ዶር. ኦባንግ ኢትዮጵያ እና የአብይ መንፈስ ቀለበት።

ዶር. ኦባንግ ኢትዮጵያ ሜቶ 
አዲሱ የኢትዮጵያ ጠ/ሚር 
ዶር. አብይ አህመድ መሪዬ፤ 
ጠቅላይ ሚኒስተሬ እናም 
ጀግናዬም ነው በማለት 
ዕውነትን አጸደቃት። 
አዬ አባ ቅንዬ - እዮብ!
                                                            
ከሥርጉተ ሥላሴ 06.04.2018 
(ከመንኩሴዋ ሲዊዘርላንድ ዙረክ።)
„አሁንም ልጆቼ ሆይ ስሙኝ ከአፌ ቃል አትራቁ።“ 
(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፯)

·      



ወዳጄ ዶር. ኦባንግ ሜቶ ጋብቻ መፈጸምህን ሰማሁኝ ደስም አለኝ። ይህን ጹሁፍ ሳተናው ብራና ተባብሮኞኝ ለጥፎልኝ ነበር። 

ዛሬ ደስታዬን ለመግለጽ በብሎጌ ለመለጠፍ ፈለግሁኝ። 

ቅንነትህ እና ደግነትህ ሁልጊዜም መምህሮቼ ናቸው አና መልካም የትዳር ዘመን እንዲሆንልህ ከልብ እመኛለሁኝ። እህትህ። 




  •           መነሻ።

https://www.youtube.com/watch?v=xzLwOtZ6UsY&t=2s „መልካም ጅማሬ ኦባንግ ይደመጥ“
·         የማከብርችሁ የሐገሬ ልጆች ሆይ!

የማከብራችሁ የሐገሬ ልጆች - ቅኖቹ እንዴት ናችሁ? ዛሬ ስለሐገሬ የሐብትም ሐብት ለዛውም የመንፈስ ስለሆነው ሰለ አቶ ኦባንግ ሜቶ / ዶር. ኦባንግ ኢትዮጵያ/ ትንሽ ነገር ማለትን ፈቀድኩኝ። አቶ ኦባንግን እኔ የማውቀው ንጹህ መንፈሱን ነው። ይህ ንጹህ መንፈሱ ደግሞ ለሰው ሁሉ የተመቸ እና ለሰዋዊነት የተፈጠረ፤ ለዛም የሚታገል ስለሆነ ረጅም ጊዜ ሆነኝ ፈቅጄ እና ወድጄ የዶክትሬትነት ክብርን ከሰጠሁት። ግር እንዳይላችሁ ማዕረጉን የሰጠሁት እኔው እራሴው ነኝ። እኛ እኮ ባንታደል እንጂ እሱ የብዙ ዓለምዐቀፍ የሰላም እና የሰብዕዊነት ሜዳሊያ ተሸላሚ እንዲሆን በተጋንለት ነበር። ግን ምቀኞች ነን። ውስጡ ፈጣሪ አንጽቶ እንደ ፈጠረው እንደ አዲስ እንደሚወለድ ህፃን ልጅ ነው። ጥሩ ውሃ ነው። የአባቱን ስምም „ኢትዮጵያ“ እምለው ያለምክንያት አይደለም። የአቶ ኦባንግ ኢትዮጵያ ዕውነት ስለሆነች ነው። የሚያገልግላት ዕውነት ገላጩ ዕውነቱ ራሱ መሆኑ ነው። የኦባንግ ኢትዮጵያ ለሥም፤ ለዝና፤ ለክብር፤ ለሥልጣን፤ ለመሸጋገሪያ፤ ለገንዘብ፤ ሁከት ለመፈብረክ የታጨች አይደለችም። ለእናትነት ክብሯ የተሰጠ ዕንቁነት እንጂ። ሁሉ እንደሱ ነገሮችን በቅንነት ለማዬት ባይችል እንኳን የመልካም ነገሮች እንቅፋት ባይሆን ምንኛ ጥሩ በሆነ ነበር።፡

