ታሪከ ብራና ከክፍል አንድ አስከ ስድስት!

የአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ታሪክ ከክፍል አንድ እስከ ስድስት።
    
„አቤቱ ጣልኽን አፈረስንኽም፤
ተቆጣኽን ይቅርም አለኽን።“
(መዝሙር ምዕራፍ ፶፱ ቁጥር ፩)
ከሥርጉተ ሥላሴ 19.07.2018
(ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ)


  • ·     መቅድም።

ይህን የዋልድባ አብርንታት ገዳም የተወሰነውን ክፍል እንድተርክ ያስገደደኝ ዶር አብይ አህመድ የሳይንስ እና የቴክኖጂ ሚ/ር በመነበሩበት ጊዜ „ከርምጃ ወደ ሩጫ“ የሚል ሞቶ ብሄራዊ ጉባኤ አሰናድተው ነበር። በዛ ብሄራዊ በሆነ ጉባኤ ላይ ልዩ የሆነ መንፈሳቸው በኢትዮጵያዊነት ንጽንህና የተቀዱሱ ኢትዮጵያዊ ሊቃናት የተሳተፉበት ፍጹም ንጹህ ጉባኤ ነበር።

ያው የጹሑፌ መደበኛ ተካታታዮች እንደምታውቁት የኢሳቱ ጋዜጠኛ አቶ ማስረሻ ዓለሙ „ከመለስውያን ወደ ለማውያን“ የሚል አንድ ፍጹም የሆነ ጥላቻን ያነገሰ፤ ሰብዕናን የተደፈረ፤ እንዳትቀበሏቸው የሚል ጠንከር ያለ የለማ እና የአብይን መንፈስ እንደ ግል እንደ ድርጅትም ኦህዴድን የተጻጸረረ ዝግጅት ነበረው። ያን ጊዜ ወደ 22 ሺህ አድማጭ ተከታትሎታል። እዚህ የውጭ አገሮቹን ጨረሱ እና አገር ቤት ደግሞ ቡቃያ ብቅ ሲል የሰላ መዶሻቸውን እነ የተባበሩት ይዘው ወጡ … መቼም አይታክታቸውም ቡቃያ መንቀል፤ ቅናዊ ጉዞን ማገት … 

  • ·      ፍቅራዊነት እና ኢትዮጵያ።

እኔ ደግሞ ዶር አብይ አህመድ እና ዶር ምህረት ደበበን በንጽሁ ህሊናን አደረጃንት፤ እንዲሁም ዶር ገምቺስ ደስታን  በብልህ አመራር እና አስተዳደር ሳይንሳዊ ትንተና ቀደም ብዬ ለፍቅራዊነት ፕሮጀክቴ አህጉራትን ሳስ አፍሪካ ላይ ነፍስ ያለው ተግባር የሚከውኑ ስለመሆኑ መረጃ አገኘሁኝ።

በዚህ ስሌት በህሊናዬ ውስጥ ለእነኝህ የመልካምነት ብቃት ብልሃት መምህራን የመንፈሴ ቤተኞች አድርጌ በህሊናዬ ሴብ አድርጌያቸው ነበር። አስቀድሞ ቦታ ነበራቸው ከውስጤ ለውስጤ።

እናም ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙን ለዛውም የቤተ መንግሥቱን ጋዜጠኛ፤ ትንሳኤና ህይወት እኛ ነን ብለው ባወጁበት ወቅት  አሁን እማ በዓይኔ መጣችሁ ብዬ አብይ ኬኛን! ከመግቢያ እስከ ክፍል ስድስት በዝርዝር ሰራሁት።

ይህን እዬሠራሁ እያለሁኝ አንድ ጊዜ በፃፍኩት ጹሑፍ „አብይ ክሰትት ነው“ ብዬ በጥር 01.2018 የዓመቱ የመክፋቻ ጹሑፌ ላይ https://sergute.blogspot.com/2018/05/01.html

ስለ ኢትዮጵያ የምህዋር ሊቅነት ዶር አብይ አህመድ ስለገለጹት ታሪክ ቀመስ ትራስ አስፈለገኝ …

 

·      ግዕዝ የሚስጢራት እጬጌ!

