ልጥፎች

ከጁን 17, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ለእስር ጊዜ ሦስት ዕጥፍ ቀረጥ መክፈል።

ምስል
                                ሌላ ግፍ ለእስር ጊዜ ሦስት                                         ዕጥፍ ቀረጥ                                       መክፈል ግድ ነው።                                                       ከሥርጉተ ሥላሴ 17.08.2018                                                          (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)                                  „ህልም ከመሆን ወዳለመሆን ይሄዳል በዬምሳሌውም እዬራሱ ያሳያህል።“                                                             (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፩ ቁጥር ፫) መቼም ተችሎ የተኖረው ጉድ ምን ይባል? ማን ይባል? አይታወቅም? ያው የደብረታቦር እና የባህርዳር ጉባኤ እጅግ የተመሰጥኩበት ስለሆነ ዛሬ ደግሜ ማድመጥ ፈልጌ አማራ ቴሌቪዥን ላይ አገኘሁት። ለካንስ ትናንት ከተለጠፈው የተቆራረጠ ስለነበር ነው መሰል ዛሬ ደግሞ ሙሉውን አገኘሁት። ግርም ብሎኛል። ለካንስ የእስር ጊዜም ቀረጥ በሦስት እጥፍ መክፈል አለበት አንድ እስረኛ። ያ ቀረጥ እዚህ እስር ቤት አልነበርኩም። እንግልትም አልደረሰብኝ ብሎ ነው።  ወዲህ ነው ነገሩ አንድ እስረኛ አንድ ዓምት ከስድስት ወር ከታሰረ ሲፈታ ታስሮ ነበር ተብሎ የሚሰጠው የእስረኝነት ማረጋገጫ የፍዳ ዲግሪው የሦስት ወር ብቻ ነው። ሦስት ወር ታስሮ ነበር የሚል ምስክር ወረቀት ብቻ ነው የሚሰጠው። የደገምኩት እንድታምኑት ነው። የአንድ ዓመት ከሦስት ወሩ የቆጥ የበረከቱ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ መሳፍንታት ቆሌ መቋደሻ ነው። እዚህ እስር

መደመጥ ያለበት የቅኔ ጉባኤ።

ምስል
                                   በደብረታቦር እና በባህርዳር                                          የቅኔ ጉባኤ ዕድምታ።                                                                ከሥርጉተ ሥላሴ 17.06.2018                                                                     (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ)                                                         „እግዚአብሄርን የሚፈራ ሰውነት የተደነቀች ናት።“                                                                (መጽሐፈ ሲራክ ምእራፍ ፴ ቁጥር ፲፰) ኦቦ ለማ መግርሳም ይሄን በማደመጥ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት ይኖርባቸዋል። የወገን ሰቆቃ የ አማራ እና የ ኦሮሞ መከራ እና ፍዳ በጽሞና ሊመረመርም እና ዘመን በቃችሁ ሊላቸው ይገባል። እጅግ መራራ፤ እጅግም ጎምዛዛ ጉዳይ ነው። በ ኤርትራው ቅልብ  በአቶ ሞላ አስገዶም ድርጅት የሚከሰስ የሚሰቃይ የለም በ ኦነግ እና በ ግንቦት 7 ግን ህዝብ በጨካኞች ታረሰ። አብሶ የ አማራው ፍዳ እንዴት እና እንዴት ተብሎ በዚህ ሰንሰለት ውስጥ አንደ ገባ ታሪክ ይፍረደው።  ·         ቅቤ ያጠጣኝ የአንበሶቼ ህብረ ድምጽ። መቼም ይህ የአማራ ተጋድሎ እና የኦሮሞ ንቅናቄ ያመጣው ገድል ተዘርዝሮ አያልቅም። ነፍስ ትንፋሽ አገኘች። የነፍስ ቧንቧ ተከፈተ። የታመቀ በሽታ ፈነዳ። ፋሽቱ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥርዓትም እንደተሳበው በቁሙ ሞተ። ሥነ - ልቦናው ውልቅልቁ ወጣ። አንበ

ዶር. ኦባንግ ኢትዮጵያ እና የአብይ መንፈስ ቀለበት።

ምስል
ዶር. ኦባንግ ኢትዮጵያ ሜቶ  አዲሱ የኢትዮጵያ ጠ/ሚር  ዶር. አብይ አህመድ መሪዬ፤  ጠቅላይ ሚኒስተሬ እናም  ጀግናዬም  ነው በማለት  ዕውነትን አጸደቃት።  አዬ አባ ቅንዬ - እዮብ!                                                              ከሥርጉተ ሥላሴ 06.04.2018  (ከመንኩሴዋ ሲዊዘርላንድ ዙረክ።) „አሁንም ልጆቼ ሆይ ስሙኝ ከአፌ ቃል አትራቁ።“   (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፯) ·        ወዳጄ ዶር. ኦባንግ ሜቶ ጋብቻ መፈጸምህን ሰማሁኝ ደስም አለኝ። ይህን ጹሁፍ ሳተናው ብራና ተባብሮኞኝ ለጥፎልኝ ነበር።  ዛሬ ደስታዬን ለመግለጽ በብሎጌ ለመለጠፍ ፈለግሁኝ።  ቅንነትህ እና ደግነትህ ሁልጊዜም መምህሮቼ ናቸው አና መልካም የትዳር ዘመን እንዲሆንልህ ከልብ እመኛለሁኝ። እህትህ።             መነ ሻ። https://www.youtube.com/watch?v=xzLwOtZ6UsY&t=2s „መልካም ጅማሬ ኦባንግ ይደመጥ“ ·          የማከብርችሁ የሐገሬ ልጆች ሆይ! የማከብራችሁ የሐገሬ ልጆች - ቅኖቹ እንዴት ናችሁ? ዛሬ ስለሐገሬ የሐብትም ሐብት ለዛውም የመንፈስ ስለሆነው ሰለ አቶ ኦባንግ ሜቶ / ዶር. ኦባንግ ኢትዮጵያ/ ትንሽ ነገር ማለትን ፈቀድኩኝ። አቶ ኦባንግን እኔ የማውቀው ንጹህ መንፈሱን ነው። ይህ ንጹህ መንፈሱ ደግሞ ለሰው ሁሉ የተመቸ እና ለሰዋዊነት የተፈጠረ፤ ለዛም የሚታገል ስለሆነ ረጅም ጊዜ ሆነኝ ፈቅጄ እና ወድጄ የዶክትሬትነት ክብርን ከሰጠሁት። ግር እንዳይላችሁ ማዕረጉን የሰጠሁት እኔው እራሴው ነኝ። እኛ እኮ ባንታደል እንጂ እሱ የብዙ ዓለምዐቀፍ የሰላም እና የ