ታላቅ የምሥራች ከኤርትራ መንግሥት ተደመጠ!

እንሆ በአንድ ወር ውስጥ ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ የልቤን አደረሱልኝ። አምላኬም ፍላጎቴን አዳመጠ። ተመስገን!
„ወዳጅህን ሂድና ተመለስ ነገ እሰጥሃለሁ አትበለው፣
በጎ ነገር ማደረግ ሲቻልህ።“
(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፳፱)
ከሥርጉተ©ሥላሴ 01.08.2018
(ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።)


  • ·       ሰላምታ።

ጤና ይስጥልኝ ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ እንደምን ሰነበቱ? እነኛ ደስ የሚሉ ፍቅር የሆኑ ቤተሰቦቸዎትስ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። ዛሬ ዘሃበሻ የሚባል ድህረ ገፅ ላይ አንድ መልካም ዜና ሰማሁኝ፤ ቀደም ባለው ጊዜ እኔም አምደኛ ነበርኩኝ። ኤርትራ የሚገኘው ባቶ ዳውድ ኢብሳ ለሚመራው የኦሮሞ ነፃ አውጪ ድርጅት ሁለት አዎንታዊ አማራጭ እንደሰጡት አዳምጫለሁኝ። እጅግ አድርጌ አመሰግነወታለሁኝ። ይህቺ የቡኒነት ወላዊነት የዘመናችን የልባዊነት እኛዊነት ልዩ እዮራዊ ሸልማት ናት።

ቀደም ብዬም ምን ያህል መልእክቴ እንደደረሰ ባላውቅም፤ ይህኛው አዲስ የጀመርኩት ብሎግ ስለሆነ ጥቂት ቅኖች ብቻ ስለሆነ የሚታደሙበት ላያገኙት ይችሉ ይሆናል፤ ከኤርትራ መንግሥት በዚህ ስምምነት ከምፈልገው መንፈሳዊ ጉዳይ ትልቁ እና ዋንኛው ማንኛውንም የኤርትራ መንግሥት ያስታጠቀቻቸው የነፃነት አርበኞች ወደ ኢትዮጵያ እንመለሳለን ሲሉ ትጥቅ እንዲያስፈቱ በታላቅ ትህትና ጠይቄ ነበር። 

አሁን የልቤን አድርሰውልኛል እጅግ አድርጌ አመሰግነወታለሁኝ። ይህ የኢትዮጵያ ሰላም መሆን ለኤርትራም በ እጅጉ ያስፈልጋታል። ስለዚህ ኤርትራ ለራሷ ሰላም እምትሳሳ ከሆነ ማደረግ የነበረባት ቀዳማዊ እርምጃ ይህ ነበር።
  • ·       ማመሳከሪያ።

„የደምሂት መሳቂያ ቀረርቶ በኔት ሲሰላቅ በሚል“ ርዕስ በ14.07.2018 የተጻፈ ነው በዚህ ርዕስ ሥር ንዑስ ርዕስ አሉት፤
አቤቱታዬ እንዲህ ይል ነበር። ይድረስ ለፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ በሚለው ንዑስ እርስ። አሁን ዛሬ ጥዋት ይህን የምሥራች ስሰማ ሐሤት አደረኩኝ።

መቼም ዘንድሮ የሥርጉትሻ መንፈስ የሻማ ዘመን ነው። እያንዳንዳንዷ ቅንጣት ነገር ጠብ ያለች የለችም። ስለምን? ቅንነት ሲመጣ መቀበል አትራፊ ስለሆነ። የ አላዛሯ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ቅንነት ሲጠፋ ጠፋ ሲል 43 ዓመት ታገለ፤ ቅንነት ሲመጣ ደግሞ ማቄን ጨርቄን ሆነ።
  • ·       የወግ ገበታ።

የማከብራችሁ የእኔ ውዶቼ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ የተደረጉ ስምምነቶችን ያልተማቻቸው ወገኖቼ ነበሩ። ከማስታውሳቸው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሽፈራው አንዱ ነው „ኢሳያስ ኢሳያስ ነው“ በሚል ያስነበበን እጅግ ከባድ መልእክትን የመከተ ጹሁፍ እኔም ጽፌ ነበር። 

