ሰባዕዊነት አገናኝ አግኝ ፌስቡክ X Pinterest ኢሜይል ሌሎች መተግበሪያዎች - ጁን 19, 2024 ሰባዕዊነት እራስን በቅጡ ከማስተዳደር ይነሳል። ያ ደግ ሰው እራሱን ማስተዳደር ከተሳነው ለተጎዱ ጠበቃ የመሆን አቅሙ ስንፍናው ይውጠዋል። ስለሆነም ደጎች ለራሳቸው ጊዜ ሊኖራቸው ይገባል። ሥርጉተ©ሥላሴ አገናኝ አግኝ ፌስቡክ X Pinterest ኢሜይል ሌሎች መተግበሪያዎች አስተያየቶች
ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም። - ዲሴምበር 16, 2019 ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም። ከዚያ የከበደ መከራ ላይ ናቸው አላዛሯ ኢትዮጵያም ሆነ እማማ አፍሪካም። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱) ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። · እፍታ። ጤናይስጥልኝ የአገሬ ቅኖች እና ቅኔዎች። እንደምን አላችሁ? ለረጅም ጊዜ ጠፋሁኝ - በምክንያት። እርግጥ ነው እሰከ ሚያዚያ ወር መጨረሻ በቀንበጥ ብሎጌ እጽፍ ነበር። ከዛ ደግሞ ቀንበጥ ብሎጌ ለተወሰነ ጊዜ መሰተጓጎል ቢገጥመውም ፌስ ቡክ ላይ ብዙ አድካሚ ያልሆኑ ግን በውስጤ እማምንበት አጫጭር ጹሁፎችን ስጽፍ ቆይቻለሁኝ። ዕይታዬ ያመለጣችሁ ይኽውና ሊንኩ። https://www.facebook.com/pages/category/Personal-Website/Httpfbmecg-1591546727802213/ በዚህ ሁሉ ሁኔታ ግን የድምጽ አልባዎችን የኢትዮጵያ ዕናቶች ዕንባ በፈቃድ ውክልና ለሚያደምጡኝ ደጋጎች መላኬን አላቆምኩኝ። አሁን ታስህሳስ ወር ነው በዚህ ወር ላይ ሰሚ የለም ክርስሚያስ ጥድፊያ ላይ ስለሆኑ ነጮቹ። ስለዚህ ታህሳስ እና ጥር አጋማሽ ረፍት ይሆናል ማለት ነው። አዲሱ ጉዳይ የማይድኑ ሃሳቦች ላይ ጊዜ ማጥፋት ትቼያለሁ። አቁሜያለሁኝ። የማይድኑ ሚዲያዎችንም አላዳምጥም። ስለዚህ ሙግቱ ቀንሷል ማለት ነው። ሌላ በልቤ ሙዳይ የነበሩ ወገኖቼ ሲያዛልጣቸው ባይም ልወቅሳቸው ግን አልደፈርኩኝም። ስለምን? መብታቸው ስለሆነ። እርግጥ ነው በልቤ ያላቸውን ቦታ እንዳያጡ ባላዳምጣቸው ስለሚሻል አቅሜን ቆጥበውልኛል። እንዳከበር... ተጨማሪ ያንብቡ
እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች። - ጃንዋሪ 06, 2021 እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል። እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል። ምሳሌ 16 ቁጥር 9“ እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች። ለእኔ ሰማዓት ናት አጊቱ! ጀግናዬም! „A cheese making business in the Alps is the project of Ethiopian entrepreneur, Agitu Ideo Gudeta. Forced to flee Ethiopia, she has built a new life in Italy.