ልጥፎች

ከጁላይ 19, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ታሪከ ብራና ከክፍል አንድ አስከ ስድስት!

ምስል
የአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ታሪክ ከክፍል አንድ እስከ ስድስት።      „አቤቱ ጣልኽን አፈረስንኽም፤ ተቆጣኽን ይቅርም አለኽን።“ (መዝሙር ምዕራፍ ፶፱ ቁጥር ፩) ከሥርጉተ ሥላሴ 19.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) ·       መቅድም። ይህን የዋልድባ አብርንታት ገዳም የተወሰነውን ክፍል እንድተርክ ያስገደደኝ ዶር አብይ አህመድ የሳይንስ እና የቴክኖጂ ሚ/ር በመነበሩበት ጊዜ „ከርምጃ ወደ ሩጫ“ የሚል ሞቶ ብሄራዊ ጉባኤ አሰናድተው ነበር። በዛ ብሄራዊ በሆነ ጉባኤ ላይ ልዩ የሆነ መንፈሳቸው በኢትዮጵያዊነት ንጽንህና የተቀዱሱ ኢትዮጵያዊ ሊቃናት የተሳተፉበት ፍጹም ንጹህ ጉባኤ ነበር። ያው የጹሑፌ መደበኛ ተካታታዮች እንደምታውቁት የኢሳቱ ጋዜጠኛ አቶ ማስረሻ ዓለሙ „ከመለስውያን ወደ ለማውያን“ የሚል አንድ ፍጹም የሆነ ጥላቻን ያነገሰ፤ ሰብዕናን የተደፈረ፤ እንዳትቀበሏቸው የሚል ጠንከር ያለ የለማ እና የአብይን መንፈስ እንደ ግል እንደ ድርጅትም ኦህዴድን የተጻጸረረ ዝግጅት ነበረው። ያን ጊዜ ወደ 22 ሺህ አድማጭ ተከታትሎታል። እዚህ የውጭ አገሮቹን ጨረሱ እና አገር ቤት ደግሞ ቡቃያ ብቅ ሲል የሰላ መዶሻቸውን እነ የተባበሩት ይዘው ወጡ … መቼም አይታክታቸውም ቡቃያ መንቀል፤ ቅናዊ ጉዞን ማገት …  ·       ፍቅራዊነት እና ኢትዮጵያ። እኔ ደግሞ ዶር አብይ አህመድ እና ዶር ምህረት ደበበን በንጽሁ ህሊናን አደረጃንት፤ እንዲሁም ዶር ገምቺስ ደስታን  በብልህ አመራር እና አስተዳደር ሳይንሳዊ ትንተና ቀደም ብዬ ለፍቅራዊነት ፕሮጀክቴ አህጉራትን ሳስ አፍሪካ ላይ ነፍስ ያለው ተግባር የሚከውኑ ስለመሆኑ መረጃ አገኘሁኝ። በዚህ ስሌት በህሊናዬ ውስጥ ለእነኝህ የመልካምነት ብቃት ብልሃት መምህ

አብዩ ገላገለው!

ምስል
   ጌታን ተማጸንኩኝ!                    ከኤፍራታ ኃይሉ (ኮሎንቦስ ኦሃዩ - USA።)                       በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ                     አህዱ አምላክ። አሜን!        እንደምን አድረሃል? ሰላም ነህ ውዳችን?        ጌታ ይጠብቅህ አንተ ነህ ተስፋችን።        የትናንትን ጭንቀት ሁሉም በያለበት        ለመኖር ዋስትና ምንም በሌለበት፤        ወጥቶ ለመግባቱ ድፍረት ለተሳነው        አንተ ደረስክለት አምላክ ገላገለው።        ወይ ዶር አብይ እኔስ ሳሳሁልህ        ጌታን ተማጽንኩኝ ሁሌ እንዲጠብቅህ።         v  ሥ ጦታ ለጠቅላይ ሚ/ር ዶር አብይ አህመድ።         ወስብሃት ለእግዚብሄር።