  • ·         መልእክትህ ውስጤ ነው።

የማከብርህዶር የኔታ አባንግ ኢትዮጵያ ሜቶ የምታስተላልፈውን መልክት አዘውትሬ አዳምጣለሁኝ። ለእኔ ትልቅ ዕድል ነው። እንዲህ በዬጊዜው ድምጽህን መስማት መቻሌ። በአንተ ውስጥ ያለው ንጹህ ነገር ፍቅር ብቻ ነው። ሰፋ አድርገህ በባለሙያ ትንሽ ነገር አክለኸበት ጥራቱ የጠበቀ ብታደረግው ደግሞ የሌላም ጥገኛ አያደርግህም። በፈለግከው ጊዜ ከእኛ ጋር ትገናኛለህ። ከእንተ እኮ የሚቀዳው የመልካምነት መስኖ ነው። ከአንተ መንፈስ የሚመነጨው የሰላም ማር ወለላ ነው። እንደ አንተ ያለ ታላቅ ቅን ኢትዮጵያዊ የሐገር እና የወገን ኩራት፤ የብሄራዊ ሰንደቅዓላማ ዓርማ ዋቢ የሚሆን ሚዲያ የሌለን መሆኑ እጅግ ያሳዝነኝ ነበር። ለዚህም ነበር የድርጅታችሁን የኢዲሲቱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ርዕሰ አንቀጽ „ደወል“ መደበኛ የጸጋዬ የራዲዮ ፕሮግራሜ በር ከፋች አንድትሆን በትጋት አደርጋት የነበረው። በዛውም በሎሬቱ ታቦት ትሳለም በማለት።

ድምጽህን ስሰማ እንዴት ደስ እንደሚለኝ። አማርኛ ደግሞ ቅኔ መናገር ሁሉ ጀምርሃል። አቤት እንዴት እንደሚያምርብህ ብታዬው። የዕውነት ቃናው፤ ምቱ፤ ልስላሴው እንዴት እንደሚያምር ብነግርህ ላይገባህ ይችላል። እጅግ ውብ እና ተወዳጅ ነው። ይናፍቃል! ይህን ለሰጠህ አምላክ ልታመሰግነው ይገባል። ሊያደምጥህ የሚፈልግ፤ ሊያደምጥህ የሚጓጓልህ ብዙ ሰው መኖሩ እኮ መታደል ነው አይደል? ሌላው በእንግሊዘኛ መቀላቀሉም አትሳቅቀው። ቃላቱን ቀላል አድርገህ መጠቀሙን ግን አትርሳው። ብዙ ሰው ሊረዳው እንዲችል። የብሄራዊ ንግግር ገለጣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሆነ እንደ መሪነትህ እንግሊዘኛ ከተደባለቀበት ይከብዳል፤ የተገባም አይደለም። በጣም መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ፈጽሞ እንግሊዘኛ የማይሰማ ዜጋ ስለሚኖር መልእክቱን በትክክል ማድረስ ይችግራል። ለውጪ ሐገር እዚህ ላለነው ሰብዕናን ለመቅረጽ ድርጅትህን ሳትወክል አንተን ብቻ ወክልህ በምታደርገው ንግግር እንግሊዘኛ መጠቀሙ እግረ መንገዱን ያስተምራል። ይጥማል። ውበቱም ልክ የለውም።

  • ·         ባለቤት ላጡት ስለእናት።

ለስደተኛ - አባት፤ ተቆርቋሪ ለሌላው - ደጀን፤ ሐዘን ለጠናበት እንደ ድንግል ማርያም በተጠራበት ፈጣኖ ደራሽ - ስለእናት፤ ሐገር ላጡ ወገኖቹ - የጽናት መሰረት፤ መሪን ተስፋ ለሚያደርጉ ምንዱባን - እረኛ፤ ባለቤት ላጡ የእኔ ቢጤ ከርታታ ለተገፌ ወገኖቹ - ህይወት፤ ለብቸኞቹ የአይዟችሁ - ሙሴ፤ ለጭንቀት ፈጥኖ - ደራሽ። እኔ እያለሁ ብሎ ድረስልን በታባለበት ቦታ ሁሉ ፊት ለፊት ወጥቶ አህጉር አቆርጦ፤ ተንከራቶ ከወገኖቹ መከራ ጋር አብሮ - የሚፈተን ትጉኽ ሊሂቃን፤ ራሱን ረስቶ የኖረ። ደከመኝ፤ ሰለቸኝ፤ እረፍት አስፈልጎኛል የማይል፤ በገንዘቡ፤ በጊዜው፤ በኑሮው ላይ ደንታ የማይሰጠው ከእናትም እናት የሆኖ የከበረ ተግባር የሚከውነው ድንቅ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ነው ዶር አቦንግ ኢትዮጵያ ሜቶ ማለት። የኢትዮጵያ ኦባንግ የኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያም የኦባንግ ኢትዮጵያ። ብትደምሩትም ብታባዙትም አቦንግ + አባንግ ይሆናል ኢትዮጵያ። አባንግ ሲባዛ በኦባንግም ይሆናል ኢትዮጵያ። የመንትዮሹ ፍቅር አህታዊ አዕምሮ ነው - ለእኔ። ለብሄራዊ ሰንደቁ ለልሙጡ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ታቦቱ ነው። ለእናቱ ዶር አቦንግ ኢትዮጵያ እንደራሷ፤ እንደ ፍላጎቷ፤ እንደ ልኳ ሆኖ የተፈጠረ ውስጧ ነው። ሁለመናዋ ነው። መልካም ዜናዋ ብሥራቱ ነው። ክፉ ዜናዋ ደግሞ ህመሙ ነው። ተስፋዋም ተስፋው!

