በመኖር እና በመሞት መካከል ያለው ልዩነት የመተንፈስ ይሆናል። ማስተዋል ያለብን #እዬተነፈሰም #ተገድሎ #የሚኖር ህዝብ ሊኖር እንደሚችል ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ

 በመኖር ውስጥ ያለ መከራ ቃልህን ጦርነት ከፍተህ ስታወድመው ይሆናል።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/04/2022 

ብትን አፈር ያጣ ህዝብ እና መተንፈሻ ያለው ህዝብ እኩል ሊታይ አይገባም። የአፋር እና የአማራ መከራ ከሁሉም የበረታ፣ የከፋ ነው። አያያዙም አስተዳደሩም ብልህነትን ይጠይቃል።
ሥርጉተ©ሥላሴ

 በሞቅታ፣ በለብታ፣ በግርግር፣ በሁካታ፣ በአፍላ፣ በግንፍልፍ ፖለቲካ አገር ፀኖቶ አያውቅም። አገር በዕውነት፣ በተፈጥሮ ማስተዋል እና ትጋት ብቻ ይፀናል።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie

 ባለቤት ለሌለው ህዝብ ባለቤት ይሰጠው ዘንድ መፀለይ #ትርፍ ሥራችን ሳይሆን #መደበኛ ተግባራችን ሊሆን ይገባል፣ በተለይ አቅም ያላቸው አቨው ሱባዬ
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie

 09/04/2022

 የጭንቅ ዘመን የሰጠው ህዝብ ቢያንስ የመቻል ፀጋውን ማዘረፍ አይኖርበትም።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/04/2022

 

በመኖር እና በመሞት መካከል ያለው ልዩነት የመተንፈስ ይሆናል። ማስተዋል ያለብን #እዬተነፈሰም #ተገድሎ #የሚኖር ህዝብ ሊኖር እንደሚችል ነው።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/04/2022

 የፈጣሪ ታምር ኢትዮጵያን አይረሳትም ብዬ አምናለሁ። በተለይ እሷን የመሰጠሩ ጠፍተውም አይጠፋም፣ ደክመውም አይደክሙም። ከመልካም ቀን ጋር መገናኜታቸውም አይቀሬ ይሆናል።
ሥርጉተ©ሥላሴ

 በዚህ ዘመን ያዬሁት የጽናት ተቋም የአማራ እና የአፋር ህዝብ የሰጡን #የፅናት #ሽልማትን ነው። ተመስገን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/04/2022

 

 የአማራ እና የአፋር ህዝብ መከዳት ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ ጽናትን በዕውን እናይ፣ እንማርበትም ዘንድ ፈጣሪ አላህ ፈቀደልን። ተመስገን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/04/2022


 እኔ የማንም አይደለሁም። የድምፅ አልባው ዕንባ ግን ነኝ። ድርጅት ከተባለ ዕንባዬ ነው ተቋሜ። እና ፀጋዬ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/04/2022

 

 ዕውነት መሆን፣ መርኽ መከተል ህይወት ነው። ስትደክሙ የሚያጽናና፣ ስትዝሉ አይዟችሁ የሚል። ቀን አይቶ የማይሸሽ፣ ዘመን አይቶ የማይገፈትር።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/04/2022

 

 ወረት እና የህልውና ተጋድሎ አይገናኙም። ኪዳን እና ቃል አባይነትም እንዲሁ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/04/2022

 መኖርህን በወረት ከጠቀለልከው አንተ ሬድሜድ ወይንም አርቲፊሻል ይሆናል መኖርህ። በዬትኛውም ግንኙነት መኖርን ለማኖር #ጊዜያዊነት ከሰውነት በታች ነው። አንገት አልባ ስለሚሆን።
ሥርጉተ©ሥላሴ

 

 

