#የአዳኝ ባተሌ አባት ነፍስ እንደ ዋዛ መንገድ ላይ መቅረት። #መራራ ስንብት። እንደ አልባሌ #ዕውቀት ለባሩድ??? #ልቅና ለበቀል???
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"

ሃኪም ለእኔ #ነብይም #መላእክም ነው። ለምን ሃኪም #በጭካኔ ይገደላል? ሃኪም ሩህሩህ ሰባእዊ እና አዛኝ ፍጥረት ነው። ለምን #አረማዊ ነገር ይፈፀምበታል? ህይወታችን የቀጠለችው እኮ በእነሱ ድካም ነው። ከፈጣሪ በታች እረዳታችን የመኖራችን ጌታወች እኮ እነሱ ኒቸው። በእጅግ አሳዛኝ ዜና ነው። የጉበት፤ የቆሽት እና የሃሞት ከረጢት እስፔሻሊስቱ ዶር አንዱአለም ዳኜ ከአንዱ ሆስፒታል ወደ ሌላ ሆስፒታል ነፍስን የመታደግ ቅዱስ ተግባር እዬባተሉ በነበሩበት ከመኪናቸው አስወርደው እንደተገደሉ ነው ዜናወች የሚያመለክቱት።
#አዳኝ እንዴት ይገደላል? በዬትኛውም አለም ሃኪሞች ቀስ ብለው ሲራመዱ እንኳን አታዮዋቸውም። ሁልጊዜ ጥድፊያ ነው። ሰውን የማትረፍ፤ ለሰው ችግር ፈጥኖ የመድረስ ጥድፊያ።
ለመሆኑ ከዚህ ሙያ ለመድረስ ስንት መዋለ መንፈስ አገርስ፤ ማህበረሰብስ? ቤተሰብስ አፈሰዋል? መምህርም እኮ ናቸው። የብዙኃን #አባ። መዳህኒትም ፈዋሽ ናቸው። ያቺን የጭንቅ ሰዓት እኮ ሁላችንም እናውቃታለን። ሃኪም ባይኖር በህይወት ማን ይቀጥል ነበር። አንድ ጣሊያናዊ ሃኪም በኮረና ዘመን "ነገ ትረሱናለችሁ ብለው ነበር። " ዩቱብ ቻናሌ ላይ በድምጽ ሠርቸዋለሁኝ። መሬት ላይ ተነባብረው እያደሩ ነበር ያን የሲኦል በሽታ ኮረናን ጥቃት የታደጉን።
ፖለቲካ ለሰውካልሆነ ለማን እና ለምን ሊሆን ነው? ሰው መሆን #የተሳነው ስለምን የፖለቲካ ቤተሰብ ይሆናል???? ህሊና የላችሁም? ይህን ስል ያልተማረ ሙያ የሌለው ይገደል እያልኩ አይደለም። ሰው የተፈጠረው ለሰው ነው። ሰው የተፈጠረበት አመክንዮ ለምስጋና ነው። የመፈጠራችን ሚስጢር ነው እዬተቀጠቀጠ የሚገኜው። እራስን የሚገል፤ ሚስጢርን የሚገል አረማዊነት እንደምን ክቡር ሊሆን ይችላል። እራሳችን እያረከስን፤ እያከሰርንም ነው እምንገኜው።
ከጭካኔ፤ ከበቀል፤ ከምቀኝነት፤ ከጥላቻ መቼ ነው እምንፋታው? መቼ???? ግን ሰው ነን? ከሰው ተፈጥረናልን? መፈጠራችን እንዲህ ለጭካኔ ሲገዛ ምን ይሰማናል? እራሳችን በራሳችን ህሊና መድረክ እንጠያዬቅ።
አንጀትን በድርቡ ብጥስጥስ የሚያደሬግ መከራ ነው። ሃዘኑ የሁሉም ሊሆን ይገባል። ጭካኔ ይቁም! ይህን ስላልን አይቆምም። ነገር ግን የህሊና ሰውነት ብቃት ይጠይቃል። መሰልጠን ማለት ለእኔ ሰው ሆኖ መፈጠር ማለት ነው። እኛ ግን ከሥልጣኔውም ሰው ሆኖ ከመፈጠሩም ሚስጢር ተላልፈን አጓጉል፤ የጓጎለ ጉዞ ላይ እንገኛለን። እግዚአብሄር ይማረን። አሜን።
ሰማዕትነትን በሙያቸው ላይ እያሉ ለተቀበሉት ዶር አንዱአለም ቤተሰቦች መጽናናትን እመኛለሁኝ።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን። ከሌላ ቤተሰብ ያገኜሁት ነው።
"Life is not to be trusted; it will betray you without a moment's hesitation. Those with cruel hearts will never see the road you've traveled, the purpose that drives you, nor the deep love you hold for your people. They are simply malicious, they will take everything. Dr. Andualem was not just a person; he was a beacon of hope, a beloved, disciplined surgeon, specializing in Hepatobilliary and Pancreatic surgery; a brilliant Gold medalist from Jimma, a star at Bahir Dar University during his Residency in General surgery, and a Best Fellow award recipient from his HBP fellowship in Addis Ababa. His path took him from Jimma University to Bahir Dar to Addis Ababa, then to Bahir Dar again to serve his community. But even a light so bright could not escape the darkness of that cursed day when fate, with a cursed hand and a bullet's cold blade, extinguished his life. This incredible person, who we valued so greatly, was gone in a single second. The mind that eased so many anxieties went silent, and the hands that had held so much promise grew still. An unthinking act of evil cut short a life dedicated to saving others; a day of utter cruelty."
"We had a dream, Andualem, a dream woven from your spirit."
RIP ወንድማለም





ይህ ከአቶ ስመኜው ጌታሁን ያገኜሁት መረጃ ነው።
"ምን ተብሎ እንደሚፃፍ አላዉቅም 

"ዶ/ር አንዷለም ዳኜ ትናንት ምሽት ከሆስፒታል ስራ ቆይቶ ወደ ቤቱ ሲመለስ በጥይት ተደብድቦ ህይወቱ ማለፉን ሰማን

ሀኪም ነበር ቢባል ሀኪም ብቻ እንዳይመስላችሁ ፤ እጅግ የተለየ እና የተጨበጨበለት ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪም ነው። የመጀመሪያ ዲግሪዉን ፣ ስፔሻላይዝድ ሲያደርግ እንዲሁም ሰብ ስፔሻላይዝ ሲያደርግ ሶስት ጊዜ የወርቅ ዋንጫ የወሰዶ እንቁ ሀኪም ነበር። በቀዶ ህክምና ክህሎቱ በትህትናዉ በፀባዬ የተለዬ ሰው ነበር። ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ጥበበ ግዮን ሆስፒታል አራት አመት አብሮ የመስራት እድል ነበረኝ። የማይተካ ሰው አጣን 





ነብስህ በገነት ትረፍ!!"" አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02/02/2025
በቃችሁ ይበለን ፈጣሪያችን። አሜን።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