ባለ ተስፋዋ ኢትዮጵያ #እንኳን #ደስ #አለሽ። እማማ አፍሪካም። ዘለግ ሲል ግሎባሉም።

  

 

May be a graphic of 1 person and text

 May be an image of 1 person

 

ባለ ተስፋዋ ኢትዮጵያ #እንኳን #ደስ #አለሽ። እማማ አፍሪካም። ዘለግ ሲል ግሎባሉም።
"የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፦
እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።"
(ምሳሌ ፲፮ ቁ ፱)
ዛሬ ልጅ መሳይ በምስራች ነበር ዝግጅቱን አህዱ ያለው። ኢኮኖሚ ሳይንስነቱን ብቻ ሳይሆን ተፈጥሯዊነቱን የሚያስተምሩት #ርጉ የኢኮኖሚ ሊቀ - ሊቃውንት ፕሮፌሰር ተሾመ አበበ ዛሬ ከልጅ መሳይ ጋር ቃለ ምልልሳቸውን አህዱ ያሉት በብሥራት ዜና ነበር። ተመስገንም ብያለሁ። ሰበር ዜና ናላችን እረፍት ስላሳጣው።
የሆነ ሆኖ የኢትዮጵያችን የደስታ ብቻ ሳይሆን #የሐሴትም ቀን ነው። ሐሴት ከደስታ የላቀ ነው። መንፈሳዊውን ዓለም እና ገህዱን አለም በተስፋ ያዋህዳልና። መንፈሱም ዘላቂ ነው። በውነቱ ብዙ ረኃብ አለብን። ጥማትም። #ሩቅ ነው ህልማችን፦ #ረቂቅ ነው ምኞታችንም። ተስፋችን አምላካችን አላኃችንም ነው። ሲጎድልብን እንዲህ ተስፋችን ቲፍ ያደርገዋል። በገኃድ አምላካችን አላሃችን መጽናኛ እንደላከልን አስብማለሁ። በብዙ ተጎድተናል። ለጋህዱ ዓለም ብቻችን ነን።
መሪነት ቅንነት - ትጋት - #ሰወ #ወዳድነት - ማህበራዊነት - ቀለማዊነት - ህግ አክባሪነት- አድማጭነት ሁሉም ድል አድርገው ጥረቱም ስኬቱም የምሥራቹ ተጋሪ እንሆ አደረገን። የሊቀ ሊቃውንታት ጉባኤ #ብጡለ #ሊቅነት። ተመስገን። እኔ ከዚህ በላይም እመኛለሁ። ከዚህ በላይም ተስፋ እጠብቃለሁ። ለኢትዮጵያ #አይዞሽም ነው። ውስጣችን ማስኖ እረፍት ላጣም ልዩ በረከት።
ክብሮቼ እንዴት አደራችሁ። ዛሬ ሌሊት ምን እንደታዬኝ ባላውቅም ስለመሪነት ትንሽ ብዬ ነበር። ሲነጋም ይህን ዜና አገኜሁ። ይህ የኢትዮጵያ ሐሴት ብቻ ሳይሆን የአፍሪካም፤ የግሎባሉ አለምም ነው። #ሰው #ወዳጅ #ሰው ማግኜት ለዘመናችን ቁልፋ ዕድል ነው። የሳበኝም ይህ ነው። ሰውነት ግሡ አናባቢው ተነባቢው የሆነ ሰብዕና ውድ ነው። የደከሙ ከርክመው ላሳደጉ ለፕሮፌሰር ተሾመ አበበ ቤተሰቦች እና ለድሉ ባለቤትም ለዶር ዳንኤል አበበም እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን። ልጅ መሳይ መኮነንም ተመስገን። ተባረክ።
የዶር ዳንኤል አባት ፕሮፌሰር ተሾመ አበበ "ዕድሉ መኖሩ ብቻ ሳይሆን #መዘጋጀትም።" ያስፈልጋል ብለዋል። ኃያል መርሆ ነው። ልጆችን ለምታሳድጉ ጥንቁቅ ወላጆች የሚረዳ መስመር ይመስለኛል። #ኢትዮጵያ #ባለተስፋ #ናት። ሚስጢሯን ያልደፋ ልጆች ስላሏት ዘራቸውን በዊዝደም እንዲህ #አስብለዋል። ተመስገን። ዛሬ ዕውነትም አንከር ሆነኃል። አንከር የሆነ መረጃ ነው። የሰጠኽው ዕውቅና እና ክብር መስጦኛል። ሰው የሚወድ ሰብዕና ህሊናዊነት ነውና። አዬህ አቶ ወንድም መሳዩ መኮነን የሰው ልጅ በእህል በውኃ ብቻ ነፍሱ አትቀጥልም እንዲህም ህሊናን የሚጠግኑ ፈዋሽ መረጃወችን ይጠይቃል። ጥበብም ነው። አይዟችሁም ነውና።
