"በዩክሬን እና ሩሲያ የሰላም ድርድር ቁልፍ ሚና እየተጫወቱ የሚገኙት እነማን ናቸው?» BBC. (#ጦርነት እንጂ #የሰላም #ንግግር፤ #የሰላም #ውይይት #ፈጽሞ ሊፈራ አይገባም። Sergute Selassie)
#ጦርነት እንጂ #የሰላም #ንግግር ፤ #የሰላም #ውይይት #ፈጽሞ ሊፈራ አይገባም። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። "በዩክሬን እና ሩሲያ የሰላም ድርድር ቁልፍ ሚና እየተጫወቱ የሚገኙት እነማን ናቸው?» BBC. https://www.bbc.com/amharic/articles/c4g5r4pmjd8o "አሜሪካ፡ ዳን ድሪስኮል። አሜሪካ፡ ስቲቭ ዊትኮፍ። አሜሪካ፡ ማርኮ ሩቢዮ። አሜሪካ፡ ያሬድ ኩሽነር። ዩክሬን፡ አንድሪ ዬርማርክ (አሁን ከሥልጣን ለቅቀዋል)። ዩክሬን፡ ሩስቴም ኡሜሮቭ። ዩክሬን፡ ሩስቴም ኡሜሮቭ። ሩሲያ፡ ዩሪ ኡሻኮቭ። ሩሲያ፡ ቭላድሚር ሜዲንስኪ» እነኝህ ከአሜሪካ፤ ከዩክሬን እና ከራሺያ በሰላም ጉዳይ የሚተጉ ሊቀ ሊቃውንታት ናቸው። ምእራፍ ፲፯ ሰላም አብዝቶ ቅንነትን ይሻል። ሰላም አብዝቶ ሰብዓዊነትን ይጠይቃል። ሰላም አብዝቶ አወንታዊነትን ይጠይቃል። ሰላም አብዝቶ አድማጭነትን ይጠይቃል። ሰላም አብዝቶ መከባበርን ይጠይቃል። ሰላም አብዝቶ ታጋሽነትን ይጠይቃል። ሰላም አብዝቶ አድማጭነትን ይጠይቃል። • ሰላም አብዝቶ የትውልድ ኃላፊነትን እና ተቀባይነትን የመቀበል ልዩ አርቆ አሳቢነትን ይጠይቃል። • ሰላም ናፋቂ ጥርስ ፋቂ አይደለም፤ ጥላቻን ሃራም ባይነት እንጂ። ጥላቻን ከሥሩ ለማድረቅ ቂም፤ በቀል፤ ግለኝነትንመንቀል የሚችል ብቸኛው ጎዳና የሰላም ሐዋርያነት ዕድሉን ሲያገኝ ብቻ ነው። ይህን አቃለው፤ ይህን አጣጥለው ሊዩ የሚፈልጉ ሰብዕናወች ፍላጎታቸው አሳቻ ነው ማለት ይቻላል። ሰላም የትውልድ መዳኛ ነውና። • የሰላም #...