ወጣቱ ጋዜጠኛ በሰባዕዊ መብት ረገጣ በድፍረት የታታረ ቢሆነም፤ ወጣነቱን ለማሸነፍ ከቅርብ ሰው የበሰለ የፖለቲካ ሊሂቅ በእጅጉ ያስፈልጋዋል። ፖለቲካ ሳይንስ መማሩ በራሱ ሰብዕናን ቀራጭ እና መሬት ላይ ህዝብ በማገልገል ካልተፈተነ ከንቱ መሆኑን ባለፉት ዓመታት አስተውያለሁኝ። በዲግሪ ተመርቀውበት ግን ሳይንሱን ሳይንስ የማድረግ አቅም ያነሳቸው ትጉሃንን ስለተመለከትኩኝ።

የሆነ ሆኖ በማከብረው ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ስሜቱ እና ፍላጎቱን አመዛዝኖ አመጣጥኖ ባለው አቅሙ ልክ አዎንታዊ የማድረግ አቅም አንሶት አያለሁኝ። በእሱ ብቻ አይደለም ላይ ያወጣናቸው ችግሩ የወላቸው ነው። ይህን ወጣት የ አማራ የብዙሃን የመገናኛ ኤጄንሲም ጋር ቃለ ምልሱን ሳዳምጠው ገና ለጋ ወጣት ነው። በፖለቲካ ዕሳቤው ለጋ ነው። ግን ዕድለኛ ነው በዚህ የፖለቲካ አቅሙ ይህን ያህል ንግሥና?

የህዝብ ሰቆቃ ውስጡ ደፍሮ እራስን መማገድ እንጂ አፈጻጻሙን እንዴት እና ለምን? መቼ እና ወደዬት የሚለውን አልጀመረውም። ስለምን ዕድሉ የለውም? ኮርስ የሚሰጠው የለም። በበጀት የሚያጠናከረው የለም። መሪ አካል የለውም። በራሱ ወጪ እና ጊዜ ነው ለሚሊዮኖች ድምጽ የሆነው።

ተነሳሽነቱን፤ ትጋቱን፤ ጀግንነቱን ወደ ዕውቀታዊ፤ ጥበባዊ፤ ስልታዊ ወደ ፖለቲካዊ ፍልስፍናውን ወደ መርሃዊ ዕይታ የሚቀይርለት፤ ሞደሬት እንዲያደርግ የሚገራው የሙያ አባት / እናት ያስፈልጋዋል። 

የፊቱን እንጂ የሁለገብ አቅጣጫ ሳይድ ኢፌክቶችን አያገናዝብም። „መደገፍ ግዴታ የለብኝ፤ መቃወም ግን መብቴ ነው“ የሚል መንፈስ የመብት እና የግዴታን ፍልስፍናዊ ቀመር ዕውቀታዊ በሆነ መሰረት የመጣት ያመጣው ችግር ነው። በሱ የሙያ ተነሳሽነት ላይ ባላቤት ያለው አንድ መዋቅራዊ ድጋፍ ሰጪ ያስፈለገዋል። አሁን ይህም ያላቸው ቢሆኑ ሰብዕና በብቃት መቅረጽ የዬድርጅቶች ዓላማ ስላላነበረ በሁሉም ቦታ የወረርሽኝ ያህል ችግር ነው። መሪውም ተመሪውም ዕድሉን አላገኙም። 

ይህን ጥሶ የወጣው የለማ ኦህዴድ ነው። ለዚህ ነው ለማ የምዕት ዓመት ቅኔ ነው የምለው።

ኢሠፓ ዝም ብሎ ቦታ አይሰጥም። ለአባልነት አንድ ዓመት የዕጩ አባልነት የመፈተኛ ጊዜ አለው። ውጪ አገር ኮቺ የሚሉት ዓይነት የበሰለ ተግባር የሚፈጽሙ የታዱለ ብርቅዬ ሊሂቃን ነበሩበት፤ ሁሉም ማለት ባለችልም። ለምሳሌ ዶር ካሳ ከበደን መውሰድ እንችላለን። 

በህይወት ይኖራል ብዬ አስባለሁኝ የፖለቲካ ሙያ አባቴ ጓድ ገ/ መድህን በርጋ። ኮ/ ጎሹ ወልዴ ብዙ ማንሳት ይቻላል። እኔ አኮ ገብሬ ተቀይሮ ከተመደበው አለቃዬ ጋር መሥራት አልቻልኩም ነበር፤ እሱም በ አጭር ጊዜ ቆይታ በኋዋላ ተቀይሮ ሌላ ሲመጣ አልቻልኩም። 