  • ·         አውራ መሪዬ ሲል …

የሰባዕዊ መብት አውራ ተሟጋቹ የኔታ አቦንግ „ስንወለድ፤ ዘር፤ ጎሳ፤ ቋንቋ እና ሃይማኖት አልነበረነም“ የሚል ግሎባል ፍልስፍና ይዞ የተነሳ የዓለም አብሪ ኮከብ ነው። ሰውን ማዕከል ያደረገው አቋሙ ፈተና ቢበዛበትም ለኢትዮጵያ ጠ/ ሚርነት ሆነ ለመሪነት ከሚታጩት ጥቂት ብልህ ኢትዮጵውያን ውስጥ በህሊናችን ሰሌዳ ተመዝግቦ የተቀመጠ ምርጥ ሰው ነው። „ጥቁሩ ሰው“ የእኔም  የእርሰዎም፤ የሁላችንም ነው። በዶር. ኦባንግ ኢትዮጵያ ሜቶ ልቦና ውስጥ እንኳንስ እኛ ኢትዮጵውያኑ የሰው ልጆች በሙሉ፤ ተፈጥሮ ራሱ በእኩልነት አለን። ለዚህም ነው ዓለምአቀፍ ዕውቅናው ጉልህ እና ተደማጭ የሆነው።

በአስተሳብ ሳይለያይ ግን በአካሄድ ልዩነት በሁሉ ኢትጵያዊው የክብር ሰው ሲደርስ ሁላችንም የሚያስማማን ቁምንገር አለው። ይህም ብልህ ሰብዕናው ነው። ከሰይጣኖች በስተቀር፤ ለእሱ የምንሰጠው ፍቅርም ባለመበላለጥ የህሊና ነው። ሁላችንም  የእኛ ኦባንግ ነው የምንለው። የእዮባዊነት ሐዋርያው ነው የኔታ ኦባንግ። የታደለ ነው። ብዙ አድማጮች እና ደጋፊዎች አሉት። አሁን አድማጮቹንም፤ ደጋፊዎችንም የመሰረተውን ተቋሙንም ይዞ አብይ ኬኛ ብሏል! አብይ መሪዬ ነው ብሏል። መንፈሱ ራሱ ቅዱስ ስለሆነ አብሮት ከዚህ መንፈስ ጋር ያለው መንፈስ ቅዱስም አብይ ኬኛ ብሏል! ተመስገን!

  • ·         ን ስለምን ይህ የመልካምነት ሰብዕና በሽበር ክስ ተከሰሰ? እኮ ስለምን?

የሰው ልጆች ሁሉ አባትነት ከእናትነት ጋር በፍቅር ለማስተናገድ የፈቀደው „ጥቁሩ ሰውን“ ዶር ኦባንግ ኢትዮጵያ ሜቶን በወያኔ ሃርነት ትግረይ ሥርዕው መንግሥት „ወንጀለኛ ሽብርተኛ“ ተብሎ ተፈርዶበታል። ወያኔ ሃርነት ትግራይ አረመኔ እና ከሰውኛ ጋር በተጻራሪ የቆመ ስለሆነ። እንደ እሱም በሌሉበት ተሰደው እንኳን ሰላማቸው እንዲታወክ፤ ቤተሰብ እንዲሳቀቅ የሥነ  - ልቦና ጫና እንዲፈጠር ለማድረግ አሰቃቂ የፍርድ ውሳኔ በብዙ ወገኖቻችን ላይ ተላልፏል። በእስራት እና በሞት። ለዛውም ኢትዮጵያ በዓለም ታሪክ በአንድ ዜጋዋ ላይ ሁለት ጊዜ የሞት ጥቁር ፍርድ ስትሰጥ የመጀመሪያዋም የመጨረሻውም ሐገር ናት። በህሊና፤ በሃሳብ የተገደለን ሰው እንዴት ድጋሚ የሞት ፍርድ ይሰጠዋል። በመንፈስህ የገደልከውን ሰው እንዴት እንደ ገና ደግሞ ድርብ የሞት ፍርድ ትፈርድበታለህ? ከአውሬነትም የተለዬ አውሬነት ነው - ጭራቅነት።

