በምእራብ ሽዋ አንዲት የ7 ዓመት ቀንበጥ #ተደፍራ በጭካኔ #መገደሏን ዜና አዳምጫለሁኝ።


ሌላም አሳዛኝ ዜና በኦሮምያም አለ። በምእራብ ሽዋ አንዲት የ7 ዓመት ቀንበጥ #ተደፍራ በጭካኔ #መገደሏን ዜና አዳምጫለሁኝ። ህፃን ሱንባ ብርሃኑ ይመስለኛል ስሟ። ትምህርት ቤት እንደ ሄደች ነው እንደወጣች የቀረችው።
ይህ አረመኔያዊነት መቼ እንደሚቆም ይናፍቀኛል። #የጭካኔ #ፋክክር። የጠቅላይ ሚር አብይ የብልጽግናቸው ወፈ ሰማይ 15ሚሊዮን አባላት ከፊሉ አካል ነው የማንን ጎፈሬ ሲያበጥር ውሎ እንደሚያድር እግዚአብሄር ይወቀው። የዜጋው ህሊና ይህን ያህል ሸፍቶ ጭካኔ ሲነግስ የተሰባሰበው የአባላቱ ተግባር {} ምንም መሆንን የሚያመለክት ነው።
የሆነ ሆኖ #ወላጆች ሆይ! እባካችሁን ልጆቻችሁን ጠብቁ። ዘመኑ ልብ አስጥሎ የሚያስቀምጥ አይደለም። ለህፃኗ እንደ ህፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ሰማዕትነት ነው። ለቤተሰብ ግን የዕድሜ ልክ ሃዘን ነው። መጽናናትን እመኛለሁኝ። አይዟችሁ። ፎቶዋን ስላላገኜሁት ነው ያልተለጠፈው። አሁን ያገኜሁት ይመስለኛል።
ሥርጉትሻ2025/02/02
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