የዝምተ ቀለም ተቋምነት።
በሦስት ዓመት ውስጥ በፌስቡክ ቤተኝነቴ ጥቂት ሰው ነው እማውቀው በጽናታዊ ሥነ ምግባር። ዛሬ ስለ አብርኃሙ የዝምታ ቀለም ትንሽ ልበል። በዝምታቸው ውስጥ ወጀብ የማያናውፀው ጽናት። ወረት የለም።
ዛሬ ሰው ነገ ሌላ አይሆኑም። እንዲህ ዓይነት ሰብዕናን ነው ቀጣዩ ትውልድ ሊኖረው የሚገባ። ሼር፣ ላይክ የሚያደርጉትን ሳይ ይገርመኛል።
ሁሉንም ሼር ላይክ አያደርጉም። መጥነው ነው። ጽናታቸውን ወጀብ ነክቶት አያውቅም። ሲሞቅ አይፈሉም፣ ሲበርድም አይቀዘቅዙም።
በተመጠነ ሙቀት እንደ ተፈጥሮው በስክነት መኖርን፣ የነፃነት ተጋድሎን ይመሩታል። ያስተዳድሩታል። ሁሉንም ዕውቅና ሰጥተው በአትኩሮት ይከታተሉታል።
ትውልድ በዚህ መሰል ሰብዕና የመገንባት አቅም ሊያድግ ይገባል ባይ ነኝ። የኛው ዘመን ብክነት ላይበቃ የዛሬውንም እያባከነው ነው። ተግ እንበል። እባካችሁን።
ፌስቡክ ላይ ብዙ መማር ይቻላል። ብዙ ማዬትም። ሰብዕና ጨዋነቱን ታዩበታላችሁ። ትመዝኑበታላችሁም።
ትናንት ተፃፍኩት በዓለም ዓቀፍ የእግር ኳስ ዳኛው በአቶ በአምላክ ያዬሁት የኢትዮጵያዊነት ፀደይ ሰብዕና እኔ በአቶ ሠለሞን ኃይሌም ሦስት ዓመት ሙሉ ታዝቤያለሁ።
አይናገሩም ወይንም አይጽፋም ግን በዝምታ ህብራዊ የተጋድሎ አርታቸው እደመማለሁኝ። እጽናናለሁም። ተመስገን እላለሁኝ። ማጣትን ስለሚቋቋም ሰብዕናቸው።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/04/2022
 
 


ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ናት። ውራጅም ጉርድም አይደለችም።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/04/2022

 ኢትዮጵያ የትውስት አይደለችም። የተፈጥሮ ፀጋ እንጂ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/04/2022

 ኢትዮጵያ በሞግዚት አስተዳደር ተመርታ አታውቅም። በራሷ #የዊዝደም አቅም እንጂ። ዛሬ ይህ እዬተጣሰ ነው። ወደ ክብር ባአፋጣኝ መመለስ ግድ ይላል።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/04/2022

 

 

ህግን ጥሶ ህጋዊነት የለም። የሰናፍጭ ታክል ህግ ከተጣሰ በዛ ውስጥ ኢትዮጵያዊነት የለም። አይኖርም። የሚኖረው አናርኪዝም ነው። ያ ደግሞ ወረርሽኝ ነው። አገርን፣ ትውልድን አደራን ያፈርሳል። እንጠንቀቅ።
ህግ ጣሾችን ለመታገል ህግ በመጣስ ፍትህ አይሰፍንም። ቀድሞ ነገር ህግ ጥሰት ፋክክር ውስጥ ከገባ የእርግማን ይሆናል። መርገምት።
ትውልድ በህግ ጥሰት መቅረጽ አገርን ውል አልባ መና ማስቀረት ነው።
"ህግ ተላላፊወችን ጠላሁ" ይላል የልብ አምላክ ዳዊት ምስባህክ። ህግነት የፈለጉትን በልኩ ለማግኜት መንገድ ነው። ጥሰት ለውድቀት ይዳርጋል። ጥሰት መታበይም ነው። ጥሰት ሽሚያም ነው። ሽሚያ ደግሞ የሳሙና አረፋ ነው። ኮፈፍ ብሎ ረብ ይላል። ረብታው ምራቅ።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/04/2022
 
 
 በክፋነት ውስጥ የቁም ሙትነት አለ። #አትተባበሩት። ሙት ይዞ ይሞታል እና።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/04/2022
 
 
 ክፋነት ማራኪ አይደለም። ፋንጋ፣ መልከ ጥፋ፣ ፅልመታዊ፣ መርዶ ነው። ተጠዬፋት።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/04/2022
 
 

 በቀል ለፋክክር የማይበቃ ገደል ነው። ስለዚህም ለገደል ፋክክሩ ይቁም። አብሮ መከስከስ አለና።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/04/2022

 

 የፍቅር ተፈጥሮ ዝልቅ ነው። አይበርደው አይሞቀው ምጥን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/04/2022

 

 

