#የአዳኝ ባተሌ አባት ነፍስ እንደ ዋዛ መንገድ ላይ መቅረት። #መራራ ስንብት። እንደ አልባሌ #ዕውቀት ለባሩድ??? #ልቅና ለበቀል???
#የአዳኝ ባተሌ አባት ነፍስ እንደ ዋዛ መንገድ ላይ መቅረት። #መራራ ስንብት። እንደ አልባሌ #ዕውቀት ለባሩድ??? #ልቅና ለበቀል??? "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ሃኪም ለእኔ #ነብይም #መላእክም ነው። ለምን ሃኪም #በጭካኔ ይገደላል? ሃኪም ሩህሩህ ሰባእዊ እና አዛኝ ፍጥረት ነው። ለምን #አረማዊ ነገር ይፈፀምበታል? ህይወታችን የቀጠለችው እኮ በእነሱ ድካም ነው። ከፈጣሪ በታች እረዳታችን የመኖራችን ጌታወች እኮ እነሱ ኒቸው። በእጅግ አሳዛኝ ዜና ነው። የጉበት፤ የቆሽት እና የሃሞት ከረጢት እስፔሻሊስቱ ዶር አንዱአለም ዳኜ ከአንዱ ሆስፒታል ወደ ሌላ ሆስፒታል ነፍስን የመታደግ ቅዱስ ተግባር እዬባተሉ በነበሩበት ከመኪናቸው አስወርደው እንደተገደሉ ነው ዜናወች የሚያመለክቱት። እስከ መቼ ነው #የአማራ እናት፤ የአማራ #እህት ፤ የአማራ #ሚስት ፤ የአማራ #አክስት ፦ የአማራ #ምራት ፤ የአማራ ልጆች ተስፋ የባሩድ #ቀለብ ሆነው የሚቀጥሉት? የጭካኔ ፉክክር ለየትኛው ማህበረሰብ እድገት ይሆን የሚጠቅመው? የአማራ ልጅ ቀጣይ ህይወት #የዝብሪት ቤት ነው የሆነው? እባካችሁ #አደብ ግዙ እና #ቁጭ ብላችሁ ምክሩ። ከመገዳደል የሚያተርፈው ሰይጣን ብቻ ነው። #አዳኝ እንዴት ይገደላል? በዬትኛውም አለም ሃኪሞች ቀስ ብለው ሲራመዱ እንኳን አታዮዋቸውም። ሁልጊዜ ጥድፊያ ነው። ሰውን የማትረፍ፤ ለሰው ችግር ፈጥኖ የመድረስ ጥድፊያ። ለመሆኑ ከዚህ ሙያ ለመድረስ ስንት መዋለ መንፈስ አገርስ፤ ማህበረሰብስ? ቤተሰብስ አፈሰዋል? መምህርም እኮ ናቸው። የብዙኃን #አባ ። መዳህኒትም ፈዋሽ ናቸው። ያቺን የጭንቅ ሰዓት እኮ ሁላችንም እናውቃታለን። ሃኪም ባይኖር በህይወት ማን ...