ቅዱሱ ሙሴ አብዩ አሜኑ እንሆ ዛሬም ዲያቢሎስን ድል አድርገ!

የአብዩ አሜኑ ገድለ ድርሳናት እነሆ ታዬ!
ቅዱሱ ሙሴ እንሆ ዛሬም ዲያቢሎስን ድል አድርገ!

  
                „ጥብብ ቤቷን ሠራች፤ ሰባቱንም ምሰሶዎች አቆመች።“
                 (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፩)

ከሥርጉተ©ሥላሴ 01.07.2018
(ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ)
  • ·       ከዘመናት ህማማት ወደ ሰሞነት ትፍስህት።

እንቅልፍ አልተኛሁም። እንዲህ ነኝ እኔ በማንኛውም ወሳኝ ጉዳይ ላይ ስጋተኛ እና ፈሪ ነኝ። ስለሆነም ከመተኛት መዝምሩ ዳዊትን ሳነብ ማደሩን መረጥኩት። ያኖረኝ የልብ አምላክ ዳዊት ቅኔ ነው። የሚገርመው ሰውነቴ ንቁ ነው። እንቅልፉ በኗል።

እንሆ ይህም ምኞቴ ተፈጸመ
„አድርገህልኛል እና ለዘላለም አምሰግንሃለሁ።“
 (መዝሙር ምዕራፍ ፶፩ ቁጥር ፱)

„አዲስ ቅዱስ ጸበል በመንፈስ ሲፈልቅ የተዋህዶ ተጋድሎው ሊገፋው አይገባም“ የሚል ብፁዕን አበው አገር መግባት አለባቸው፤ መሞት ካለባቸውም ሄደው የሰማዕትነት ጽዋውን ይቀበሉ፤ ይህን የምርቃት ታምራት ሊገፉት አይገባም ብዬ ጽፌ ነበር። 

ታዳሚዎቼንም በዬፌስ ቡካችሁ ለጥፉልኝ ብዬ ተማጽኜ ነበር። ምኞቴ እንሆ ተፈጸመ። በስልክም እስከ ንግቱ 9 ሰዓት ድረስ ስወያይ ነበር ቁጭ ብዬ ያድርኩት። መንፈሴን ከተጋራችን ነፍስ ጋር።

መወሰን ያልደፈረ መኖርን አይጀምርና። ቅደስት ተዋህዶ በባዕቷ ትውፊት እና ትሩፋቷን ያከበረው እዬራዊ ታምር ጸሎታ የተደመጠው መጋቢት 18 ቀን 2010 ነበር። ቅብዕው ደግሞ የተክልዬ ዕለት ነበር። 

ፈጣኑ ሐምሌ ኡራኤል፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ ትክልዬ ጥሪውን እንሆ መልክ አስያዙት።ዛሬ ቤቴ ሻማ ብቻ ነው። እርግጥ ቀጠሮ ነበረኝ ዛሬ አገር ልብስ ለመልበስ። ያው የእኛ ነገር ሃዘን ተፍሰሃ ነው ዕጣችን። 

ይህ ለውጥ ከመጣ ጀምሮ በእግዜሩም በሰው ሰራሽም ቅስማችን የሰበሩ ድንገተኞች አሉ፤ ደግሞ ያን የሚጠግኑ ታላቅ አህጉራዊ ተግባርት የተከወነበት የምሥራቻዊ ዜናም አለን። ስለዚህ ዛሬ የአባቶቼን አገር መግባት እልልታ ብቻ ሳይሆን በሰላም ስለመግባታቸው ቁጭ አድርጎ አሳደሮኝ ነበር። እንደገናም ሌላ ኢትዮጵያ ሃብትም ያጠናበት መርዶም ያው ሰማሁኝ።

የህይወት ቀን

ዛሬ ለዓለም ሰላም ወዳዶች በሙሉ ታላቅ የህይወት ቀን ነው። ታላቅ የሰላም ቀን ነው። ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሁለመና መሠረት ናት። ተዋህዶ ሁሉም አላት። ዕድማታውም ተደሞውም፤ ቅኔውም ሁሉም ገሃዱን ዓለም እና መንፈሳዊውን ዓለም የሚያገናኝ የጥበብ  ዕውቀት በገፍ የረበባት ናት።

ከሁሉ አስቀድሜ የሲያትል እና የኮሎንበስ ኦህዩ የቅድስት ተዋህዶን ልጆች፤ ሰበካ ጉባኤዎችን ዝቅ ብዬ ላመሰገን ይገባኛል። በዛ የመከራ ዘመን አሜሪካ፤ ካናዳ፤ አውሮፓ፤ አፍሪካ፤ አውስትራልያ፤ ኖይዝላንድ የሚገኙ የተዋህዶ አጥቢያ አድባራት ሆኑ ማህበረ ምዕመናን፤ የቤ እግዚአበህር ሊቀ ትጉሃን አገልጋዮች፤ ሊቀ ሊቃውናት ሁሉንም ሁነውላታል ለቅደስት ቤተክርስትያናችን። ሁሉንም ሰጥተዋታል። ደክመውላታል። 

