ስለተከደነ።
እንኳን ደህና መጡልኝ። ስለ ተ ከደነ። „የመከረኝን እግዚአብሄር እባርከዋለሁ።“ መዝሙር ፲፬ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 13.03.2019 ከእመ ዝምታ - ከሲዊዘርላንድ እንዴት ናችሁ ውዶቼ? ደህና ናችሁ ወይ ዛሬ ከፍቶታል። የደነዘዘው ቀን ነው። እኔም አውሮፕላን አደጋ ሲከሰት ድርጭት ነው የምሆነው። ይጨንቀኛል። ለደረሰው አደጋ ብቻ ሳይሆን የአውሮፕላን አደጋ ሲደርስ እጅግ የሚያሳስበኝ ያን ተከትለው ተጨማሪ ተከታታይ አደጋዎች ደግሞ ስለሚከሰቱ ነው። ይህ ስለምን እንደሆን እኔ እንደማስበው በሌሎች አገር አብራሪዎች ላይ አደጋው ተጨማሪ ስትረስ ስለሚፈጥር ይምስለኛል። ስሊዚህ አንድ አደጋ ሲደርስ ተከታይ ሌላ አደጋ ደግሞ ይኖራል የሚል ተጨማሪ ስጋት ያድርብኛል። ያው እኔ የግሎባል የበረራ ቤተኛ ከሆንኩኝ ዓመታት ተቆጠሩ። ብረሳው፤ ብተወው ደስ ይለኝ ነበር ግን ከነፍሴ ጋር ባላሰብኩበት ሁኔታ ተጠባቀ። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ አዬር መንገድ በድንገተኛው አደጋ ሳይደናቀፍ ተግባሩን በተለመደው መንገድ በትጋት መቀጠሉ በውነቱ የአመራሩን ብቃት ደረጃ ከፍ አድርጎታል። እነ አጅሬ ካለልካቸው ገብተው ደግሞ ለወደፊቱ ካላተራመሱት። https://www.youtube.com/watch?v=7StjNwkYTAM አስደሳች ዜና የተከሰከሰውን አውሮፕላን አስመልክቶ ከአቶ ተወልደ አውን የተሰጠ መግለጫ የሆነ ሆኖ ዛሬ ምንም ዜና የለም። የኢትዮጵያ መንግሥትም ዜናውን ተግ እንዲል ያስ ደረገ ይመስለኛል። በተጨማሪነት ሌሎችም ተጨማሪ አገሮችም የተወሰነ ጊዜ ማዕቀብ በቦይንግ 737 ማክስ 8 እንዳደረጉ ዓለም አቀፍ ዜናዎች እዬዘገቡ ነው። አውስትራልያ...