#አንሰበርም! ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 06/04/2023 #ቫወል አንሰበርም!
ለሰማእታቱ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት እና ቤተሰቦች ከልብ ዬተሰማኝን ሃዘን እገውፃለሁኝ።
ከፋሽስታዊው ሥርአት የሚጠበቅ ነው። በህግ እና በሥርዓት ተፋልመን ደረጃውን ልኩን አውቆ እንዲራመድ ለማድረግ የሚገባነን እንሠራለን። እናደርጋለንም። ኢትዮጵያ ያላችሁ ወገኖቻችን ዞር ማለትን ልመዱ። በርደኑን እኛ እንሸከማለን።
ሚዲያ ላይ ያላችሁ ደግሞ እርእሱን ተራጋጭ አታድርጉት፤ መፃፊያ ቀለሙን አታንቀልቅሉት። ዬአማራ ልዩ ኃይል ከመንግሥት አፈነገጠ ይላል የኢትዮ 251 ሚዲያ። ማንን ይጠቅማል ምንስ ያተርፋል? ቀለሙ ቢጫ ነው ጥሩ ነው። በምንም ሁኔታ ቀይ ቀለም አያተርፍም።
ሰማያዊ ቢጫ መጠቀም ይበጃል። አረንጓዴም ሸጋ ነው።
ወጣትነት ከጨካ ሥርዓትን እፋለማለሁ ሲሆን ከባድ ነው። ወጣቶች ወንጀል ቢሆንብኝም ወጣትነታችሁን ተላለፋት። እንደ ዕድሜ ሙሉ ሰው ሁኑ። ሁላችንም ጠብ ለማይል ትግል ወጣትነታችን ተላልፈን ከዚህ ተደርሷል። ቀን አያልቅም። እና ነገን ታዩ ዘንድ በእርጋታ እና በስክነን ታገሉ፤ አታግሉ። መኖር ሁሉን ይሰጣል። ማለፍ ደግሞ መፈጠርን ያጠናቅቃል። ከጎናችሁ ነኝ። አይዟችሁ።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
06/04/2023
#ቫወል አንሰበርም!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