    ኢትዮጵያዊነት #ትርፊ #ቅርጥምጣሚ ማንነት አይደለም።
    ኢትዮጵያዊነትን ሰው ስለመጣ እና ስለሄደ፣ ስለተሾመ እና ከሥልጣን ስለወረደ ሳይሆን ዕውነት ሆኖ ዕውነትን ስለሚያዘልቅ በተፈጠረበት ማንነቱ እራሱን አስችለህ ውደደው።
    ኢትዮጵያዊነትን ለሰው ብለህ የምትወደው፣ ለሰው ብለህ የምትጠላው ጨርቅ ወይንም የድግሥ ኢቬንት አይደለም። ለዚህ ነው እኔ አዘውትሬ ኢትዮጵያዊነት ለሁላችንም ከብዶናል የምለው።
    ዕውነትን የካድክ ዕለት
    በመርህ የሸፈትክ ዕለት
    ቃልህን የሸሸህ ዕለት
    በፌክ ዳንኪራ ባልስ የዳነስክ ዕለት በውስጡ ሾልከኃል። በኢትዮጵያዊነት ውስጥ ስትኖርበት ጥንቁቅ፣ ቁጥብ፣ እራስህን የገዛህ ስታጠፋ ቀድመህ እራስህን የምትገስጽ ብርቱ ትሆናለህ።
    ኢትዮጵያዊነት ብርታት ነው።
    ኢትዮጵያዊነት ጥንካሬ ነው።
    ኢትዮጵያዊነት ጽናት ነው።
    ኢትዮጵያዊነት አናባቢም ተነባቢነትም ነው።
    በግል ህይወትህ፣ በማህበራዊ ህይወትህ፣ በሃይማኖታዊ ጉዞህ ሁሉ እሱን እና ዶግማውን ከታጠቅ ማን እንደ አንተ ጌታ።
    ዕውነቱ ኢትዮጵያዊነት ትርፍራፊ አይደለም። ኢትዮጵያዊነት ተክለ ቁመናው እራሱን ችሎ የተፈጠረ፣ በሙሉ አቅም በተቀደሰ ዕለት የተባረከ ምሩቅ ማንነት ነው።
    እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
    ሥርጉተ©ሥላሴ
    Sergute©Selassie
    09/04/2022


  • Woubie Denekew Mekonnen
    አዎ ኢትዮፕያውይነት ሁሉም መልካም ነገሮች በውስጡ የታመቁበት ለአለም ህሉ በጎ የሚያስብ፣ በክፉ የሚመጡበትን እንደ አመጠጠቸው የሚመልስ የተከበረና የተወደደ ማንነት ነው!!!
     
     
     
    ኢትዮጵያዊነት #የጡንቻ ማንነት አይደለም።
    ኢትዮጵያ በታሪኳ የማንንም ደንበር ተጋፍታ፣ ጥሳ ተከሳ አታውቅም። ፈፅሞ። ኢትዮጵያ እራሷ ፍልስፍናም፣ ሳይንስም፣ ዩንቨርስም፣ አስተምህሮም ዶግማ ናት።
    ኢትዮጵያ ዊዝደም ናት። ለዚህ ነው ኢትዮጵያ ላይ የሚፈጠሩ ክስተቶች ሁሉ ዓለም በሙሉ አቅሙ እንዲታደም የሚገደድበት።
    ኢትዮጵያ የስልት፣ የመሆን፣ የቃልኪዳን አገር ናት። ችግሩ የእሷን ጥልቅ ተፈጥሮ የሚመጥን አቅም አላገኜችም። ስለሆነም ዘመን ከዘመን ተረጂ ሆነች። ቀደምት ግን ደኃ። ሁሉ ያላት ግን ለማኝ።
    ኢትዮጵያ ውስጥ የለም የሚባል ነገር የለም። ሰጥቷታል። ግን ሙሴ?
    እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
    ሥርጉተ©ሥላሴ
    Sergute©Slassie
    09/04/2022
     
     ተፈጥሮን ክዶ የተነሳ ትውልድ አደራ አይደለም። የህወኃት ትውልድ አደራን መነጠረ፤ የኦነጉ ኦህዴድ ትውልዳዊ አደራን ሰዋዊነትን ጨምሮ ወደ አመድነት ቀዬረው። ይህን ጥቃት የሚመክት በእጅ ያለ ወጥ አቅም አለመኖሩ ማህፀንን እንደ ዱባ ይቀረድዳል። አዝናለሁ።
    ሥርጉተ©ሥላሴ
    Sergute©Selassie
    07/04/2021
     
