ልጥፎች

ከኤፕሪል 3, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

"ፊንላንድ ለስምንት ተከታታይ ዓመት የዓለማችን ደስተኛ ሀገር ሆና ተመረጠች፤ ኢትዮጵያስ?" BBC

ምስል
   "ፊንላንድ ለስምንት ተከታታይ ዓመት የዓለማችን ደስተኛ ሀገር ሆና ተመረጠች፤ ኢትዮጵያስ?" BBC https://www.bbc.com/amharic/articles/cdxq7yvxeq4o     "ፊንላንድ ለስምንት ተከታታይ ዓመት በዓለም ደስተኛ ሀገር ሆና ተመርጣለች።" "የተፈጥሮ መዳረሻ ከመሆን እና ጠንካራ የማሕህበራዊ ዋስትና ስርዓትን መዘርጋቷ ደስተኛ አገር ሆና ለመመረጧ ምክንያት እንደሆነ ባለሙያዎች ተናግረዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድጋፍ ባደረገለት የዚህ የዓለም የደስታ ሪፖርት ፊንላንድ ከሌሎች ሦስት የኖርዲክ አገራት ቀድማ መቀመጥ የቻለች ሲሆን የላቲን አሜሪካዋ ኮስታሪካ እና ሜክሲኮ ለመጀመሪያ ጊዜ እስከ 10ኛ ባለው ደረጃ ውስጥ ገብተዋል። በሪፖርቱ መሠረት ኢትዮጵያ 132ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ጎረቤት አገር ኬንያ 115ኛ ስትይዝ ግብጽ ደግሞ 135 ደረጃን ይዛለች። አፍጋኒስታን በሪፖርቱ ደረጃ ግርጌ ላይ በመቀመጥ 147 ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። ዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካ በዝርዝሩ ላይ ደረጃቸው ወርዶ 23ኛ እና 24ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ይህም ሁለቱ አገራት ያስመዘገቡት ዝቅተኛው ደረጃ ሆኗል። ጥናቱ እንግዳ ሰዎች ወይም የማይተዋወቁ ሰዎች ከሚጠበቀው በእጥፍ የበለጥ ደግ ሆነው መገኘታቸውን ጥናቱ አረጋግጧል። ሆን ተብሎ የኪስ ቦርሳ በመጣል ምን ያህል እንግዳ ሰዎች እንደመለሱ በማየት እና ሰዎች ይመልሳሉ ብለው ከሚጠብቁት ጋር በማነጻጸር ተለክቷል። የተመለሱት የኪስ ቦርሳዎች መጠን ሰዎች ከገመቱት በእጥፍ የሚበልጥ ሆኗል። ከዓለም ዙሪያ የተገኙ መረጃዎችን ባሰባሰበው ጥናት መሠረት የሌሎች ደግነት ቀደም ሲል ከታሰበው በላይ ከደስታ ጋር የተሳሰረ መሆኑን አስታውቋል። የኪስ ቦርሳ ጥናቱ መረጃ እ...

ትራምፕ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ100 አገራት ላይ ታሪፍ ጣሉ BBC

ምስል
  ትራምፕ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ100 አገራት ላይ ታሪፍ ጣሉ https://www.bbc.com/amharic/articles/c367prpn0d3o   "ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢትዮጵያን ጨምሮ 100 ገደማ አገራት ወደ አሜሪካ በሚልኳቸው ሸቀጦች ላይ ታሪፍ ጣሉ። ትራምፕ ረቡዕ፣ መጋቢት 24/2017 ዓ.ም. ይፋ ያደረጉት ታሪፍ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ትልቁ የዓለም አቀፍ ንግድ ለውጥ ነው። ትራምፕ በአገራቱ ላይ የጣሉት የመነሻ ታሪፍ ምጣኔ 10 በመቶ ነው። ይህ ታሪፍ መጠን ለምርጫ ቅስቀሳ ባደረጉ ጊዜ የእቅዳቸው አካል አድረገው ከጠቀሱት ቁጥር ጋር ተመሳሳይ ነው። የአሜሪካ መንግሥት ወደ አገሪቱ ምርቶችን የሚልኩ 60 አገሮች "የለየላቸው አጥፊዎች" የሚል ምድብ ውስጥ አካትቷል። በዚህ ምድብ ውስጥ የተካተቱት የአውሮፓ ኅብረት፣ ቻይና ለተከተሉት ፍትሐዊ ያልሆነ የንግድ ፖሊሲ ምክንያት ከፍተኛ የታሪፍ ምጣኔ እንደሚጣልባቸው ትራምፕ ተናግረዋል። እንደ ዋይት ሀውስ ገለጻ 10 በመቶ የታሪፍ ምጣኔ በተጣለባቸው አገራት ላይ እርምጃው ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው ከመጪው ቅዳሜ፣ መጋቢት 27/2017 ዓ.ም. ጀምሮ ነው። ከፍተኛ ታሪፍ የተጣለባቸው አንዳንድ አገራት ላይ ውሳኔው ተፈጻሚ መሆን የሚጀምረው ከሚቀጥለው ሳምንት ሚያዝያ 1 ጀምሮ መሆኑም ተገልጿል። ኢትዮጵያ ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ የተወሰኑ አገራት ምርቶቻቸውን ከቀረጥ እና ከታሪፍ ነጻ በመሆን ወደ አሜሪካ ገበያ እንዲያስገቡ ከሚፈቅደው የአጎዋ ዕድል ተጠቃሚነት ውጪ የተደረገችው ኢትዮጵያ፤ በትራምፕ ታሪፍ የተጣለባቸው አገራት ዝርዝር ውስጥ እንደተካተተች ፎርብስ ያወጣው መረጃ ያመለክታል። በኢትዮጵያ ላይ የተጣለው የታሪፍ ምጣኔ 10 በመቶ ሲሆን በዚህ መሰረት አዲስ አበባ ከመጪው ቅዳሜ...