መደመጥ ያለበት የቅኔ ጉባኤ።

                                   በደብረታቦር እና በባህርዳር 
                                        የቅኔ ጉባኤ ዕድምታ።
                                                               ከሥርጉተ ሥላሴ 17.06.2018 
                                                                   (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ)

                                                        „እግዚአብሄርን የሚፈራ ሰውነት የተደነቀች ናት።“ 
                                                              (መጽሐፈ ሲራክ ምእራፍ ፴ ቁጥር ፲፰)

ኦቦ ለማ መግርሳም ይሄን በማደመጥ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት ይኖርባቸዋል። የወገን ሰቆቃ የ አማራ እና የ ኦሮሞ መከራ እና ፍዳ በጽሞና ሊመረመርም እና ዘመን በቃችሁ ሊላቸው ይገባል። እጅግ መራራ፤ እጅግም ጎምዛዛ ጉዳይ ነው። በ ኤርትራው ቅልብ  በአቶ ሞላ አስገዶም ድርጅት የሚከሰስ የሚሰቃይ የለም በ ኦነግ እና በ ግንቦት 7 ግን ህዝብ በጨካኞች ታረሰ። አብሶ የ አማራው ፍዳ እንዴት እና እንዴት ተብሎ በዚህ ሰንሰለት ውስጥ አንደ ገባ ታሪክ ይፍረደው። 
  • ·        ቅቤ ያጠጣኝ የአንበሶቼ ህብረ ድምጽ።

መቼም ይህ የአማራ ተጋድሎ እና የኦሮሞ ንቅናቄ ያመጣው ገድል ተዘርዝሮ አያልቅም። ነፍስ ትንፋሽ አገኘች። የነፍስ ቧንቧ ተከፈተ። የታመቀ በሽታ ፈነዳ። ፋሽቱ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥርዓትም እንደተሳበው በቁሙ ሞተ። ሥነ - ልቦናው ውልቅልቁ ወጣ። አንበሶቼ በደብረታቦር  በዶር አንባቸው መኮነን ባህርዳር በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሰብሳቢነት በተካሄደው ጉባኤ ላይ ቅቤ ጥጥት አድርጎኛል።

ፋሽስትነት ሲያነሰው ነው ወያኔ ሃርነት ትግራይ። የሰው ልጅ ቀን ከሌት ተሰቅሎ ጨርቅ ልበሱ እንደ ሙት እሬሳ በማዕከላዊ ኤሉሄ የሚልበት ገመናው የልጅ ልጅ ካወጣለት የሚታይ ይሆናል። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ደቡብ ጎንደር ያሰረውን ኤርትራ ልሄድ ወደ ግንቦት 7 ሊሄድ እያለ የጎንደርን ህዝብ በሌለበት አምክንዮ ሲያርድ የኖረበት አመክንዮም ተቃጠለ። ግንቦት 7 በዚህ አለኽሆኝ በዛ አለሁኝ እያለ አማራን ሲስቀቅል የኖረበት ገመናው ዘመን ፈታው። አማራ ለሁለቱም እንደ ጥንቸል የመሞከሪያ ጣቢያ ነበር። አሁን በዘመነ እርጋ ደግሞ ጭምቶች የታሸገውን የሚስጢር ክዳን ከፈት አድርገው ቢመረምሩት የሰመኗቱ ግርግር ከዬት ተነስቶ የት እንደ ደረሰ ማገናዘብ አያቅታቸውም። ይህን ብልህነትን የሰነቁ ሰሞኑን ስብሰባ ሲካሄድ ከሚነሱ ጥያቄዎች ማገናዘብ ይቻላሉ። እንዲህ እና እንዲያ ነው የእነቶኔ ነገር  … አቅም ሲጣፋ፤ አቅል መዘቅዘቅ። ማጣፊያ ሲያጥር ሌላ መውጫ በር መሻት …
  • ዓራት ዓይናማዎቹ ከታደሙበት ቅኔ … ትንሽዬ   

„ብአዴን ባዶ የቀፎ ስልክ ነው የትግራይ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሴሚ ካርድ ነው። ብአዴን ባዶ ጆንያ ነው እህል የሌለው። አንተ ትሻለለህ ያላችሁኝ ከተኙት ቁጭ በማለቴ ነው፤ ሦስት ጊዜ የሚጣደው ጀበና ነው ብለህ አሻም በለው፤ አንዱ ቦታ ላይ አንስቶ ሌላ ቦታ ወስዶ መጎለት“ ምን ያልተዘረጋ ቅኔ አለ። የቅኔ ጉባኤ ነበር። ወጣቶቹ ሽበት በሽበት ሆነው በቀያቸው መቀመጫ አጥተው አንድ ሁለት ሦስት አራት እያለ 27 ዓመት ተደረሰ። አሁን ዶር አንባቸው መኮነን ይሄን ሰምተው ሄደው የአማራን የክስ ጭብጥ ማስተካካል እና አማራ ላይ የወረደውን ማዕት ግፍ በደል እና ስደት ዕውቅና አስጥቶ ይቅርታ ማስጠዬቅ፤ ካሳ ለሚያስፈለግቸው ካሳ ማሰጠት ግድ ይላቸዋል። በቀያቸው በባድማቸው ይህን ያህል እንግልት ይህን ያህል ፍዳ። ቆሰልኩኝኝኝኝ ….

