እና ጥያቄ»
«የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት እና ሦስት ዶክተሮች ታሰሩ»
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