አሸባሪው ማን ነው? አቶ አባይ ወልዱ ወይንስ ዬአማራ ተጋድሎ አክቲቢስት ወጣት ንግስት ይርጋ? ከሥርጉተ ሥላሴ 21.01.2017 (ዙሪክ - ሲዊዘርላንድ)
• ዬአማራ ተጋድሎ ሲነሳ ዬፃፍኩት ነው። ዛሬ 09.04.2023 አመት ድገም እያለን ነው። • አሸባሪው ማን ነው? አቶ አባይ ወልዱ ወይንስ ዬአማራ ተጋድሎ አክቲቢስት ወጣት ንግስት ይርጋ? ከሥርጉተ ሥላሴ 21.01.2017 (ዙሪክ - ሲዊዘርላንድ) „እንደ ጠቢብ ዬሆነ ሰው ማነው? ነገርንስ ዬሚያውቀው ማነው?" (መጸሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፰ ቁጥር ፩) ይድረስ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ መሪዎች። ትግራይና አዲስ አበባ። • እፍታ። ያለለት ሃቅ - ትነጥራለች። ያለለትም ውንብድና - ይቆማል። ያለለት ዬምድር ዕንባ ለፍሬ - ይበቃል። ያለለት ዬአፓርታይድ ግዛት መቃብር - ይበላዋል። ያለለት ጥጋበኞች ዬማዕት አውሎ - ይውጣቸዋል። ያለለት ዬዕንባ ቤተኞች መከራቸው መከውኑን ምክንያት አድርገው አምላካቸው ስላደረገላቸው መልካም ነገር ሁሉ በተመስጦና በቀስታ ያመሰግናሉ። ይህ ከምድራውያን ዬሚጠበቅ ዬራፊ ጸጋ ሳይሆን ዬዕንባ አድማጭ ከሆነው ከፈጣሪ ደጅ ብቻ ዬሚታፈስ፤ በውለታና በጉቦ ዬማይደፈር ሰማያዊ በረከት ነው። በሰው እጅ በመቁንን ተለክቶ በአድሎ - ዬማይደለደል። መክሊት። እራሷን ለበላህሰቦች ዬማገደች ወጣት ናት። አዎን በአማረነቷ ዬሚደርሰው በደል ልኩን ስላለፈ - ፊት - ለፊት ወጥታ ዬወያኔ ሃርነት ትግራይን ማንፌስቶ አንጎል ዬሞገተች ድንቅ ፍሬ ናት። ዬአማራ ጉዳት ዬማይሰማው አካል በግማሽ ግድግዳ ቤትን እንደ መገንባት ስለማሰብ በመሆኑ፤ ሙሉ አቋም ላይ ዬሚገኝ ዬጋራ ቤት እንዲኖረን ዬራሷን ዬቤትሥራ ዬተገበረች ዕንቁ ናት። ዬአማራ መከራ እንደ አልባሌ ማበሻ ጨርቅ ካልተወረወረ … ብሄራዊ ጀግናችን ናት። እንደ ህዝባዊና ሙያ ማህበራት አደራጅነቴ ደግሞ ዓይኔ ናት! ብርቄ ናት! ናፍቆቴ ናት! መሪዬ ናት! • ምልክት። ለወያኔ ሃርነት መሳፍንት...