በቋንቋ ልንግባባ ፈጽሞ አልቻልኩም፤ ድርጅቱ ያው ነው፤ መመሪያው ያው ነው፤ ደንቡ፤ ፕሮግራሙ፤ የውስጥ መሪው፤ ፖሊሲው ያው ነበር፤ ደረጃዬ ያው ነው ግን የአመራር ብቃት እና ጥበቡ ግን የሰማይ እና የምድር ያህል ሩቅ ነበር። የቻሉ ነበሩ እንደ እኔ ዕድሉን አግኝተው ከሥር በገብሬ መንፈስ ተኮትኩተው ያላደጉ መብቀል ከጀመሩ በሆዋላ የተቀላላቁ ስለነበሩ እኔ ግን ያን የእሱን አቅም ምነፈስ ጠጥቼ ነው ያደግኩት። 

እና እሱን የሚመጥን ካልመጣ ወጣ ገብ ነበር የሆነው … እሱ ሃሳብ ሲያፈልቅ ሁሉን ነገር አደረጅቶ ነው በሥሩ ላለነው ለተባባሪ ሃላፊዎች ወይንም የዋና ክ/ ሃላፊዎች ሃላፊነቱን የሚሰጠው ሌሎች ደግሞ ሃሳቡም የላቸውም እንኳንስ ለአመራር በሚያመች መልኩ አደራጀተው ሊያመጡት ቀርቶ … ዝርክርክ ነበሩ … ማለቴ ለዛ ዘርፍ ለክ/ ሀገር የድርጅት ጉዳይ ሃላፊነት መምሪያ ቦታ። ድርጅት ጉዳይ ህሊና ነው ለ አንድ የፖለቲካ ድርጅት።

ለዚህ ነው የምወደው ፓርቲዬን ኢሠፓ ከፈረሰ በኋዋላ ዘው ብዬ የፖለቲካ ድርጀት አባልነቱንም ደጋፊነቱም ዘው የማልልበት። ኢሠፓ የህግ የመንፈሴ ትዳሬ ነበር ሲያገኜኝ በድንግልና ነበር ሲፈርስም በድንግልና ኖርኩለት። ሌላ ድርጀት አባል በመሆን መንጨቧረቅን አስቤውም አላውቅ። ገብሬ የቀረጻትን ሥርጉተን ለመምራት ዲግሪ ብቻ ሳይሆን ጥበብ ስለሚያስፈልግ። የመንፈስ አቅም፤ የማድመጥ አቅም። ቁጭ ብሎ የማሰብ አቅም፤ ድርጅት ቂጥ ይፈልጋል።  የመፍጠር አቅም። የማያያዝ አቅም። የመቅድም አቅም። ሩቅ የማለም አቅም …. ወዘተ … ግን ሴራ ፖለቲካ ለዘር ሳይበቃ ከሰመ።
  • ·       ቅምን ስላማስተዋል።

ለዚህም ነው ከሁሉም ብሄራዊም ሆነ ዞጋዊም ድርጅት አገር ውስጥም ይሁን ውጪ መርጬ ኦህዴድ ብሄራዊ ፓርቲ የመሆን፤  የአገርን አደራ የመረከብ አቅም አለው፤ ኦህዴድ ጭንቅላት ብቻ ሳይሆን አዕምሮ አለው ያልኩት። ስብዕናን ሙሉ አድርጎ የመፍጠር ታሪካዊ ተልኮን በመደበኛ እዬሠራበት ስለሆነ - ማን ኦህዴድ። አሁንም የምለው ኦህዴድን የሚተካ ፓርቲ ኢትዮጵያ ገና አልጀመረችውም መንገዱን። 

እግረ መንግዴን ግን ከዶር ለማ መገርሳም ሆነ ከዶር አብይ አህመድ ጋር ለመሥራት ዕድሉን ያገኛችሁ ወገኖቼ ሁሉ እንኳንም ደስ አላችሁ ልላቸውሁ እሻለሁኝ። ድርጅትህ ሕይወትህ ነው፤ ህይወትህን ልትሰጥለት የመዘጋጀት ጽኑ አቋም የሚኖርህ ብቁ መሪ ሲኖርህ ነው። ቢፈርስ እንኳን ተመክሮህ እና ረቂቁ የህሊና አቅምህ አይፈርስምና። በለብ ለብ ከሆነ ግን መንገድ ላይ ነው የምትቀረው። ለዛውም ሴራ እኮ ነው የኢትዮጵያን ፖለቲካ ሲያስተዳድር፤ ሲመራ፤ ሲገዛ የኖረው። 