ብፁዓን አባቶችን እንደ ባህሪአቸው፤ እንደ ጸጋቸው እንደ ደረጃቸው እቅፍ ድግፍ አድርገው እንደ ታቦት ከብክበው ለዚህ አብቅተዋቸዋል። ድካማቸውም እንሆ አፈረላቸው። ተመስገን።  

አምካለችን ልዑል እግዚአብሄር ደግሞ ከሰውም፤ ከተራራም፤ ከቦታም ምርጫ አለው እና የሲቲያል እና የኮሎንቦስ ኦሃዩ መዳህኒዓለም ምዕመን አጥቢያ አድባራት ግን ልቅናቸው በአንድም በሌላም እሰማ ስለነበር ጉልላታችን ናቸው። ጸሐዮዎቻችን ናቸው። ጽዮኖቻችን ናቸው። ለዚህም ነው ታላላቅ ጉባኤዎች ኮሎንቦስ ኦሃዩ ሲካሄዱ የኖሩት።

በፍጹም ሁኔታ ታዛዦዞችም ነበሩ። እነዚህ መንትዮሽ ቦታዎች ለቅድስት ተዋህዶ የመከራ ዘመን ለጽናት አውታርነት የተመረጡት በጥበቡ በአንድዬ በአማኑኤል ነበር። ለእኛ ለቅድስት ተዋህዶ ልጆች ብቻ ሳይሆን ለነፃነት አርበኞች ሁሉ ዛሬ ታላቅ የምሥርች ቀን ነው። የክርስትና እምነት ተከታዮች ሆኑ የእስልማና ተከታዮች ትጋታቸው ሰላም እንዲሰፍን ነበር ትጋታቸው። በቤታችን፤ በማዕዳችን በአውዳችን የሰላም ዜማ እንዲወረብ ነበር። ይህ ሲሆን የሚከፋው ዲያቢሎስ ብቻ ነው። 

እርግጥ ነው እኔ ከዚህ ሆኜ እንኳን ሳስበው መለዬቱ ቢከብድም፤ በመንፈስ አብሬ ስለነበርኩኝ ዕንባዬን ልቆጣጠረው ባልችልም ፈቃዱ በማይመረመር ታምራቱ የተከወነ ስለነበረ ደስታዬ ወደር የለውም።
 እውነት ለመናገር ብፅዕናት ለመስከርም 8 ጉዟቸውን ሲቀጥሩት፤ የውሳኔአቸውም ጭብጥ ስመረመረው እኔ እንደ ተዋህዶ ልጅነቴ ውስጤ ማዲያት በማዲያት ነው የሆነው።

በዛች ቅጽበት እኔ መንፈስን፤ ገጽን ስለምከታታል የልጃቸውን፤ የታዛዣቸውን የዶር አብይ አህመድን መንፈስ ጥቁር ሲል ነፍሴን አላውቀውም ብዕሬን ሳነሳ።

እንደገናም በእንቅልፍ ሰዓት ብስጭቴን ደውዬ መልዕክት ተውኩኝ። እንደዚህ ቤተሰቦቼን በፍጹም ረብሻቸው አላውቅም። በቤተ እንግዚአብሄር መንፈስ ውስጥ ስሆን እኔ ሌላ ሰው ነኝ። አመራር ስስጥ ደግሞ ሌላ ነኝ። ያን ቀን ግን ጉልበት ነበረው ድምፄ። ብስጭት ነበረው ልሳኔ።

እግዚአብሄር እንዴት ይገፋል ነበር ያልኩት።
ሁሉም ነገር ከ እግዚአብሄር ስለመሆኑ ቁልጭ ብሎ ይታዬኛል። የሰው ሥራ አይደለም። በፍጹም። በ አንድ ወቅትም በዚህ በጠ/ ሚር ሹም ሽር ላይ እንኩሮ ሲበዛ „ለማ አብይ“ በሚል „እግዚአብሄር እንዴት ተራሳ“ ብዬ ጽፌ ነበር።

እግዚአብሄር መሬት ላይ ወርዶ እዬሠራው ያለው ረቂቅ የማይመረመር ስጦታ ነው። በአባቶቼ እምነት ነበረኝ። ዕምነቴም አፍርቷል። መቼም ዘንድሮ ይሳካልሽ፤ ይሁንልሽ ተብያለሁኝ እና … መንፈሴ የፈቀደው ሁሉ ሰምሮልኛል። ሆኖልኛል።

ይህቺ ይቅብዕ ዕለት ለብፁዕን አባቶቼ እንድታልፋቸው አልፈቀድኩኝም ነበር። ለቅደስት ተዋህዶም ይህ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ነው። ታሪኩ፤ ገድሉ፤ ታምራቱ ድርሳን ነው። ድንጋጌ ነው። ልናከብረው፤ ልንከባከበው ይገባል እንጂ ልንገፋው፤ ልናጎደፈው አይገባም።

