ልጥፎች

ከጁን 19, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ባለ ተስፋዋ ኢትዮጵያ #እንኳን #ደስ #አለሽ። እማማ አፍሪካም። ዘለግ ሲል ግሎባሉም።

ምስል
          ባለ ተስፋዋ ኢትዮጵያ #እንኳን #ደስ #አለሽ ። እማማ አፍሪካም። ዘለግ ሲል ግሎባሉም። "የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፦ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።" (ምሳሌ ፲፮ ቁ ፱) ዛሬ ልጅ መሳይ በምስራች ነበር ዝግጅቱን አህዱ ያለው። ኢኮኖሚ ሳይንስነቱን ብቻ ሳይሆን ተፈጥሯዊነቱን የሚያስተምሩት #ርጉ የኢኮኖሚ ሊቀ - ሊቃውንት ፕሮፌሰር ተሾመ አበበ ዛሬ ከልጅ መሳይ ጋር ቃለ ምልልሳቸውን አህዱ ያሉት በብሥራት ዜና ነበር። ተመስገንም ብያለሁ። ሰበር ዜና ናላችን እረፍት ስላሳጣው። የሆነ ሆኖ የኢትዮጵያችን የደስታ ብቻ ሳይሆን #የሐሴትም ቀን ነው። ሐሴት ከደስታ የላቀ ነው። መንፈሳዊውን ዓለም እና ገህዱን አለም በተስፋ ያዋህዳልና። መንፈሱም ዘላቂ ነው። በውነቱ ብዙ ረኃብ አለብን። ጥማትም። #ሩቅ ነው ህልማችን፦ #ረቂቅ ነው ምኞታችንም። ተስፋችን አምላካችን አላኃችንም ነው። ሲጎድልብን እንዲህ ተስፋችን ቲፍ ያደርገዋል። በገኃድ አምላካችን አላሃችን መጽናኛ እንደላከልን አስብማለሁ። በብዙ ተጎድተናል። ለጋህዱ ዓለም ብቻችን ነን። መሪነት ቅንነት - ትጋት - #ሰወ #ወዳድነት - ማህበራዊነት - ቀለማዊነት - ህግ አክባሪነት- አድማጭነት ሁሉም ድል አድርገው ጥረቱም ስኬቱም የምሥራቹ ተጋሪ እንሆ አደረገን። የሊቀ ሊቃውንታት ጉባኤ #ብጡለ #ሊቅነት ። ተመስገን። እኔ ከዚህ በላይም እመኛለሁ። ከዚህ በላይም ተስፋ እጠብቃለሁ። ለኢትዮጵያ #አይዞሽም ነው። ውስጣችን ማስኖ እረፍት ላጣም ልዩ በረከት። ክብሮቼ እንዴት አደራችሁ። ዛሬ ሌሊት ምን እንደታዬኝ ባላውቅም ስለመሪነት ትንሽ ብዬ ነበር። ሲነጋም ይህን ዜና አገኜሁ። ይህ የኢትዮጵያ ሐሴት ብቻ ሳይሆን የአፍሪካም፤ የግሎባሉ አለምም ነው። #ሰው ...

እርስተኛው

  በመልካም ነገር ውስጥ አሰር የለም። እርካታ ነው እርስተኛው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19/06/2021

መልካምነት

 ሰው ሆነህ መፈጠርህ ሚስጢሩ መልካምነት ብቻ ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie

ሰባዕዊነት

  ሰባዕዊነት እራስን በቅጡ ከማስተዳደር ይነሳል። ያ ደግ ሰው እራሱን ማስተዳደር ከተሳነው ለተጎዱ ጠበቃ የመሆን አቅሙ ስንፍናው ይውጠዋል። ስለሆነም ደጎች ለራሳቸው ጊዜ ሊኖራቸው ይገባል። ሥርጉተ©ሥላሴ

ከተጎዱት ጎን

  ሰውነትህ ካልደረቀ ከተጎዱት ጎን ትቆማለህ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19/06/2021

ልጅ ያለው

 ልጅ ያለው ሰው ክፋ ሲሆን የእርግማኑን ልክ ታውቀዋለህ። የፈጠረን፣ ያስፈጠረ አምላክ መካዱ ሳጥናኤልነት ነውና። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19/06/2021

ውስጥህ

  ውስጥህ ሽሁራር ሲበላው ፀረ ሰው እና ፀረ ተፈጥሮ ትሆናለህ። እንዲህ እርቃን ሆኖ ከመኖር አለመፈጠር በስንት ጣዕሙ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19/06/2021

ባዕድ

  በሰወች መከራ የሚሳለቅ የባዕድ መንፈስ ምርኮኛ ነው። የአንተ አይደለም እና ዕውቅና ንፈገው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19/06/2021