መሠረቱ ከሌለህ ሥምህ ከታሪክ አያልፍም። መሳሪያውን ያስጨበጥህ ያስታጠቅህ ሰው ብቃት ይወሰንሃል አንተን ከብረት ቁርጥራጭ አድርጎ የማስቀጠል አቅሙ።

የበቀሉትን አግኝተህ እንኳን ልታሰብል ልታዳምጣቸውም አትፈቅድምና። የበቀሉትን ማጽደቅ አለበህ። የጸደቁትን ማስበል አለበህ፤ የሰበሉትን፤ መብሰል አለብህ። የበሰሉትን ሌላ ችግኝ እንዲያብቅሉ መንገድ መጥርግ የመቻል ብቅታቸውን በጥራትህ መስወለድ አለበህ። …. 

ሂደቱ በማያቋርጥ ሁኔታ መቀጠል አለበት …. አድካሚ ነው አድካሚነቱን መድፈር አለብህ። ያ ሲሆን ዓላማ ያለው፤ ግቡን የሚያውቅ፤ ወጀብ በመጣ ቁጥር ዘንበል ቀና የማይል፤ ተስፋ የማይቆርጥ፤ ጽኑ ትውልድ ትፈጥራለህ። ታዩ እኮ መሪዎች በአንድ ጠ/ ሚሩ በመሩት ውይይት በቃ እጃቸውን ሰጥተው ክብር እና ሙገሳቸውን ሲቀጥሉ …. እራሳቸውንም አላበቁም እንኳንስ ተከታይ ሊያበቁ ቀርቶ … በራሳቸው ውስጥ ያልነበሩ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ነው የነበሩን።

ወደ ቀደመው ነገር ስንመለስ ማስተዋል የጎደላቸው ጹሁፎች ማህበረስብን ገዳዮችም ናቸው። ያ ሰው ወዳጅ የጎንደር ህዝብ መሪውን ላዛውም አብይ ጌጡን „ረግጦ ሄደ“ የሚለው ዕድምታው ትውፊትን ገዳይ ነበር፤ በተጨማሪም ምን ያህል ጎንደርን እያሰገለላት እንዳለ እመለከታለሁኝ። አንዳንድ ጊዜ በሆኑ አጋጣሚዎች ሰዎች ወደ ፖለቲካው አለም ይምጡ እና እውቅና ያገኛሉ፤ „ከአውር ቤት አንድ ዓይና ብርቅ ነው“ ይሉታል ጎንደሮች። 

እነኝህን ታታሪዎች ሁኔታቸው እንጂ መሰረታዊ የሚያድርግ የስልት አቅማቸው ፈቅዶ አይደለም ወደ ነፃነት ትግሉ ጎራ የሚያመጣቸው። የወንዝ ውሃ ሁሉንም ዓይነት ታንኳ እንደሚያመጣው ማለት ነው።
እኛ ብርቅ ስለሚሆንብን ላይ እናወጣቸዋለን። በወጡት ላይ ልክ ግን ያነን የሚመጥን ተመከሮ ለማምጣት እንዲጥሩ አናደርጋቸውም፤ እነሱም አይፈቅዱትም። ስለምን? ከሚፈልጉት ቁንጮ የስም የዝና የክብር ደረጃ ደርሳዋልና። ሲጀምሩት ሥም እና ዝና ሽተው አይደለም። 

ፍጹም በሆነ በወገን ተቆርቋሪነት ነው፤ ግን እኛው ነን ያን ያልተመጣጠነ መንፈስ እንዲያድርባቸው የምናደርገው። ለዚህ ቦታ፤ ለዚህ ሃላፊነት ታጭቻለሁኝ ለካንስ ይሉና በቃ ከዛ መውረድ ይሳናቸዋል።