 

የዋልድባ እና የቦረና የቀደምት የሥነ ፈለግ ምርምር አሁን እንኳን መልስ ለመስጠት ያልቻለበት ሞጋች እጅግ የቀደመ፤ እጅግም ስልጡን የሆነ ቅምጥ የምህዋር የሳይንስ ጥበብ ፍስፍና ቅርስ እንዳለን በዛ „ከርምጃ ወደ ሩጫ ጉባኤ“ ላይ የጉባኤው ሰብሳቢ ዶር አብይ አህመድ የሰብሰባውን ማጠቃለያ ሲያቀርቡ ስለገለጹት እኔም ማመሳከሪያ  ለሙግቴ ስለቀረብኩት አንዳንድ ጥያቄዎች፤ ስለዋልድባ ታሪክ ስለመጣልኝ ከእኔ ይልቅ እዛው የተፈጠሩ፤ አባታቸው አግላጋይ የነበሩ፤ 

ወደ ዋልድባ ለሚሄደው ማህበረ ምዕመን ሁሉ ሁሉ ዓመት ይዞ እስከ ዓመት 365 ቀናት ሳይጓድል ቤቱ ክፍት ሆኖ መንገድ ላይ ቆሎ እና ጠላ ስንቅ የሚቀርቡት ቅዱስ አባት ልጅ የጻፉትን ለማስረጃነት ማቅረብ ግድ አለኝ እና ይህን የመጸሐፉን የተወሰነውን ታሪክ በንባብ አቀረብኩት።

እግረ መንገድም ወልቃይት እና ጠገዴም የጎንደር ግዛት ስለመሆኑ መጸሐፉ አሳምሮ ይገልጸዋል። የመጸሐፉ ሽያጭ ግዴታ የጣለው ለዛው ለአካባቢው ተዋላጅ ህዝብ ነው። 

ስለዚህ በጣምራ ሁለቱን የታሪክ መሰረቶች ለማገናዘብ ያስችላል በሚል ቅናዊ መንገድ የሠራሁት ትረካ የመጨረሻውን ክፍል ዛሬ ፖስት አደረኩት።

እርግጥ ነው መጽሐፉ ቀሪ ሃሳቦች አሉት እኔ የፈግሁት ለመነሻነት የሆኑ ታሪካዊ መሰረቶችን ብቻ ስለነበር ይሄ በቂ ይመስለኛል።
  • ·      ታሪኩ የእናት ኢትዮጵያ ልጆች ሁሉ ነው።

ይህ ታሪክ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ታሪክ ነው። ለዚህም ነው በአንድ ወቅት እጅግ የማክበረውን ኡስታዝ አህመድ ጀቢልን የቀረህ ነገር አለ፤ ግዕዝን አጥና ብዬ ማሳሰቢያ የጸፍኩለት። 

ግዕዝ ለገሃዱም ለምንፈሳዊውም ህይወት የሚስጢሮች ሁሉ አናት፤ ቁልፍም ነው። ግዕዝን በመደበኛ የተማሩ ዕድለኞች ሁሉ ነገር አላቸው።

ባለመታደል ገፍቼ ባልሄደበትም እና ባቆርጠውም ግዕዝ ያለውን የዕውቀት ዲካ የሚያክል ማንም የለውም። እንግዲህ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሊቀ ሊቃውንታትም ሁኔታው አለመቻችላቸው ብሎ ነው እንጂ ሰማይ እና መሬትን የሚያስማማ ረቂቅ ዕውቀት አላቸው።

ግዕዝ የተማሩ ኢትዮጵውያን ሊሂቆች ናቸው በዓለማዊ ኑሮም ቢኖሩም እንኳን የሚዋሱት የሌላቸው፤ ግዕዝ ዓለም መዳፉ ውስጥ ናት ያለችው።

የአውሮፓን ስልጣኔ አብሶ የጀርመን የዓለም የመዳህኒት አንጎል የሆነው „መጸሐፈ ፈውስ“ ምንጩ ግዕዝ ነው። አውሮፓ ላይ ሳይንቲስት የተባሉት ሁሉ መሠረታቸው ከዛ ጋር በፍጹም ሁኔታ የተስማማ ነው። 

ለዚህ ነው ጀርመን እኛ የናቅነውን፤ ከቁብም ያልቆጠርነውን፤ ንቀን ላቲንን የሙጥኝ ስንል ልጆቹን ዩንቨርስቲ ከፍቶ እያስተማረ ያለው። ሙያ ነው። የሚረቁበት፤ ፍስፍና ነው የሚጠበቡበት ግዕዝ በጀርመን። ለዛውም ላቲንን ገፋ አድርጎ ማለት ነው ጀርመን። የመኖርን የሥልጣኔን ልቡን አግኝቶታል ጀርመን!
ግዕዝ እና ሁለመናንት።