በዚህ ውስጥ ነው አዲስ ትውልድ፤ ተተኪ ትውልድ የሚታሰበው። አሁን ሞት አባታቸው የተፈረደባቸው የአርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ ልጆች በምን ስሌት፤ በምን ሂሳብ ተረጋግተው ሊማሩ፤ ኢትዮጵያን የተስፋ ሐገሬ ሊሏት ይችላሉ? ልጆችም እኮ ተሰደው የተስፋ ሐገር ስደተኛ ናቸው። ሐገራቸው ኢትዮጵያ እንዴት ትናፍቃቸው? ፈጣሪ በፈጠረው ሰው ላይ እንዴት ፍትህ ያስከበራል የተባለው ዳኛ የሞት ፍርድ አንቀፃት፤ ድንጋጌ ጋር ለመስራት ይፈቀዳል? ራሱ ቃሉ „የሞት ፍርድ“ የሚለው ኢትዮጵያ ላላት ትልቅነት በፍጹም አይመጥናትም። ተስፋ አለኝ እንደሚፋቅ።

በሌሉበት የዕድሜ ልክ እስራት እና ሞት፤ ከሞትም ሁለት ጊዜ ሞት የተፈረደባቸው ወገኖቼ ከይቅርታ ጋር ፍርዱ እንደሚነሳላቸውም ተስፋ አደርጋለሁኝ በአብይ መንፈስ ውስጥ። ከተፈረደባቸው ጊዜ ጀምሮ ስደት ላይ ሆነው በሥነ - ልቦናቸው ፍርዱ ያደረሰው ጫና በቤተሰብ ሳይቀር እጅግ ረቂቅ በደል ነው። የመንፈስ ካሳ ያስፈልገዋል። እንግዲህ ይሄ የአዲሱ የአብይ ካቢኔ የቤት ሥራ ይሆናል። እኔም የምሥራቹን ለመስማት ተሰናድቼ ጆሮዬን ከፍቼ እጠብቃለሁኝ ግን እዮባዊነትን ሰንቄ።
  • ·         ፍቅርን የደፈረው የሰዋዊነት ሊሂቅ መሪ!


እንደ አቦ ለማ መግርሳ ደፋር የሰባዊነት መሪ፤ አውራ ተሟጋች የሆነው ዶር አቦንግ ኢትዮጵያ ሜቶ አዲሱ የኢትዮጵያ ጠ/ ሚር ዶር አብይ አህመድ መሪዬ፤ ጠ/ ሚኒስተሬ፤ ጀግናዬ በማለት በሙሉ ድፍረት እና ሰብዕና ገለጠ። ይገርማል! ይደንቃል! ይህ ዘመን ስንት የታሪክ አውራ ተግባራት እዬተፈጸመበት ነው። የእኛ ኦባንግ ሲታገልለት የነበረው ዓላማ በራሱ ጊዜ ፈጻሚ ሲያመጣ እንዲህ ነበር እንዲያ ነበር አላለም፤ እስኪ ልዬው፤ ልፈትሽው አላለም፤ በፐርስንት እንዲህ እንዲያ አላለም፤ ይህን ከፈጸመ ያን ካልፈጸመ አላለም፤ ቅድም ሁኔታ ለእሱ ስብዕና አልመጠነውም ሩቅ ነውና። ገና በ ዕለተ ቀኑ ፋታ ሰይሰጥ ሺ ሚሊዮን የቤተ ሥራ አልከመረም። የ100 ቀን መስፈሪያ ቁና አላሰፈለገውም፤ የወያኔ የደህንነት መዋቅሩ፤ የጸጥታ ሃይሉ፤ የኢኮኖሚ ተቋማቱ፤ ጠበንጃው ያሰራዋል፤ አያሰራውም አላለም፤ ንጹህ መንፈሱን ብቻ አምኖ በፈጣሪው ተማምኖ „ቃል“ ን የፈጠረው ፈጣሪ የቀባውን „መሪዬ“ አለ። „ቃልህን“ በሙሉ ልብ ተቀብለኩት አለ። „እንኳን መጣህልን“ „እንኳንም ደስ አለህ“  አለ። ይገርማል! ይደንቃል! ምን ይልቅ ይሄ ሰብዕና።  የጠራ እና የበቃ የዓለም ንጽህና እውቅና ያለው የአዲሰቱ ኢትጵያ ንቅናቄ መሥራች እና መሪ ሙሉ አብነት አለው። ይሄ ነው ኢትዮጵያዊነት። ትግሉ ለነፃነት ከሆነ፤ ትግሉ ሞት እንዲቆም ከሆነ፤ ትግሉ እስር እንዲቆም ከሆነ … ትግሉ ተስፋ ስዋዊነት እና ተፈጥሯዊነት ከሆነ፤

