ቅዱሱ ሙሴ አብዩ አሜኑ እንሆ ዛሬም ዲያቢሎስን ድል አድርገ!
የአብዩ አሜኑ ገድለ ድርሳናት እነሆ ታዬ! ቅዱሱ ሙሴ እንሆ ዛሬም ዲያቢሎስን ድል አድርገ! „ ጥብብ ቤቷን ሠራች፤ ሰባቱንም ምሰሶዎች አቆመች።“ (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፩) ከሥርጉተ©ሥላሴ 01.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) · ከዘመ ናት ህማማት ወደ ሰሞነት ትፍስህት። እንቅልፍ አልተኛሁም። እንዲህ ነኝ እኔ በማንኛውም ወሳኝ ጉዳይ ላይ ስጋተኛ እና ፈሪ ነኝ። ስለሆነም ከመተኛት መዝምሩ ዳዊትን ሳነብ ማደሩን መረጥኩት። ያኖረኝ የልብ አምላክ ዳዊት ቅኔ ነው። የሚገርመው ሰውነቴ ንቁ ነው። እንቅልፉ በኗል። እንሆ ይህም ምኞቴ ተፈጸመ „አድርገህልኛል እና ለዘላለም አምሰግንሃለሁ።“ (መዝሙር ምዕራፍ ፶፩ ቁጥር ፱) https://sergute.blogspot.com/2018/07/blog-post_76.html „አዲስ ቅዱስ ጸበል በመንፈስ ሲፈልቅ የተዋህዶ ተጋድሎው ሊገፋው አይገባም“ የሚል ብፁዕን አበው አገር መግባት አለባቸው፤ መሞት ካለባቸውም ሄደው የሰማዕትነት ጽዋውን ይቀበሉ፤ ይህን የምርቃት ታምራት ሊገፉት አይገባም ብዬ ጽፌ ነበር። ታዳሚዎቼንም በዬፌስ ቡካችሁ ለጥፉልኝ ብዬ ተማጽኜ ነበር። ምኞቴ እንሆ ተፈጸመ። በስልክም እስከ ንግቱ 9 ሰዓት ድረስ ስወያይ ነበር ቁጭ ብዬ ያድርኩት። መንፈሴን ከተጋራችን ነፍስ ጋር። መወሰን ያልደፈረ መኖርን አይጀምርና። ቅደስት ተዋህዶ በባዕቷ ትውፊት እና...