አባቶቻችን ሁሉም ነበራቸው። ፈጣሪም ቅንነታቸውን አይቶ የዓለምን ሚስጢር ገልጦላቻዋል። የኢትዮጵያ እስልምና ቁራንን በአረብኛ ከመቅራት በግዕዝ መቅራት ጀምሩ ሁሉ ብዬ አስተያዬት ጽፌ ነበር። የትውስት ቤት የሚያስኬደን ምንም ነገር ስሌለ። ወደ ውስጣችን በተመለስን ቁጥር የውስጥ ሰላማችን ዘበኛው እሱው ራሱ እኛዊነት ይሆናል።

ታውቃላችሁ ቤተክርስትያናችን እንኳንስ እስልምና አካሏን ቅርቶ፤ ውበቷን ቀርቶ ስለ ቡድሂዝም ትምህርት እንደምትሰጥ። አያቴ ለእኔ ይነግሩኝ ነበር።

እና ከልጅነት እስከ እውቀት ከልቤ የገባ መንፈሳዊ ምስጋና ሲኖረኝ ጣቶቼን አጣምሬ ነው ጉንብስ ብዬ እምቀበለው። ልክ እንደ ቡድሃ ሃይማኖት አማንያን። በልጅነቴ የተቀረጽ ስለሆነ።

እንደ ጊዜ አያቴን መንገድ ላይ አገኘሁት እና አንድ ቦታ አብሬ ይዤው ስሄድ „አላህ አክብር“ ሲል ይሄውልሽ እኔ እና አንቺ በጋህዱ ዓለም ጉዳዮች ላይ ነን በዚህች ደቂቃ እነሱ ደግሞ ፈጣሪያችን ያመሰግናሉ ነበር ያሉኝ።

የወጣለት ዓራት ዓይናማ ሊቀ ሊቃውንት ነበር። የታወቀም። ድምጹ ራሱ ምን ብዬ ልግለጸው፤ ርጋታው፤ ወረቡ፤ ማህሌት ሲቆም አቋቋሙ፤ ቅኔ ዘረፋ ላይ ያለው ጥሞና ትዝ ይለኛል። ማዕረጉም መላዕክ ብርሃንነት ነበር፤ የአባቱም የታናሽ ወንደሙም እንዲሁ በዚህ የቤክርስትያናችን ቅብዕ ክብር ነበር የሚጠሩት። ነፍሳቸውን ይማርልኝ። ለነገሩ ሦስቱም ሞታቸውን አውቀው ቤተሰብ መርቀው፤ ተሰናብተው ነው ያረፉት።

ምን ለማለት ነው የእጬጌው ሊቀ ሊቃውንታት ትምህርታቸው ጥልቅ ነው፤ ሚስጢርን ለማወቅ ደግሞ የሃይማኖት፤ የቀለም፤ የደንበር፤ የወሰን፤ የአህጉር ክትር የላቸውም። ልጅ ሰለነበርኩኝ የመጸሐፉን እርእስ ረስቸዋለሁኝ እንጂ ስለቡድሂዝም የሚጠናበት መጽሐፍ ሁሉ እንደ ነበር ነግረውኛል እንኳንስ ቁራዕን።

ቅዱሱ መጸሐፍም „ሁሉን መርምሩ የሚበጃችሁን ውሰዱ“ ነው የሚለው። ለዚህ ነው „ድምፃችን ይሰማ ነኝ“ ብዬ ለመወጣት ችግር ያለነበረብኝ። ህሊናዬን የቀረጹበት ጥበብ ወጣ እንዲሆን እንጂ የሚአረገርግ እንዲሆን ስላልነበር።

አሁን ከዚህ ጓደኞቼ ከመንፈሴ ጋር የገጠሙት እንጂ ጎንደሬ ፍለጋ ሄጄ አላውቅም፤ እነሱም ጎንደሬዎቹ፤ ጎንደሬ ናት ብለው እኔን በማፈላለግ የሚያባክኑት ጊዜ የለም።  ለሁለታችንም ጉዳያቸው አይደለም።