የቴሊቪዥን ፕሮግራሙ አልበቃ ብሎ በውጥረት ኦህዴድ ሲናጥ ከርሞ፤ ችግር በዬቀኑ ሲያመርቱ ተባጅቶ ለውጡን የበረከት ሴራ ሊቀለበስው ተሰናድቷል ክላስተሪንግ በጓሮ በር!” በዚህ ተደራጁ በዚህ ተወጣ ተወረደ ብሎ መረጃ መስጠት ጥሩ ነው ግን መቼ ከልብ ተደገፈ እና። ችግር አምራች የነበረው ሰብዕና ራሱን ይጠይቅ። ራሱ የአማራሩን አቅም ቢያገኘው ከርሸሌ ነበር የሚለቀው። ስለምን በምቀኝት እና በኢጎ መሪነት ሲታማስ ነበር የተከረመው። እና እኔ ሥርጉተ አይደንቀኝም። የተገኘን መልካም ነገር አክሮ ተጨማሪ አቅም መሆን ሲገባ ጦርነት ነው የታወጀበት በሁሉም አቅጣጫ። ለወያኔ ሃርነት ትግራይ በኢጎን ምቀኝንት ተወጥሮ አቅም ሲሸለም ተከርሞ „የሚጠበቀው እንየሆነ ነው“ ያለው ቢሉት „ወትሮ ነበር አንጂ ነው“ ለውጥ ተፈልጎ ለውጥ ተፈርቶ እኮ ነው የናንተው ነገር። ለለውጡ ተቆርቋሪ ሆኖ ለመውጣትም አንደበትም አይኖርም። አለማፈር ነው - ለእኔ። ለነገሩ ዛሬም አዲስ ዜና አለ። ማዕከላዊ እንደ ተዘጋ። ይህ እንግዲህ ለመርዶ አብቃዮች ሟርት ጋር በምን ሊታይ እንደሚችል እነሱ ተንታኞቹ፤ በታኞቹ ይሸንሽኑት …
በረዶ ተማምኖ ድርድር ላይ ከዝኖ የከረመው ሐገር ቤት ያለው የሰላማዊ ትግል መንፈስንም እያዬነው እዬሰመነው ነው። ያን የተቃጠለ ካርቦን ሴራ የአቶ በረከት ስምዖንን፤ የአቶ አስመላሽ ወልደሥላሴን ኤሎሂያዊ ትንፋሽ ተማምኖ ተጠልሎ ብጣቂ ክፍተት ባገኝ ብሎ ዓመት ሙሉ ሲሰበስ የከረመው የሰላሙ ታጋይ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሁለገብ አቅም ጎልብቶ ሲወጣ „ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም“ በማለት ሌላ ዙር የሰው ግብር ይመኛል፤ ያማትራል። በዬትኛውም ሁኔታ ይህ የለወጥ ዕድል ቢደናቀፍ፤ ሳይሳካ ቢቀር የወያኔ ሃርነት ትግራይ አቅም ችሎት ሳይሆን በውስጥም በውጭም በተፈጠረው  የሴራ ጥምጣም መሆኑን አምኖ ተቀበሎ ደግሞ ለሌላ የሰው ግብር መሰናዳት ነው። አቅም በላሹ እራሱ ነውና አቅሙን አሰባስቦ ደግም “ አረንጓዴ ፓርቲን፤ አንድ አማራን አጠናክሮ አገር አድኑን አጠናከሮ ደግሞ በራስ መንገድና አቅም መሞከር ነው“ ያለ ነገር ካለ። ራስን ማደራጀት በቃ! ያለው አማራጭ ያነ ነው። ከእሳት ተማግደው እስከዚህ ያደረሱትማ ሲብለጠሉ ቀንድና ጅራት ሲወጣላቸው ነው የተከረመው። በቅድመ ሁኔታ ድርድር ሲዋከቡ። ታዛቢ እኮ ህዝብ አለ። ሰው ምን ይለናልም እንበል … ማተብ የሚባል ነገርም አለ። ታዲያ ያ የበረከት ጋንታ ዝም ብሎ ሊቀመጥ ታስቦ ኗርልን? በሚገባ በቀጥታ ተደግፏል እኮ …