ሁሉም ሰው ልኬ አይደለም፤ ሁሉም በጎ ነገር አይመጥንም የማለት ነገርን ያሳደጉና ሌላ ሰው ይሆናሉ። ግራጫም ሰብዕና ይኖራቸዋል። ከማህል አልታረስ ከደንብር አልመለስ ይሆናል ጨዋታው። የሚገርመው ይህ በወጣት ወጣንያን ብቻ ሳይሆን በሙሉ ዕድሜ ላይ ያሉትም በዚህ ዘመን ጎልቶ የወጣ አመክንዮ ነው። ይሄ እንግዲህ በኢትዮጵያ የነፃነት ትግል የታዬው ከባዱ ችግር ነው። 

አሁን የመጣውን ለውጥም ደጋፊ አልባ አድርጎ ለማስቀረት የነበረው ጉግስም እኛው እራሳችን ላይ አውጥተን የነገሥነው መንፈስ ሁሉ በውል በአንድ ሃዲድ እና ባቡር ተሳፍሮ ስለነበር ነው። የበቃ፤ የጸደቀ፤ ያሰበለ አቅም ሲመጣ ጭንቅ የሆነውም በዚህ ምክንያት ነው።
  • ·       ነገረ እግዚአብሄር የሁለመና ሃይል ነው፤ አሸናፊም ነው።

የሆነ ሆኖ ትልቁ ነገር የተዘነጋው ይህ የለውጥ መንፈስ ከእግዚአብሄር መሆኑን አለማገናዘብ ነው። አሁንም አልጠፉም የቀደመውን የኤርትራ እና የኢትዮጵያን ቁስል እዬቀረፉ የህዝብን ሳቅ ለመንጠቅ የሚሹ። ነገር ግን ከሰው የሆነው ነገር አይተናዋል። ይሄ  ከእግዚአብሄር የሆነ ነው። 

ለዚህ ነው እኔ ያን ያህል እሞግታት የነበረቸው ኤርትራ ልዑኳን በፍጥነት ወደ ኢትዮጵያ ልዑኳን ልካ ቦሌ ሲረግጡ ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርጌ መንፈስ ቅዱስ የሰጠኝን የሰላም እረፍት የተቀብልኩት። እኔ ረስቸዋል አሁን የ የኢትዮጵያ እና የ ኤርትራን የፖለቲካ የዘመናት ንትርክ፤ ጥፋት እና ድቀት፤ ወደፈት ይመጣል ብዬ የምሰጋውንም። ድንግል ታውቃለች ንጽህናዬን። የሆነው ሁሉ ነገር  እግዚብሄር ስለመሆኑ አሳምሬ ስላማውቅ። ይሄው አሁን ታላቅ የምሥራች ሰማን። ተዛጋጁ ለአዳዲስ የምሥራች ሁሉ ብዬ ጽፌ ነበር።

የኤርትራ መንግሥት የነፃነት ሃይል የሆኑትን ሁሉ እዛው ለመኖር የሚፈቅዱትን እንዲኖሩ፤ አገር እነገባለን የሚሉትን ደግሞ ትጥቃቸውን ፈተው አገራቸውን እንዲገቡ አማራጭ ሰጥቷል። ይህ የመንፈስ ስጦታ ነው። ስለሆነም ትሁታዊ፤ አክብረቶታዊ፤ ታማኛዊ በሆነ መንፈስ የኤርትራ መንግስት ለወሰነው ውሳኔ እና ለወሰደው ቁርጠኛ አቋም ከልብ አመሰግናለሁኝ።
  • ·       ክወና!

ፍቅር ዕዳ ነው። ፍቅር አደራ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ለኤርትራ መንግሥት፤ ህዝብ እና መሬ የሠጣው ታላቅ አደራ ነበር የፍቅር ዕዳ ይሄው መሬት ላይ የሆነውን አዬን።  ይህን የፍቅር ዕዳ የመፈጸም እና የማስፈጸም ሃላፊነቱ ደግሞ በአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ የወደቀ ነው። ኤርትራም አላዛሯ ኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነት ብልህ፤ አስተዋይ፤ ፍቅር የሆነ መሪ ይኖራታል ብላ አላሰበችውም ነበር። ለእግዚአብሄር የሚሳነው የሌለም እና ይህን አደረገልን ለሁላችንም። እንኳንም አልሞትኩኝ! እንኳን ደስ አለን!

ሰላደረገልን መልካም ነገር ሁሉ እግዚአብሄርን እናመስግን!

ቅንነት ያሸንፋል!
ፍቅር ዕዳ ነው!
ፍቅርም አደራ ነው!
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ!


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።