ቤተሰብ በ እኔ ላይ ብዙ ተስፋ ነበረው፤ በ አባቴም ወገን ሆነ በእናቴም፤ ስለዚህም የተለዬ አትኩሮት ለእኔ ነባራቸው፤ በተለይ እናቴ ወገኖች ሰፊ ነበር። 


ዛሬም እንደዛ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁኝ። የሆነ ሆኖ አያቴ ለእኔ የሚያጠፉት ጊዜ ሃይማኖታዊ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ዕውቀት ተኮር ላይ ነበር። ጠቅሞኛልም። 

የትኛውን ፈተና ለመዳኘት። ተስብሬም ላለመቅረት፤ በተለያዬ መንገዶች ጥረትን ለመድፈርም። ሌላው ፖለቲካዊ ህይውቴንም አለቆቼም እንደዚሁ ደክመውለታል።  

ወደ ቀደመው ምልስት ሲሆን የፍቅራዊነት ፕሮጀክቴን ስሰራ፤ ህሊናን መግራትን በሚመለከት ዓለም የዘረጋቻቸውን አውታሮች ለመፈተሽ ሳስብም እንዲሁ ካለምንም መጨናነቅ ነው የምሰራው። 

የቡድሃ ዕምነት የፍቅር መሪን Dalai Lama  ጽኑ ተግባር ለመከታተል ንግሮቻቸውን ለማድመጥ፤ ሜዲቴሽን የመልካምነትን መንፈስ በማበልጸግ እረገድ ያለውን አቅም ለመለካት በራሴ ላይ ስፈትነው፤ ዮጋን በሰውነት አደረጃጃት እና አመራር ላይ ያለውን አቅም ለመለካት፤ በውስጥ ሰላም በመስጠት እና መንፈስን በማሰባሰብ ላይ ያለውን በጎ ተጽዕኖም በራሴ ላይ ለመፈትን አልተቸገርኩኝም።

ይህን ቀደም ብለው ሊቀ ሊቃውነቱ አያቴ ቀድመው ህሊናዬን ባያሰናዱት አልደፈረውም ነበር። ስለምን? ዬየትኛወን ሃይማኖቱ ተጽዕኖ አግልዬ ስለመምለከተው።

የራሴ ዕምነት አለኝ ግን የሌሎችንም መልካምነትን ለማፍለቅ በሚደረግው ጥረት ውስት የዓለምን ጉማዊ ዘመን ለመዋጋት ያላቸውን አስተዋፆ ከፍቅራዊነት ፕሮጀክቴ ጋር ለማያያዝ ሆነ ለማወረራስ፤ እንዲሁም ግንዛቤዬን ለማስፋት በርቀት ለመመልከት አገዘኝ።

አሁን ዶር ምህረት ደበበ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ሰባኪ ናቸው፤ ግን በዛ ውስጥ ያሉትን ዘመናዊ የሆኑ ህሊን ወደ በጎነት በሥልጡን አቀራረብ፤ በዲጂታላዊ መንገድ ለማስረዳት የሚያደርጉት ጥረትን ለማዬት፤ ላመድመጥ፤ ቃለ ምልሳቸውን አድኜ ለመከታተል በሃይማኖት ያለን የልዩነት አቋም አለገደበውም።

ምክንያቱም እኔ በዚህ ሰው ሰብዕና ውስጥ ይህን ድፍርስ አለም የሚያጠራ፤ የሚገራ፤ መጣሪያ፤ ማንጣለያ አለ ብዬ ስለማመን ልክ እንደ Dalai Lama.  

ወላጆች፤ ቤተሰቦች አትኩሮት ሰጥተው የህሊና ችግኙን ባለታሠረ የመንፈስ ነፃነት ቢያበቅሉት ዓለም እንዲህ የስጋት ምንጭ ባለሆነች ነበር። በጣም ነፃ መንፈስ ነው ያለኝ። የሚሰማኝን ለመግለጽ ምንም ገደብ የለኝም። ነፃ አድርገው ስላሳደጉኝ።

ዓለም ታስፈራኝ አለች፤ ከዛሬውም በላይ ነገ … ለዚህም ነው ወላጆች ልጆቻቸውን እንዴት ቢያሳድጉ ብቁ ትውልድን መገንባት ይቻላል የሚለውን „የተስፋ በርን“ እንዲሁም የትወልዱ መሠረት የሆነው ጋብቻ በመቻቻል መርህ ህይወቱ አብነታዊ እንዲሆን ምን ነገሮች ላይ ማተኮር አለበት ብዬ „ርግብ በርን“ የጻፍኩት።