የሆነ ሆኖ የኔታ ኦባንግ አንተ ታሪካዊ ድርሻህን የቤት ሥራህን በሚገባ ተወጥተሃል። ቀሪው ሆነም አልሆነም በታሪክ ተጠያቂ አይደለህም። የተገኘውን የለውጥ መንፈስ ከጅምሩ ደግፈሃል፤ ተከታትየዋለሁኝ። አሁንም ከሁሉም በተለዬ መልክ መሪዬ ብለሃል። ዛሬ ስለምን እንደጻፍኩልህ ታውቃለህን? ላመሰግንህ ብዬ ነው። የማመስግነው ግን አንተ የተፈጠርክበትን፤ ሞት እንዳይነጥቀን የዳንክበትን ብሩክ ቀን ነው። አንተም ብሩክ ቅዱስ ሁን። ዘርህ ይለምልም! አሜን! ቅንነት ያለው ሰው ቢያንስ ለራሱ ሰላም የታደለ ነው።
  • ·         ኦባንግ ቅዱስ መንፈስ ጮራ የእስር እና የሞት ፍርድ ይነሳ!

ከመቼውም ጊዜ በላይ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በማንአለብኝነት ተነሳስቶ በዶር አቦንግ ኢትዮጵያ ሜቶ ንጹህ መንፈስ ላይ የሰጠው ወልጋዳ ብይን በራሱ የወያኔን ከንቱነት ሆድ እቃ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። አሁን ኦባንግ ምኑ ይከሰሳል? ዶር አባንግ መክሰስ ማለት እኮ ዶር. ምህረት ደበበን መክሰስ ማለት ነው። አቦንግ እንዲህ ነው - እውነትን ሲቀበል ማቄን ጨርቄን አላለም። ኦባንግ ያዘለው የተሸከመው ሌላ ዓላማ ምቀኝነት፤ ሸር፤ ደባ፤ ኮተት ወይንም ፍላጎት የለውም ከእምዬ የፍትህ ናፍቆት እና ሰውን ያከበረ፤ ተፈጥሮን ያነገሰ ሥርዓት ከመመኘት በስተቀር። የኔታ ኦባንግ የሁላችን የእኛችን ማልያችን ነው። ኦባንግ ቀለማችን የውስጣችን ነው። አቦንግ ልዩ ድምጻችን ነው። አባንግ ንጹህ ሰው ነው። አቦንግ ቅን ሰው! አቦንግ ፍቅር! አቦንግ ትህትና! ኦባንግ የመልካም ነገሮች ጳጳሳችን ነው! ልክ እንደ ዶር ምህረት ደበበ።

„ጥቁሩ ሰው“ የሚጠላው ጥላቻን፤ ዘረኝነትን፤ ምቀኝነትን፤ ጎሰኝነትን፤ ኢጎን፤ ኢ-ፍትሃዊነትን፤ አሉታዊነትን፤ ልዩነትን፤ ሴራን፤ ተንኮልን፤ ሸርን ነው። ኦቦንግ የሰዎች ተወካይ የመልካም መንፈሶች ተጠሪ ነው! በኦባንግ ውስጥ ያለው ቅዱስ መንፈስ የፈጣሪው ነው። ጥሪውም የፈጣሪው ነው። አቶ አቦንግ ሜቶ ትውልድ ከማይተካቸው ኢትጵውያን መከከል አንዱ ነው። በተለይ ከሶሻሊዝም ፍልስፍና በራቀ መልኩ የሰዋዊነት የተፈጥሯዊነት የሥርዓተ ትምህርት Cariculem ሐዋርያችን ነው። ኦባንግ ለአፍሪካም የቁርጥ ቀን ልጅ ነው። የኔታ አባንግ ለእኛ ስለ እኛ ብቻ ሳይሆን ስለመልካም ነገሮች የተፈጠረ ነው። አህጉራችን ዓለማችን ኢትዮጵያን የሚወክል ታላቅ ሰው ነው። የማያሳፍርን የማያሸማቅቀን ብሄራዊ ሰንደቃችን የሚያሰከበር ህሊናችን ነው። በዬትኛውም ሐገሩ በምትሰጠው አህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ የሃላፊነት ቦታ ሁሉ አንገታችን የማንደፋበት ታቦታችን ነው። ድልድይ መገናኛችን።