     

 ሰቆቃው አማራ በቃ! ያለ ለት ኢትዮጵያ ትከደናለች።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
07/04/2021

 የህልውና ተጋድሎ የጫጉላ ሽርሽር አይደለም። ሲያሰኝህ የምታፈላው፤ ሲያሻህ የምታበርደው። በዲስፕሊኑ ልክ ፅናትን ለመፀነስ የማይኩ አለቃ የቅጥፈት ስብከት፤ የሸፍጥ ስሌት እንዳሻው ሊጋልብበት አይፈቅድም። ለጠላፊዎችም አርምሞ ሊኖረው ይገባ ነበር። አልሆነም። በተስተካከለ ጎዳና መኖርን ለማኖር የተጋድሎውን ፅንሰት ዶግማ መዋጥ ያስፈልጋል።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
07/04/2021

 ዕውነት ሲለዝ መኖር ይደርቃል።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
07/04/2021

 ዕውነት የሆነ ሰብዕና ቋሚ ሥነ - ምግባር አለው። ትውልድ የሚተርፈው ይህን ሰብዕና የእኔ ሲለው ብቻ ነው።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
07/04/2021

 

 መኖር ለተነፈገው ህዝብ ሠርግ ምኑ ነው? መኖር ለተነፈገው ህዝብ ኮሮጆ ምኑ ነው? አገር ለሌለው ህዝብ ዴሞክራሲ ምኑ ነው? መኖሩ የተዘረፈን ህዝብስ እመራለሁ ማለት ጣዕሙ ምንድን ነው? ሚሊዮን ኢንፒቲ።
{}{}{}{}{}{}{}{}{}{}{}{}{}{}{}{}{}{}{}
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie

 

 አቅምህ ኃይል አለው። በቁጠባ አስተዳድረው። አክተሮች ፈጣጣ ናቸው ከይፋዊ ጉዟቸው ግርዶሹ ያይላል። ልባም ከሆንክ ቅንጅት የፈረሰበትን ትርፍራፊ ላለማስጠጋት ቁረጥ። ወደ አያት ቅድመ ጥበብ ተመለስ። አቅምህን ቆጥበህ አስተዳድረው፤ ምራው። በተለይ ገራገሩ አማራ ልብ ይስጥህ። አሜን። ቅንነት ከመጠኑ ሲያልፍ ጅልነትም ነውና። ጅልነቱ ባልከፋ። በጅልነት ትውልድ አለመትረፋ ነው ጭንቁ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Se…

See more
 
ዕለተ ሮዩ ማዕዶተ ተናኜ
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ሕይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
"የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል
እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።"
(ምሳሌ 16 ቁጥር 9)
የፍቅር ተፈጥሮ ቁጥር አይደለም ትላለች ሥርጉትሻ።
አለመሆኑን አመክንዮ አለኝም ትላለች።
እንዲህ ገልጻዋለች።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
07.04.2021
ጎዳናዬ የቀደምቷ ኢትዮጵያን ግርማ ሞገስ መናፈቅ ነው። ለዛም መትጋት።
 
 
 