ያው የግንቦት 7 ጉልበተኞች ሥሜን አክስለው፤ መክሊቴን ቀብረው መጋዘን ላይ ኤሉሄ ይላሉ የህሊና ምርቶቼ። አንዳንዶችን መንፈሳቸውን ብሎጌ ላይ እለጥፋቸዋለሁኝ።

የሆነ ሆኖ ያለህን ለማካፈል በር ዘግቶ አላሳልፍም፤ አናሳልፍም ማለት ከወንጀል በላይ ነው። ትውልድ እንዳይገለገልበትም በሩ ተከርችሟል።

ይህ ገመና እንደተያዘ ነው አሁን ደግሞ ከአቤቱ ሰማያዊ ጋር ግንቦት 7 ማጫ ላይ የሚገኙት። እግዚኦ!

አገር ቤት ከመግባታቸው በፊት እዚህ ያሰሩን ፈተው ቢሆን መልካም ነው። ሞት የሚፈቀደብት የጨለማ ጊዜ ነው የታለፈው። እኔ በሃይማኖቴ ባልታሠር መኖርን አልፈቅደውም ነበር። ሰው እንዲጠላህ፤ አንዲገድብህ በጣም በብሱ ቁጥበነት እና ንጽህና ላለ ወገንህ እንዴት ትፈርደበታለህ? ለዛውም 5 ዲቂቃ እንኳን ቆሜ አነጋግሬው የማላውቅ ፍጥረት … ሳያውቀኝ ሰው ተቀበላት ብቻ ነበር ህመሙ …

አሁን አቦ ሌንጮ ለታስ ቢገቡ አገር ቤት ዕዳ የለባቸውም … አልፈው ተርፈው በግል ህይወቴ፤ በማህበራዊ ህይወቴ፤ በራሴ ወጪ እና ጊዜ ባበከንኩት የነፃነት ተጋድሎ ላይ አላሰሩኝም፤ ጸጋዬን ብቱን ሆኖ እንዲቀር አልዘመቱበትም። ማህበራዊ ሰላሜን አለዋከቱም፤ ዛሬ እንኳን በቃችሁ አይሉንም። ኮቴ እዬተከተሉ ብዕሬን ያሳግዳሉ። መጥኔ እነሱን ለምትሸከም መሬት። ለዛውም እንዲህ ላምጣሙ ሳይታወቅ ላለፈው ህልመኝነት …

ደፋር ሳታናው ባይገጥማቸውማ በአገሬ ለውጥ ትራሴን ከፍ አድርጌ እንደተኛ እና እነሱን ደፋሪ አጥቶ የመልካምነት ሚዛን ማሰጠበቅ ባልተቻለም ነበር።

ደግነቱ አዎን ደግነቱን በአብዩ ላይ መረብ ዘርግቶ ማህበራዊ መሠረቱን ለማናጋት ከእንግዲህ አሞራው በረረ ቅሉ ተሰበረ ሆኗል። በተፈለገው ቅርጽና ይዘት ይመጣ … የፍቅርን አሃታዊ ግንብ ደርምሶ ለማሸነፍ አይቻልም ከሞት በስተቀር።

የሰይጣን ጆሮ ይደፍን እና ሞትም ቢመጣ እንኳን በጽድቅ ጎዳና ነው፤ በህሊና ውስጥ የፍቅር ሐውልት ተገንብቷል።

ለእርቅ አርበኛ ሲኖርም በምድር ሰማዕት ነው። ለዚህም ነው ልዑል እግዚአብሄር ህይወቱን ያተረፍልን የአሜኑን። እኔም ለዚህም ነበር እንቅልፍ አጥቼ ሳንክ አረም አብቃዮችን ስታገላቸው የባጀሁት። ተሳክቶልኛለም።

አሁን ስርክራኪው የግራጫ ሰብዕና ነው፤ ግራጫ ስብዕና ደግሞ ብዙም ሊደከምለት አይገባም፤ አዎንታዊነትን ስላልፈጠረለት፤ ሁሉንም ነገር የተያዘ የተረዘዘውን መርገም እና መቃወም ነው የተፈጠረበት ነው። ለማህበረ ግራጫ „ኢትዮጵያዊነት ሱስም“ ጠላቱ ነው፤ እንኳንስ ሌላው …  

·      የተምስገን ታምር!