ይህ ታላቅ ኢትጵያዊ ለመላ ጥቁር ህዝቦች የፍቅራዊነት መለያችን ነው። ምልክት! እሱ ዛሬ መሪ መሆን እዬቻለ መሪም ሆኖ ግን ራሱን ዝቅ አድርጎ በትህትና የኢትዮጵያ አዲሱ ተስፋ ጠ/ሚር „የኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ አንባሳደር ዶር አብይ አህመድ መሪዬ ነው አለ። ለውጥ ፈላጊነቱን በተግባር አረጋገጠ። የለውጥ ባልተጠበቀ ሁኔታ መምጣት እንደ ሌሎቹ አለራደውም ወይንም ሌላ መንገድ ቀልባሽ መስመር ልክትል አላለም። ወይንም ለውጡን በህውከት አላጨናነቀውም። ይህን በፈቃዱ የተላከልን የምህረት ዕድል ልረብሽው አላለም፤ ሰላሙን እንጠብቅለት ነው ያለው። የተስፋን ቀን በጠምዝማዘነት፤ በዝንቅ ፍላጎት እና ተልኮው ግልጽ ባልሆነ ድፍርስ ስሜት ልረባብሸው አላለም። ነጥሮ ወጣ „የጥቁሩ ሰው“ ቅንነት - ደግነት - በጎ አሳቢነት። ይህ ሰው የዕድላችን ሚስጢር ገብቶታል። ይህ ሰው በርግጥም የኢትዮጵያን የሰላም እና የተስፋ ዘመን ሰንቆ ሲያንቀሳቀስ ስለመቆዬቱ ሌላ የምስክር ሰነድ አያስፈልገውም። ዶር. ኦባንግ ሜቶ ጥቁሩ ሰው ልዩ ቀናችን አድዮ አባባችን ነው። ቅዱስ የሖንሳችን። ለዬትኛውም አህጉራዊ ዓለምአቀፋዊ ኢትዮጵያዊ ተልዕኮ ብቃቱ ከንጽህናው ጋር ትውልድን ይገናባል። ያኮራል! የኔታ ኦባንግ የብሥራት ልዩ አቅማችን ነው።

የቅኔው ንጉሥ ብላቴው ጸጋዬ ገ/ መድህን „ፈራን ፈራን ፍቅርን ፈራን“ ያለውን ከማንም ቀድሞ እና ልቆ „ፍቅርን አለመፍራቱን በቃሉ አረጋገጠ። ቅንነትን አስቀደመ። አወንታዊነትን ምራኝ አለ። የብላቴው ታቦትም የመንፈስ ሥጦታውን ያከበርለታል በተግብሩ በቃሉ ነው።“ ዕውነትን የደፈረ ብቸኛው ታላቅ መሪ አባንግ ሜቶ! ኑረልን። እንኳንም የእኛ ሆነክ። አንተ የእኛ ባትሆን ይቆጨኝ ነበር። ይህ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ እና ለዘረጋው 27 ዓመት ሙሉ የአፋኝ ሥርዓት መንፈሱን ከሥረ መሠረቱ ለመንቀል የዕውነተኛ ሰዋዊነት ጠረን በተሰፋ ከሰማይ ሲታዘዝ የእኛ ኦባንግ እጆችን ዘርግቶ ተቀበለው። አፈቀረው። መንፈሱን አቀፈው። ወደደው፤ ተመኘው። ናፈቀው። ተመስገን! የተከሰሰበት „ሽብርተኝነት“ ትዝ አላለውም፤ በቅድመ ሁኔታም ነጥብ ይቆጠርልኝ አላለም። ወያኔ ሃርነትን የተሳሳተ ፍርድ ጸጥ ባለው በተከደነ የመሆን ብቃቱ አሳምሮ ቀጣው።