“ · እፍታ። የተወሰናችሁት እንደሚቆርጣችሁ፤ እንደሚፈልጣችሁ፤ እንደሚጨንቃችሁ፤ እንደሚያናዳችሁ አውቃለሁኝ ይህ መጣጥፌ። ዛር ካለም ጉሬያ ይፈቀዳል። በፓን አፍሪካኒስቱ ብላቴ ጌታ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን መታሰቢያ ድህረ ገፅ፤ የራዲዮ ፕሮግራም ምስረታ እና ዝግጅት ስጀምረው እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ በጣም ብዙ ተዘርዝሮ የማያልቅ መከራን ተቀብዬበታለሁኝ። እዬተቀበልኩበትም ነው። በዬትኛውም ሁኔታ ታግቻለሁኝ። የእኔን ሥም መጥራት እኔን ማድነቅ ማመስገን ውግዝ ከአርዮስ ነው። ተዘርዣለሁኝ። ሥሜ ጠፍቷል። ተወግዣለሁኝ። ሁሉንም መከራ ፈቅጄ እና ወድጄ አስተናግደዋለሁኝ። ወደፊትም። ዕምነቴ ዕውነት እና መርህ ነው። መንገዴ ተፈጥሯዊነት፤ ሰዋዊነት፤ እኛነት ነው። ከዚህ ፈቅ የለም። የራሴ ጌታ እራሴ፤ የራሴ እንደራሴ እኔው እራሴ ነኝ። እኔ „እኔን“ መሆን ከተሳነው እኔ „እኔን“ ያሰነባተዋል። ይህ ደግሞ አይፈቀድለትም። ዛሬ እንዲህ ልትክደን በወት ብርቱካን ሚዲቅሳም ዕወቅና ላይ በመትጋቴ እንዲሁ አሳሬን በልቸበታለሁኝ። በብላቴውም፤ ... ተጨማሪ ያንብቡ
የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ? - ፌብሩዋሪ 03, 2021 እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጣችሁልኝ። „አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኽኝ? እኔን ከማዳን ከጩኽቴ ቃል ሩቅ ነህ። አምላኬ በቀን ወደ አንተ እጣራለሁ አልመለስህልኝም፤ በሌሊት እንኳን እረፍት የለኝም።“ (መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 21 ከቁጥር 1 እስከ 3) ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 03.02.2021 · የ እኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ? አላዛሯ ኢትዮጵያ እና ልጆቿ እንዴት እዬሆኑ ይሆን አዋዋሉ አስተዳደሩ?? እንደምን እዬሆንሽ ነው እማ! የእኔ ልዕልተይ! እናንተስ ማህበረ ንጹኃና ቅኖቹ የብራናዬ ታዳሜዎች እንዴት ናችሁ? ስለጤንነታችሁ፤ ስለሰላማችሁ አስባለሁኝ። እናንተ ለእኔ የህሊናዬ ቤተ - መቅደሶች ናችሁ እና። ይህን ስላችሁ ከንቱ ውዳሴ ይመስላችሁ ይሆናል። እመኑኝ ብዬ አልሞግትም። ጥሞና ላለው ሰብዕና እኔን እኔ አድርገው የሚመሩኝ የህይወት መርሆቼን አቤቱ ጉግል፤ ፊታውራሪ ዩቱብ ቢጠዬቅ ይመልስዋል። ዛሬ መስካሪ አለን። ትናንት ምን ዛሬ ምን እንደሆን። በልጅነት የሚያውቁኝም በዛው ልክ ስለመሆኔ ያውቃሉ። እራሴን አታልዬ ለመኖር አልተፈጠርኩበትም። እምጽፈው እራሴ የሆንኩትን ነው። እኔ እኔን መሆን ከተሳነው እኔ ለእኔ በተሰጠው የነፃነት ልክ መቆም ካልቻለ እኔ እኔን ማሰናበት ይኖርበታል። ይህ ደግሞ አይፈቀድለትም። ይህ መርሄ ነው። · ው ሃማ ባለቀለሙ ሃሳብ? ሃሳብ ሰላም ይሻል። ሃሳብ ፍቅር ይሻል። ሃሳብ አትኩሮት ይሻል። ሃሳብ እንክብካቤ ይሻል። ሃሳብ ሰው ይሻል። ሙሉሰው። ምራቁን የዋጠ። ስለዚህም ጊዜ መስጠት - ማድመጥ - አክብሮ ማወያዬት - ማሰከን ያስፈልጋል። ማንን? የንጉሶች ንጉሥን አጤ ሃሳብን። ሃሳብ አ... ተጨማሪ ያንብቡ
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