ኢትዮጵያ በኢመርጀንሲ ሩም። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 06/04/2023 #አንሰበርም።
ኢትዮጵያ በኢመርጀንሲ ሩም።
😢
መለጠጡን በልክ። እንኩቶ ነኩቶ የትውልድ እንዳማይሆን አውቆ ቢታሰብበን። ጡንቻ ሆነ ጠበንጃ ማሸነፍ አይደለም። ፈጣሪ የእስልምና ሮመዳን ዬእኛ ሁዳዴ አዋዶ ያቀረበው ምክንያት አለው።
ኢትዮጵያ በኢመርጀንሲ ሩም ውስጥ ናት። ለዘላቂ መፍትሄ እንተጋለን። ፀሎት፤ እርጋታ፤ ስክነት፤ የአበዱ እሳቤወች ግልቢያን መጠዬፍ፦ እያንዳንዱ የግፋዓን ቤተኛ በተሟላ ሥነ - ምግባር አምላኩን እግዚአብሄርን ሳያስከፋ በልኩ እንደ ልኩ ይጓዝ። አቅም አለን። ጨምተን ሳናባክነው አቅማችን መጠቀም ከተቻለ አያቅተንም። ዝርክርኩን ገርተን፤ ወጣገባውን ልገን በልኩ ልኩን እንዲያውቅ ማድረግ ይቻላል። ዬሚፈሩትን አልጀመርነውም። ስንጀምረው ደግሞ ይሆናል። በሩን ቧ አድርጎ ለጥረታችን ስኬት የሚከፍተው አንድዬ ነው። ቅኖች ነን እና።
በሥነ - ልቦና ቀውስ ዬሚታመሰው ኦነጋዊው ፋሺዝም መጣደፋ የሚጠበቅ ነው። ሰክኖ መጓዝን ይጠይቃል። የእሱን ሰበር እዬቀዱ ሰበር ከማለት። ህወሃት ጋር መስማማት ይህን ያህል ካንጠራራ፤ እንዲያው ሌላ ቢገኝ ምን ሊኮን ይሆን ያሰኛል። እኔ እንኳን አይሞቀኝ አይቀዘቅዘኝ።
በጥሞና ሁሉንም ነገር ቀድሜ ገልጫለሁኝ። ሰሚ ጠፋ እንጂ። የሆነ ሆኖ የገዳ መሳፍንታት በልክ ብትሆኑ አሁንም እንነግራለን። "ሲከር መበጠሱን ሲሞላ መፍሰሱን" ልሸልማችሁ። መጨረሻችሁ ይናፍቀኛል። ጥጋብም፦ ጥድፊያም፥ መወጣጠርም ሁለገቡ ጥቃትም፦ የሚሰክንበት፦ ምድር ቀውጢ የምትሆንበት ቀን ይመጣል። ተስፋችን አምላካችን።
"የቤትህ ቅናት በላይ"
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
06/04/2023
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