ነፃነት ፈላጊው ማህበረስብ ዳኝነቱ የህሊና ስለሆነ የኔታ ኦባንግ ለምን እና ለማን ሲታጋል እንደ ነበረ ዘመን ዕውነቱን የመብራት መስመር ዘረጋለት። ተመስገን!  ይሄው ጊዜ መልካምነትን፤ ቸርነትን አንጥሮ አበቀለ። ሰላም ፈላጊነቱም አፈለቀለት። ዕውነትና ፍቅር ከፍ አደረጋቸው ይህን ታላቅ ምርጥ ኢትዮጵያዊ። ተመስገን።

ወንድሜ ኦባንን የእኔታ ኦባንግ የእኛ ኦባንግ ንጹህ ሰው ነህ። እንዴትስ ቅን ነህ። የሰከነውን ለማደፈርስ በሚክለፈለው አዬር ወጀብ ውስጥ አንተን ያፈለቀ፤ ያቀረበ አምላክ የተመሰገነ ይሁን።

የማከብርህ ዶር ኦባንግ፤ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለእናትህ በክፉ ቀኗ ነው የተገኘህላት፤ አቅም ማዋጣት ነበረብህ አድርገኸዋል።  ኑርልን። አንተን ያተረፈ አምላክም የተመሰገነ ይሁን። አሜን። በተረፈ ደህና ሰንበት መልካም ጊዜ።

  • ·         ስብዕዊነቱ።

የእኛ ኦባንግ የአብይ መንፈስ ከምንጠብቀው ዴሞክራሲ በላይ ስለመሆኑን ሰዋዊነቱ በጥቂቱ ለጥፌዋለሁኝ። https://www.youtube.com/watch?v=8Z6HexcMHGU&t=31s

Ethiopia - Dr Abiy ከላይ ስትሆኑ በዛ መነጽር ብቻ ታች አትመልከቱ

Ethiopia - Dr Abiy ፈረንጆቹን አሸማቆ መለሳቸዉ!!

Ethiopia - Dr Abiy እንዴት ሰዉ 1% ልዩነት ይሰቃያል?!

Ethiopia : ጠቅላይ ሚንስትሩ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ጋር አድርገውት የነበረው ቆይታ

የሰራተኞች ቃለ ምልስ እና የሰራቶች
Ethiopia - ….ኢትዮጵያ ትበለጽጋለች! ትለወጣለች!
  • ·         ክወና!

ማንኛው ሰው „ከኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ መንፈሱ ጋር የልብ ሲገናኝ ውስጡ ያለው ስርክራኪ ሁሉ ይጸዳል። ይታጠባል። ሰው ይሆናል። ይህን እረብሻለሁኝ፤ እበጠብጣለሁኝ ካለ የሚጎዳውም የሚያደክመውም ራሱ ነው። ስለምን አዲስ አቅም ፈጥሮ እንደገና ከዜሮ ጀምሮ መታገል ግድ ስለሚለው። እድልን ማድመጥ ካልተቻለ በግራበ በቀኝ ሰቅዞ ይዞ ማጣደፉ የኪሳራዎች ሁሉ አለቃነት ነው። ስናይ የከረምነው ይኸውን ነው። ዕድልን መምራት ያልቻለ ስብዕና ቀድሞ ነገር የተስፋ መሪ ለመሆን አይችልም - ለእኔ። ተስፋን እንዴት አውክሃለሁ ይባላል? 43 ዓመት ተምጦ የተገኘ፤ እሳት ወስጥ በግራ በቀኝ የተጣደ ተስፋን ለማይታወቅ አጋጣሚ ይሸልም ተብሎ ብዙ ተሰርቶበታል። „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ የገጠመው ፈተና እንደ ሪሚጦ ነው። መጀመሪያ ከሚፈለገው ነገር ይጀመር። ራስ የለውጡ ተቀናቃኝ ተሁኖ የለውጥ አራማጅ ነኝ ማለት ይቀፋል በጣም ይሰቅጥጣል።
የኔዎቹ የማከብራችሁ ቅኖቹ ጸሎት ብዙ ነገር ይረታል፤ ያሸንፋል እና በጸሎት መትጋቱ ነው አቅምን ሃይልና ብርታት የሚሰጠው።
  • ·         ቶ ምንጭ ከጉግል።

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸነፎ የተፈጠረ ሚስጢር!
ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው ፍቅር ነው።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ። መሸቢያ ጊዜ።





አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።