ሌላው የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሰከን ያለው ትንተና ከጠበቅኩት በላይ ጥልቀት አለው። መሪ እንዲህ ሲሆን ይበል ያሰኛል። እራስን ዝቅ ለማድረግ የሄዱበት መንገድም አንሶኛል ከዚህ በላይ ይሄንም ይሄንም በጣምራ እከሉልኝ ከሚሉት ጋር ሲታይ የጸጋ ልዩነቱ ወለል ብሎ ይታያል።

የኔዎቹ ክብረቶቼ በእኔ የብራና ጠብታ ጊዜያችሁን ከምወስድ እስኪ ዕለተ ሰነብትን በዚህ ታደመሉልኝ - በአክብሮት። ወገኖቻችን በግራ በቀኝ ተሰቅዘው የኖሩበት የመከራ ዘመን ያማል። ያቆስላል። ውስጥን ይፈትናል ግን ደግሞ ጀግኖቼ ለትክክለኛው ሰው ትክክለኛው ጊዜ ላይ ስለተነገሩት አስደስቶኛል። እጅግ ጥልቅ ዕውቀት ያላቸው አነስቶች … ወጣት ተብዕት ሁሉም የልብ አድርስ ሆነው አግኝቻቸዋለሁኝ። 

ብቃታቸው፤ ልቅናቸው፤ ያነሷቸው ነጥቦች ፍሬ ያለው ሲያደምጡት ውለው ቢያድሩ የማይጠገብ ነው። ቁሰል ብልም ግን ደስ ብሎኛል። ይሄ አማራ ድርጅት የሚባል ሁሉ ከሌላ ጋር እዬተለካለከ ለዳግም የነፃነት ገፈፋ ብርንዶ ህዝባችን እናዳይሆን ግን መትጋት ግድ ይላል። ይህ  ለይደር የማይቀጠር የፊት ለፊት የተጋድሎ መስመራችን ነው … ይህ እንግዲህ ደብረታቦር ባህርዳር ላይ ነው። በጠላት እጅ የወደቁት ወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ራያ እና መተከል እማ የቀን ጨለማ እንደዋጣቸው ነው። ታሪክ መቼም ለዶር አንባቸው መኮነን እና ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የጣለባቸው አደራ እጅግ ግዙፍ ነው? „እግዚአብሄርን የሚፈራ ሰውነት የተደነቀች ናት።“

·        በዶር አንባቸው መኮነን ደብረታቦር ላይ የተካሄደው የቅኔ ጉባኤ

በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረ ታቦር ከተማ የተካሄደው ክፍል 2 የወጣቶች ውይይት
·        በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሰብሰቢነት የተካሄደው የባህርዳሩ የቅኔ ጉባኤ
ርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸውና የባሕር ዳር ወጣቶች ያደረጉት የምክክር መድረክ
·        አንበሳው ሲያገሳ፤

የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣኖችን ሙልጭ አድርጎ የተናገረው ጀግና ወጣት

·        እኛም አለንልህ አማራ ይላሉ ሙሁራኑ የታሠሩበት ሰንሰለት ስለወለቀ ደፈር ብለዋል፤

የሙሁራን ተቆርቋሪነትም አጋጣሚው መፍቀዱን ያሳያል።

የአማራ ምሁራን ክልሉን ለማሳደግ መማክርት አቋቋሙ፡፡

·        ባለቅኔው ጠ/ ሚር እና ውስጣቸው

Ethiopia: / አብይ ለደቡብ ህዝቦችን ያስተላለፉት ምስጋና
በተረፈ ትግል ሲባል በጣራ ትግል፤ ነፃነት ሲባልም በጣራ ፍላጎት ካልሆነ አቅምን ማባከን ጅልነት ነው። ማገዶነትን አማራ በቃኝ ማለት አለበት።
„አማራነት ይከበር!“
የአማራነት ማገዶነት ይቁም!
የኔዎቹ መልካም የመደማመጥ ጊዜ ይሁንላችሁ።

 




አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።