በተጨማሪም ሌላው በገሃዱ ነገር የሆነው ነገር ሁሉ ትርፍ ነበር። ሰፊ የሆነ ሰው ሊያምነው የማይችል የግንኙት መሰረት ተጥሏል አሜሪካ ላይ። አሜሪካ ላይ ፍርሶ የነበረው አብሮነት መሠረቱ ተጥላል። ማስቀጠሉ ደግሞ የቅኖች ተግባር ነው። ይህ ግን ለገሃዱ አለም መሸጋጋሪያ ነው። ይህ ጥሪ ግን መንፈሳዊ ነበር። የ እስልምና እምነት የሰላም ፋውንዴሽን እና የተዋህዶ ጉዳይ ግን ዕቅዱ ከመዳህኒዓለም ነበር።

ለ ስደተኛው ቅድስት ተዋህዶ አውሮፕላን ከደጃፏ ሄዱ በፍቅር እቅፍ ያደረጋት ልዩ ዘመኗ ነው። ስለነበረው፤ ስለጣፍ ማናቸውም ነገር ሁሉ ቅደስት ተዋህዶ ብትመለስበት ቁጣው የሰማይ ነው። ከዚህች ቅጽበት ጀምሮ ልክ እንደ ኤርትራ እና እንደ ኢትዮጵያ ግንኙተነት አልነበረም፤ አልተፈጸም ብለን እርግፍ አድርገን መርሳት አለበን። ከዚህ በላይ መዳህኒዓለም ሊያደርግልን የሚችል ምንም ክብር የለምና። ቅኖች እንዲህ እሱ ባፈረው ሰብል ተጠቃሚዎች ናቸው።

ይገርማል በአንድ አፍሪካዊ መሪ በአንድ የአፍሪካ ተስፋ፤ በአንድ የራዕይ ሙሴ በአንድ የቅንነት የአሮን በትር እንዲህ ሲሳካ ከእኔ በላይ ደስተኛ ሊሆን የሚችል አንዳችም ሰው ሊኖር አይችልም። ለካንስ ሥርጉተን እንዲህ እዬሱስ ክርስቶስ ይወዳታል? ለካንስ ቅንነቷን ያከብርላታል? ተመስገን! ተመስገን። ተመስገን! ተመስገን!

ጠ/ ሚር አሜኑ ይኑሩልኝ! እንኳን ደስ አለዎት። ክፍት ብለው ባዶ እጀዎትን እንዳይመለሱ ተንበርክኬ ጸለይኩኝ። በሰውኛው ሊደረግ የሚጋውን ሁሉ ተጋሁኝ። አሁን ቅንነቴ በራለት። ተመስገን። እንኳን ደስ አለዎት። በጣም የገረመኝ የጥዋቱ ጉባኤ ላይ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እንዳይራው ያደረጉት ጥበበዎት ነው። ክበሩነተዎት ጥበብን አብዝተው ፈለጓት ተሰጠዎትም። አይዞዎት!

ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ወደ አሜሪካ የሄዱት፤ የተላኩት ከመንፈስ ቅዱስ ነበር። መንፈስ ቅዱስም ጥሪውን ላከበረ ምላሹን ሰጥቷል። ገድለ አብይ ይቀጥልላ። ዶር ለማ መገርሳም እንኳን ደስ አለዎት። የሚገርመው በሁለቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ማህል ውስጥ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አሟጋቹ ዲያቆን ነበር። እሱ እና አባቶች አንድ አውሮፕላን ውስጥ እንሆ ታደሙ! በራሱ ጊዜ እግዚአብሄር ቅንነትን አነገሠ። እዮባዊነትን ዕጬጌ አደረገ ተመስገን!

እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል!
የእኔ ሎሬት ብላቴው የቅኔው ልዑል፤ የአፍሪካ ቀንዲል ጸጋዬ ጋብረመድህን በመንፈስም እንኳን ደስ አለህ አባቴ ታቦቴ! ልጆችህ የታማራት የገድላት ሚስጢራት ሆኑልህ፤ ምን አለ እንዲያው ምን አለ ቀና ብለህ ብታይልን እንዲህ አባቶቹን ጉንብስ ብሎ እዘዙኝ የሚል ልጅ ተፈጠረልህ በአላዛሯ ኢትዮጵያ …

ቅድስት ኦርቶዶክስ ሃይማኖቴን አቤቱ ጌታ ሆይ ጠብቅልኝ!
ብፁዕን አባቶቼንም ንጉሤ ሆይ እንኳን ለባዕታቸው አበቃህልን!
የተመስገን ዕለት በተመሰገን ታቦት ትፍስህት በትርሲት እንሆ ሆነ!
የኔዎቹ ኑሩልን!

መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።