ቃ! ካላለስ?! // ሥነ - ግጥም
ቃ ። „አሁንም ልጆቼ ሆይ ስሙኝ ከአፌ ቃል አትራቁ።“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ© ሥላሴ 03.09.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ። በዝምታ ኳኳታ፤ በኳኳታ ዝምታ // ህምታ - ተተፍታታ? በሁካታ ጸጥታ፤ በጸጥታ ሁካታ // እምታ - ተተፍታታ? ልቤ በዝንቅንቅ በቅልቅል ሲምታታ - ድር ግ ምታ ቃ! እንዳይል በሎሆሳስታ... ሆታ¡ ሲሆን እልልታ በቃና ዜማ ትክታ … በትክታ … መቼ ባጅቼ ከንፌስ ለጫጫታ? ዞገቢስ ነኝ የለብኝም ውለታ! የሙሉ እድሜ ብክነት በከንቱነት አንደገብያ ለእፍታ ሲፈታ ተዬት ተገብይቶ ስክነታዊ ገበታ? ከዬትስ መጥቶ ጌታ ማስተዋል እርጋታ? ብቻ ቻቻ ቸበር ምታ፤ በቃ እስክስታ በስክስታ አንጓ - ተአንጓ የምንቶ ፍሪንባ አቤቱታ …፤ የሥም ወሽመጥ ፍስክታ፤ የህማማት ቋጠሮ ዕድምታ በቃ! ይኸው ሆነ የሞፈር ቀንበር መፍቻ?! ሰሚ ሳያገኝ ቤተ - ዋይታ? በፌስታ ግብይት እንዲህ አንደ ‘ል ባሌ ይፈታ? ብቻ … ብቻ ያ መራር እንትን እንዲህ እንደዋዛ ተረታ?! ለካንስ ለዚህ ነው የድቅድቅ ግዞት ስንጥር ፈግግታ? እንዲህ ሲ ማ ታ፤ ሲያምታታ የህቅታ ቬ ሎ ወ በ ቅታ የቃል ፍልስ - ምልስ ቅልስ - ጠጠርማ - ቃታ ህቅታ፤ የላቦት ዲሞ ግማዱ በቻ ቻ ቴ ሲፈታ … ግብዕት ሆነ ተይህ፤ ግብዕት ሆነ ተያ የእንቆቅልሹ ግርምታ፤ የዋንጫው ሩምታ! ሆ¡ በል አገር --- በትምክህትህ ቃ! በል ሲ ፈ ታ ኪዳን ሲ ያ ፋታ ወይንስ ሊያፍታታ? ገብያ ተውሎ፤ ውሎ ሲፈርስ እንደዋዛ፤ እፍ ብር ሲልም ለአፍታ የጠብታ ቸርቸር ሳይሰናበት፤ የጅረት ምት አያ እንቶኔ ያ ከርታታ፤...