እናት የመጀመሪያዋ የህይወት ትምህርት ቤት ናት። እናት የመጀመሪያዋ የማህበራዊ ህይወት መምህርት ናት። እናት የደግነት የርህርህና የቅንነትም መምህርት ናት። ውድ እናትም ይህን የመሰለ ሥጦታ ታበረክታለች። እናት የመኖር ዘውድ ናት። እናት ለእናቷ ኢትዮጵያ የሰጠችው ፍሬ ዘር እንዲህ በሰው ወዳጅነት ልቅና የከበረ ከሆነ ልናመሰግናት ይገባል። ለሥነ ልቦና ባለሙያዋ ለዶር ዳንኤል አበበ ወላጅ እናትም የተለዬ ክብር አለኝ። ሥጦታው የራህብ መዳህኒት ተፈጥሯዊ ነውና። ተመስገን።
ይህን መሰል ተግባር ለሚፈጽሙ ወላጆች በሙሉ የወላጆች ቀን ኑሮን ብናመሰግናቸው ይጨመርልናል እንጂ አያጎልብንም። ከአባቶች፤ ከእናቶች ቀን ለዬት ያለ። ልጆችን ተረክበው በኃላፊነት ለሚያሳድጉ፤ የቤተሰብ ኃላፊነትን ወስደው ለሚያሳድጉ ታላላቅ እህትና ወንድሞች፤ አክስትና አጎቶችም የክብር ቀን ቢኖረን መልካም ይመስለኛል።
ዝርዝር መረጃውን ከአንከር ሚዲያ ታገኙታላችሁ። አጤ ጉጉልም ያኮመኩማችኋል። በቃለ ምልልሱ "ማደግማ #አረምም ያድጋል" የሚባል ብቻ ሳይሆን እኔ እማቀነቅነው የሥርዓት ለውጥም የውይይቱ መቋጫ ነበር። በመቋጫው እማክለው ኢትዮጵያ የሥርዓት ለውጥ ብቻ ሳይሆን የአስተሳሰብ ለውጥም ወሳኝ ጉዳይ ነው። በዚህ ዙሪያ ዩቱብ ቻናሌ ላይ የሠራሁትን ማድመጡ ሃሳቡን ያጠናክረዋል። በሌላ በኩል መሠረታዊ ጉዳዮች ስለተነሱ ብታደምጡት ትማሩበታላችሁ።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። የእኔ ውዶች ደህና ዋሉ፤ ደህና አምሹልግኝ። ቸር እናስብ ቅንነት ይምራን አሜን።
Daniel Abebe, JD, PhD | Spirit of Maryville 2019
Daniel Abebe has been appointed the next dean of
@ColumbiaLawSchool
“ effective August 1, 2024.An impressive and experienced academic leader, Abebe will join the Law School from the University of Chicago, where he has served as vice provost for academic affairs and governance since 2018.Read the announcement: president.columbia.edu/news…»
ሥርጉተ@ሥላሴ
Sergute@Selassie
19/06/024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

 

 

 

 

ይገርማል እራስን ለማዬት አለመፍቀድ። ስለ ፕሬዚዳንት ኦባማ ዓለም እንደምን ተደመመ? ያ አቅም የእኛ ሲሆን ግን መርግ ነው። አዚም ተደርጎብናል። ከውስጤ ነው እማዝነውም። የሁሉም ነገር ራህብተኞች ነን። ውስጣችን ስናገኝ እንኳን ለማቅረብ የማንፈቅድ። ሐሴቱ ውስጣችን እንዳይገባ የምንገፋ። እና አማኑኤል እንደምን በቃችሁ ይበለን። ወደ ቀጠሮዬ ስሄድ እዬሳቅኩ ነበር። ደስ ብሎኝም። ተመስገን አንድ የቤታችን አባል ሼር አድርገውታል። ይህ ዜና ከተጽዕኖ ፈጣሪወ ፎቶ አንሶ ይሆን። እግዚአብሄር ያከበረው መንፈስ ቅባውን በልቅና ይከበክበዋል። ሚሊዮኖችም ሰው ወዳጅን ይቀበላሉ። ተመስገን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።