ክፋት

 የክፋት ካብ እራስን ያሰምጣል። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19/06/2021

ፈቅደዋልና።

  ሴረኞች ሴራ የሚያበጁት በራሳቸውም ላይ ነው። የእዮርን እርግማን ፈቅደዋልና። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19/06/20

ሰላም

  ሰላምን ስትሰጥ ሰላም ትሆናለህ። ሰላምን ስትነሳ ሰላምህ ሸሽቶ ቀዥቃዣ ትሆናለህ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19/06/2021

ተፈጥሮ

  በወፎች ውብ ዜማ ተፈጥሮ ይከብራል፣ በክፋወች እንጉርጉሮ ተፈጥሮ ይቃጠላል። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19/06/2021

ቅንነት

 ከክፋት ሁሉ ስትርቅ የፈጣሪህ ቅንነትን ትወርሳለህ። ከክፋት ጋር ስትስተጋብር የሳጥናኤል ቤተኛ ትሆናለህ። ጨለማም ብርኃንም የመምረጥ መብቱ የአንተ ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie

ትሸበሸባለህ

  ኢትዮጵያን ስትክድ ትሸበሸባለህ፣ ስትዋሻት ታራለህ፣ ስትጠላት ትታወራለህ፣ ስትገፋት ትነኩታለህ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19/06/2021

እጭ

 ኢትዮጵያን ወደድኩ ብለህ ስትዳክር ፀጋ በረከቷ ህዝቧ መሆኑን ከካድክ አንተ አልተፈጠርክም። ጭንጋፍ ወይንም እጭ ላይ ነህ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie

ልቅና

 ስለ ኢትዮጵያዊነት ሲነሳ የሚያማችሁ ተፈጥሯዊነት የመነነባችሁ ናችሁ። ኢትዮጵያዊነት ዩንቨርስቲ ገብተው ሊማሩት የሚገባ የልቅና ልዕልና ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19/06/2021

መከራን ችሎ ማስቻልን የመገበ።

 ኢትዮጵያዊነት ጥልቅ ሚስጢሩን፣ ወርድ እና ቁመናውን፣ ርቃቄውን እና ከፍታውን መለካት አይቻልም። ኢትዮጵያዊነት ዩንቨርስ ነው። መከራን ችሎ ማስቻልን የመገበ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie

መሪነት #ኢንፖርት #ኤክስፖርት አይደለም።

 መሪነት #ኢንፖርት #ኤክስፖርት አይደለም። ሥርጉ024/06/19

#ለርጉወች

 መሪነት ጀምሮ #መጨረስን አብዝቶ ይጠይቃል። ጀምሮ መጨረስ ደግሞ የመቸኮል ባህሪ ላላቸው ሳይሆን #ለርጉወች የተሰጠ ነው። ሥርጉ024/06/19

#ቅብዓ እና #ክህሎት ይጠይቃል።

  #መሪነትን #ማለም ብቻ መሪ አያደርግም። ለመሪነት #እራስን #ማጨትም ፣ በሌላ #መታጨትም መሪ አያደርግም። #ቅብዓ እና #ክህሎት ይጠይቃል። ሥርጉ024/06/19

#የመረጋጋት

  መሪነት #ቁጭ ብሎ ማሰብን፣ ሰክኖ እራስን ማደራጀትን፣ ቁጭ ብሎ #ለመሥራት // #ለማሰራት መልመድን፣ የውስጥ #የመረጋጋት አቅምን እና አቅልን ይጠይቃል። ሥርጉ024/06/19

#ገላጭነት

 በመሪነት ውስጥ የተታይታ ግር ግር ሳይሆን የተግባርን #ገላጭነት ማስቀደም ይጠይቃል። ሥርጉ024/06/19

#የፌንጣ ፖለቲከኝነትን

  መሪነት #ለተጠያቂነት # #ቅርብነት #ለኃላፊነት #ብቁነትን ብቻ ሳይሆን #የፌንጣ ፖለቲከኝነትን መጠያፍ ይጠይቃል። ሥር ጉ02/06/19

#ከመሰጠት

 ሥም ብቻውን ለመሪነት አያበቃም። ሥመ ጥርነት መታደል ቢሆንም የመሪነት አቅም #ከቅባ ፣ ከልምድ፣ ከተመክሮ፣ #ከስክነት #ከማድመጥ ፣ ለመመራት ከመፍቀድ #ከመሰጠት #ከአፍላቂነትይ መነጫል። ሥርጉ024/06/19

#ቅጽበታዊነት

  #መሪነት #አቅም ብቻ ሳይሆን #አቅልም ይጠይቃል። #አቅል ማለት #አደብ ነው። #ቅጽበታዊነት ብዙ ነገር ያወድማል። ሥርጉትሻ024/06/19