ዕለተ ሮብ ማዕዶተ ተናኜ
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ሕይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
"የሰው ልጅ መንገድን ያዘጋጃል
እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።"
(ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)
እኛዊነት ትውፊት ነው።
እኛዊነት ሰዋዊነት ነው።
እኛዊነት ተፈጥሯዊነት ነው።
እኛዊነት መኖር ነው።
እኛዊነት ትውልድ ነው።
እኛዊነት አደራ ነው።
እኛዊነት አገራዊነት ነው።
እኛዊነት መርኃዊነት ነው።
እኛዊነት ብሔራዊነት ነው።
እኛዊነት የጀገነ ነው።
እኛዊነት ኃላፊነት ነው።
እኛዊነት ተጠያቂነት ነው።
እኛዊነት ቤተሰባዊነት ነው።
እኛዊነት እሸታዊነት ነው።
እኛዊነት መታመንን መቀበል ነው።
እኛዊነት ዕውነትን ማፅደቅ ነው።
እኛዊነት ቤተኝነት ነው።
እኛዊነት የመሆን ጎዳና ነው።
በእኛዊነት ውስጥ እኔዊነት በአብሮነት በህብራዊነት አለ። እኛዊነትን የካደ ነፍስ እኔዊነትን ሰርዞታል። አንድ ሰብዕና ብቻውን አልቆመም እና። ያ እኛዊነትን የካደ የከዳ ሰብዕና እኔነቱ በተፈጥሮ ፀጋ ውስጥ የተገኜ ነው። ካለ ሴት ወይንም ካለ ወንድ አልተፈጠረምና።
መኖርን ያኖረው ፅንሰት ከተፀነሰበት ዕለት ጀምሮ በአብሮነት ፏፏቴ ይበቅላል። እናት መኖርን ስታኖር ምግብ ያስፈልጋታል። ምግቡ በህብራዊነት ቅብብሎሽ የበቀለ ነው። ዳቦ እንውሰድ። ስንዴ፤ ገብስ፤ ማሽላ ሊሆን ይችላል። ማን አመረተው? ቀድሞ ነገር ምግብ ለመሆን ማን ፈለሰመው? ማን ሃሳቡን አፈለቀው? ከፈለቀስ በኋላ ከስንዴ ዳቦነት እስከ ኬክነት በምን ሂደት አለፈ? ልብሱን፤ ማጣፈጫውን፤ ውኃውን፤ ነዳጁን፤ኤሌትሪኩን፤ እሳቱን፤ ኩራዙን፤ ፋኑሱን፤ ማረሻውን፤ ሞፈር ቀንበሩን፤ ወዘተ ወዘተ …
አንድም ቅንጣት የመኖር ጥበብ፤ የመኖር አኗኗሪ ግብ ሁሉ ከሰው ሰው፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ በቅብብሎሽ የበቀለ ነው። ይህን ጥሰህ የእኔ የእኔ ብትል ተፈጥሮን በፍራክሽን ብትሸነሽነው የካድከውም በክህደት የሰመጥከውም አንተው ነህ። ይህ ጥበብ የገባው ማህበረሰብ ነው ላቂያ የሚባለው። ላቂያነት እራስን ማወቅ ነው። እራስን ፈልጎ ማግኜት ነው።
እኔ ማን ነኝ? በማን ውስጥ ተገኜሁ? እንደምን ተፈጠርኩኝ? እንደምን ተገኜሁኝ? በምን ሂደት አለፍኩኝ? የሚል ጭምት ሰብዕና ትርምስ የለበትም። የብቻው የሆነ ቅንጣት ነገር የለውም። አሁን እኔ እፅፋለሁኝ። በአማርኛ ቋንቋ። ይህ ትውፊት የሸለመኝ ሥጦታ ነው። አማርኛ ቋንቋ ባይፈጠር አልፅፍም። ኮንፒተሩም ባይኖር አይዘምንም። ፌስቡኩም ካፒቴን ባይሆን አንገናኝም። በምድር ውስጥ የእኔ የሚባል ነገር የለም። ኑሮም አያውቅም። ይህ የእኔ ፍልስፍና ሊከብድ ይችል ይሆናል። ግን መርኃዊም፤ ዕውነትም ነው።
አንድ ሰው ብቻውን መኖርን ማኖር አይቻለውም። ይህ ቅዥትን በማህበረ ኦነጉ ኦህዴድ ሳይ ይገርመኛል። ገና ለፅንሰት ያልበቁ መሆናቸውንም አያለሁኝ። ዛሬን ማን ሰጣቸው? ዛሬንስ ማን አኖረላቸው? መልስ የላቸውም። ባለመፈጠራቸው ውስጥ ያለው የሃሳብ ድህነት ለግርድነት እንኳን አይበቃም። ለዚህ ነው ተፈጥሮን እዬገደሉት የሚገኙት። አለመታደል።
ፕላኔታችን የሚመራት እኛዊነት ነው። ድርጅት ሲፈጠር እኛዊነት ነው። ድርጅት ፈጥረህ አብሮነትን፤ ህብራዊነትን እኛዊነትን ሰርዘህ አይሆንም። ቅንጣት ነገር ብቻውን አይበቅልም፤ አይፀድቅም፤ አያሰብልም። ምንም ነገር። በአንዱ ውስጥ ሌልኛው፤ በሌልኛው አንደኛው በመስተጋብር ተዋህደው ነው የተፈጠሩት የሚፀድቁትም።
ሥርጉተሥላሴ
SerguteSelassie
07/04/2021
ጎዳናዬ ሰውኛ ነው።

 

 

 

 

 

 

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።