ልጥፎች

ከኤፕሪል 25, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ዓላማ እንኳን ተፈጠርክልኝ ብሎ ዬሚመርቀው አቶ ኤርምያስ ለገሰ። • ለዓላማው ፍፁም ታማኝ።

ምስል
  ዓላማ እንኳን ተፈጠርክልኝ ብሎ ዬሚመርቀው አቶ ኤርምያስ ለገሰ። • ለዓላማው ፍፁም ታማኝ።   ለእኔ አቶ ኤርምያስ ለገሰ ግድፈታቸው ሳይዝረከረክ ጠቅላይ ሚር አብይ እንዲመሩ የተጋበት ዓላማው ነው ብዬ አምናለሁኝ። መብቱም ነው። አያደናግር ነበር በቀደመው ጊዜ ስሞግተው የነበረው። ኦህዴድ መራሿ ኢትዮጵያም ናፍቆቱ ናት ብዬ አምናለሁ። ይህም ሙሉ መብቱ ነው። አማራ ለሞቱ ግን ተኝተህ በለኝን ከዝኖ የያዘበት ስልቱ ያመኝ ነበር። ሰሚም ዬለም። ስንት ሰው ፈዞ፦ ደንዝዞ፣ ስንት አቅም ብን ብሎ ተፍረክርኮ ቀረ? "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።" #ጠብታ ። አሁን ወጀቡ ረብ ብሏል። የጎሸውም ጠርቷል። ስለዚህ ሃሳቤን በሰከነ ሁኔታ ማቅረብ ፈለግሁኝ። አቶ ኤርምያስ ለገሰን ኢሳት መስራት ከጀመረበት ወቅት ጀምሮ አዬር ላይ አውቀዋለሁ። በደጉ ሳተናውም በሁለት ፁሁፎቼ ሞግቸዋለሁኝ። በተጨማሪም በባልደራስ እስር እና ያራምደው በነበረቀቀው ዬንደት ስልቱም በተከታታይ ፌስቡኬ ላይ ሞግቸዋለሁኝ። ሂደቱ በጥዋቱ ነበር የገባኝ እና። ከዛ በተረፈ ከህወሃት ሥልጣን ስለምን ዓላማ እንደለቀቀ፤ ሰብዕናውን ለአምስት ተከታታይ ዓመት ልክ እንደ አቶ ጃዋር መሐመድ አጥንቸዋለሁኝ። ምክንያቴ ሁሉም በዬቀለሙ ምን አስተዋፆ ሊኖረው ይችላል በሚል አርቄ ሳይሆን አቅርቤ የእኔ ብዬ አጥንቸዋለሁኝ። የፖለቲካ ድርጅት ተከፋይ ቋሚ ሠራተኛ መሆን እና ተምሮም ፖለቲካ ሳይንስን ዕድሉ ከሌለ የሰፋ ልዩነት አለው። በዚህም የዳበረ የፋንክሸነሪ ተመክሮ አለው። ከህወሃት ጋር መሥራቱ ከልጅነት እስከ ዕውቀት ከጫካ እስከ እስር ቤት ከእስር ቤት እስከ ስደት በነበረኝ ፀረ ህወሃት እና ባልተለወጠው አቋሜ ላይ ሆኜ አቶ ኤርምያስን ከህወሃት ጋር ሰራ የሚለው ወቀሳ ያመኛል፤ ለዚህ ተልዕኮም እስከ መጨረሻው ተባባ...