ዴሞክራሲ ቃሉ ሳይሆን የህሊና ማሳው ነው ዕውነትነት።
ቁልፍ። „እንሆ አፌን ከፍቻለሁ አንደቤተም በትናጋዬ ተናግሯል።“ መጽሐፈ ኢዮብ ምዕራፍ ፴፫ ቁጥር ፪ ከሥርጉተ ሥላሴ 08.08.2018 ከጭምቷ እናትዬ ሲዊዝዬ። v መክፋቻ። የእኔዎቹ እንዴት ናችሁ ዛሬ የሰነባባቱን ቃለ ምልለሶች ጹሑፎች ቅኝት ላይ ነበርኩኝ እና ይህን ደግሜ በአዲስ እርእስ ማቅርብ ፈልግሁኝ። ስለምን? ዋናው ቁልፍ ጉዳይ ስለተዘነጋ፤ በዛ ላይ የተስተዋሎት አትኩሮት ስሌለ ነው። አቤቱታዬ ለጠ/ ሚር አብይ አህመድ የነበረ ሲሆን በግልባጭ ለዶር ለማ መግርሳም ነበር፤ የጻፍኩት በ01.06.2018 ከሁለት ወር በፊት ነበር። እርእሱ አብይ ሆይ ! ኢትዮጵያዊ ዜጋ ከሆንኩኝማ እኔም ዘለግ ያለ ህላዊ አቤቱታ አለኝ፤ የሚል የነበረ ሲሆን ረጅሙን አቤቱታ ለእርገት ያልኩበት ቁልፍ ጉዳይ ይህን ይመስል ነበር። መጪው የምርጫ ዘመን ብቻ ሳይሆን ዘላቂ ከብክነት የጸዳ ትውልድን ለመገንባት ወሳኙ ቦታ ወሳኙ ቢሮ ላይ ነበር አትኩሮቴ። እውነት ለመናገር አሁን ያሉት የለውጥ መንፈስ የእኔ ብዬ ከዬትኛውም ተቋም ሆነ ግለሰብ ቀድሜ ብቀበለውም ይህን ለውጥ ወደ ዘላቂ አሳታፊ ሥርዓት ለመለወጥ ግን ዋነኛው አንኳር ጉዳይ ለዴሞክራ ግንባታ መሠረት የሆነው የቢሮ አደረጃጃት፤ አወቃቀር አሰራር የሰብዕና አገነባብ ከሁሉም ድርጅት በላይ በዚህ ድርጅት ውስጥ ሥርነቀል መሆን ካልቻለ ዛሬ ያዬናቸው ወይንም የምናያቸው ሐሤቶች በፍጹም ሁኔታ ቀጣይም አይሆኑም፤ ትውልዳዊም አይሆኑም። መንፈሱ ይቀለበሳል። ዴሞክራሲ ምርጫ በራሱ እንኳን ግብ አይደለም። መዋቅራዊ ህሊናዊ መርሃዊ ለውጥ ካልኖረ በስተቀር። እንኳንስ የሁሉም ነገር ጭንቅላት እንዲህ ተዘሎ ቀርቶ። እስ...