ልዑል እግዚአብሄርም ትክክለኛውን የፍቅራዊነት ፕሮጀክቴ የሚመጥነውን ሙሴ በአገሬ ላይ አስቀምጦልኛል! ተመስገን! እኒያ ቅን የተባበሩት መንግሥታት ጸሐፊ የነበሩት አቶ ባን ኪሙን ኢትዮጵያ ላይ የፍቅራዊነት መንፈስ እንዲህ አስኳል ሲኖር ህሊናቸው ምን ይል? እስቲ የአገርሽን መንግሥት አማክሪ ብለው ነበር የመልስ ደብዳቤ የጻፉልኝ።

ምኞት እንዲህ ሲሳካ በህይወቴ የመጀመሪያው ነው። የተቃጠለው የማህበራዊ የፖለቲካ የኢኮኖሚ ህይወቴ ሁሉ ምንም አይሰማኝም። ቅኖች አሁንም ቢሆን ህሊናቸው ይህቺ ሴት ምን ስላደረገች ይሆን ያን ያህል ዘመቻው የጠናባት ብለው ወደ ራሳቸው ተመልሰው ለክፉዎች የሰም ማጥፋት ዘመቻ ላይተባባሩ ይፈቅዱ ይሆናል። ማን ያውቃል? የፈጣሪ ታምር ዘንድሮ መሬት ወርዶ ገድል እዬሠራ ነው።

እሾኾችም ይከስማሉ! ለዛውም አሁን የሲዊዝ ስደት ተቀንቶበት? መማር የለ፤ መለወጥ የለ እንደ ተፈጠርን ተከዝነን ለኖርንበት ህይወት … መኖራችን መብላት መጠጣታችን ብቻ ነው ከዛ ውጪ ምን … የባከነ የተቃጠለ ጊዜ ነው በሁሉም መስክ …   

ወደ ቀደመው ምልሰት ሲሆን ዶር አረጋይ በርሄም አገር ቢገቡ በተመሳሳይ … ሁኔታ፤ በግል ህይወቴ ላይ የፈጸሙት ህጻጽ የለባቸውም። ጓዘ ቀላል ናቸው ዕዳም የለባቸውም። … ለዛውም እኔ በጣም ነው እምሞግታቸው ግንቦት 7 ደግፌ ሁሉ መግቻቸዋለሁኝ፤  …

በማውቃች ልክ እና ባመንኳቸው ልክ መቀጠል ስላልቻሉ …

የሆነ ሆኖ ከነሴራ ድርቶው የነፃነት ነግሥታቱ ሁሉ ዘመን ረትቶት ዛሬ ለተከፉትም ላልተከፉትም እኩል አድማጭ አላዛሯ ኢትዮጵያ አለች። ዜግነት ብክት እና በዘወትር፤ ዜግነት  በእርቦ እና በሲሶ ዕድሜወን ለሰጠው ነገ ይመጣል ስከንት ግርማማ ሲሆን …

vክብረቶቼ እንሆ የአብርንታት የተወሰነው ታሪክ ይሄውና፤ 

    ከክፍል አንድ እስከ ስድስት።

   ታሪከ ዋልድባ አብረንታት፤ ትረካ አንድ 01.04.2018

         ትረካ ሁለት - የአቡነ ሳሙኤል የአብርንታት ዋልደባ ገዳም ታሪክ፤

 

        ንባብ ሦስት፤ የአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ታሪክ። (29.04.2018)

 

·        https://www.youtube.com/watch?v=uoIZmErLHHc

       ንባብ አራት የአቡነ ሳሙኤል ዘዋልደባ ገዳም ታሪክ፤ 03.06.2017

 

·        https://www.youtube.com/watch?v=dJ5jkwvbphk&t=18s

         አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ንባብ አምስት። 17.06.2018

 

·        https://www.youtube.com/watch?v=Xp5-2pWpp-o

          አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ንባብ ስድስት። 19.07.2018

 

 

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

 

ደጎቹ የመቻቻል አርበኞቹ የጹሁፌ ታዳሚዎች ኑሩልን!


መሸቢያ ጊዜ! 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።