እናት ስትታሰር የትውልድ ተስፋ ይጠነዝላል።
እናት ስትታሰር የትውልድ ተስፋ ይጠነዝላል። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ጤና ይስጥልኝ ማህበረ ቅንነት። እንዴት ሰነበታችሁ? በብዙ ያልሰከኑ፤ ያልተገሩ፤ የሚወራጩ ሁነቶች ውስጥ ዝምታ የተሻለ በመሆኑ ዝምታ ቆምሶ ሰነበተ። ከውስጤ ሊወጣ ያልቻለውን የቤተሰብ ምስል በሚመለከት ትንሽ ልጽፍበት ወደድሁኝ። ፎቶዋን ከፌስቡኬ https://www.facebook.com/sergute.selassie/ #እናት ናት። #ትጉህ ፀሐፊ ናት። #ሞጋች ናት። #መምህርት ናት። ሚስትም ናት። #ፖለቲከኛም ናት። #ቁምነገርም ናት መስኪ። #ወጣቷ ፖለቲከኛ በሳልም ናት። መስኪ እና ብዕሯን ከ2014 ጀምሮ እኔም እሷም የደጉ ዘሃበሻ፦ የደጉ ሳተናው #አምደኛ ሆነን አውቃታለሁኝ። እኔ እንዲያውም አገር ቤት ሆና እንዲህ ትሞግታለች ብዬ አላስብም ነበር። በውነቱ ውጪ የምትኖር ነበር የሚመስለኝ። አንድ ጊዜ አመስግኜ ኢሜል ፃፍኩላት። መልስም ሰጠችኝ። መስኪ ባለትዳር እና የልጆች እናት መሆኗን ግን በጣም ዘግይቼ ነው የተረዳሁት። ምክንያቱም እኔ ከ2019 በፊት የፌቡ ተጠቃሚ ባለመሆኔ ለብዙ መረጃወች ቅርብ አልነበርኩምና። የሆነ ሆኖ መስኪ እንዲህ #ተደፍሮ ለካቴና ልትሰጥ የሚገባ ወጣት ፖለቲከኛ አልነበረችም። ልንሳሳላት የሚገባ ልዩ ወጣት ናት እና። እንዲሁም ለገዢውም ሆነ፤ ለተፎካካሪ፤ ለተጠማኝ፤ ለተደማሪ፤ ለተቀላች፤ ለተለጣፊ፤ ወይንም ለተደማሪ ለዬትኛውም ፖለቲከኛ የምትሰጠው ጉልበታም አስተያዬት ህዝብ ጠቀም በመሆኑ ይረዳዋል፤ የአቅጣጫ አመላካች ነውና። መስኪ ለግፋፎ ጭዳ ጭድ ክምር ግርግር አልተፈጠረችም። ለምታምንበት ቁም ነገር ጽኑ እና ዕውነት አፈላላጊ ናት። ጹሁፎቿን በትጋት አነባለሁኝ። ...