#ብስጭትን + ቁጣን ሰክኖ ስለማስተዳደር። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 08/04/2023 #አንሰበርም!

 

#ብስጭትን + ቁጣን ሰክኖ ስለማስተዳደር።
 

 
ክብሮች እና ክብሬ ጤና ይስጥልን? እጅ ነሳን ከጭምቷ ቅኒት ቅድስቲት ሲዊዘርላንድ። እንዴት ነን። አይዞን!
እርእስ አስቀምጬ ጽፌ አላውቅም። ጽሁፍ ከጨረስኩ በኋላ ነው እርእስ እምሰጠው። ዬሆነ ሆኖ ይሞከር። ከብስጭት በላይ ቃል ካለ ብትነግሩኝ። በአማራ ህዝብ የደረሰው ከብስጭትም ከቁጣም በላይ ቢያደርግ አይደንቅም።
ልኩን አልፎ አለመሄዱ ለዓለም ሳይቀር የአማራ ህዝብ ዓለምን ያስተማረበት ተቋማቱ ነው። የአማራ ህዝብ እና ተፈሪ መንፈሱ በዬዘማናቱ ተጫኝ፤ አግላይ ሁነቶች በአንድም በሌላም ተከስተውበታል ብዬ አምናለሁኝ። የአማራ ህዝብ በብሄራዊ ብቻ ሳይሆን በዓለምም ደረጃ የታወቀ የታመቀ ሁነት እንዳለበት ይገባኛል።
አልተሰራበትም እንጂ ቢሠራበት የአማራን ህዝብ አንድ ቁልፍ ዕድምታ ያስፈልገው ነበር። ከኢንጂነር ታከለ ኡማ ጋር የቃላት ተርቲም ከመግጠም። ልብ እና ህሊና ፍላጎት እና ምኞት ተግብ ጋር ጋራ ለጋራ፤ አፋፍ ለአፋፍ ማስነው አቅሙ ሁሉ ዬትሜን እዬተበተነ ፈሶ እዬተለቀመ፤ ተለቅሞ እዬፈሰሰ ባልተባከነ ነበር።
የሆነ ሆኖ ሁሉም አስተዳዳሪ መሪ ይሻል። ሰውም እንሰሳም መሪ ይሻሉ። ቁጣም፤ በቃም፤ አይም፤ አሻም መሪ ይሻሉ። በስተቀር አናርኪዝም ይፈጠራል። በተለይ በዚህ ዓምስት ዓመት የታዘብኩት መሪወችም አናርኪ ሆነው ነው። #ገዢው ብቻ አይደለም። ተዋህጂ፤ ተቀናቃኝ፤ ተቃዋሚ፤ ተፎካካሪወችም። ተቀናቃኝ ከተፎካካሪ፤፦ተዋህጅ ከተተቀናቃኝ የዕድምታ ልዩነት አላቸው። በ2010 እኢአ ሰርቸዋለሁኝ። አሁን ኢዜማ እና አብን መግለጫ አወጡ ተብሎ እንደ አጋር ሲታዩ ይገርመኛል። አሁን ያለውን ሥርዓት ተቀብለው እያገዙ ዬሚያጠነከሩ፤ ጉልበት የሚያመነጩ አጋር ሳይሆኑ የጀርባ አጥንት ፒላሮች ናቸው። ስለዚህ ጥንካሬያቸው ሆነ ድክመታቸው ለገዢው ገዳወኦዳ ሥርዕወ ነው። ይህን አንጥሮ አብጠርጥሮ መለዬት እና አቅምን በአቅም የማስተዳደር አቅም ሊኖር ይገባል።
ዛሬ ላስተላልፍ የምሻው ቁምነገር የአማራ ወጣቶች ብስጭታችሁ፤፦ቁጣችሁ ዬተገባ ነው። እንዲያውም ትዕግሥታችሁ ለዘመን ተቋም ነው። ነገር ግን ቁጣም ብስጭትን በቅጡ ማስተዳደር ይገባል።
1) ስልታዊነት፦
2) ህግ አለመተላለፍ የሰማዩን የምድሩን፦
3) ዬነገን ፀሐይ ለማዬት መጓጓት፤ ካልተገባ መቀጠፍ ለራስ እራሳችሁ ዘብ መቆም።
4) የራሳችሁን አንጡራ ሥልጣኔ ተቃራኒ ሆኖ አለመቅረብ፦
5) የአባቶቻችን የጥሞና ትሩፋት እንዳይሰነጠቅ ጥንቃቄ ማድረግ፦
6) ትርፍ ቃል ከመናገር መቆጠብ፦ ዛሬ ያልፋል ነገ ይመጣል፤ ለነገ ጥሪቱ መልካምነት እንዲሆን አስቦ መነሳት፦
7) ፈጽሞ አልመጣላት፤ ከአመክንዮ፤ ከተለያዬ ሰብዕና ጋር ሊሆን ይችላል፦
አክብሮ መነሳት፤ አክብሮ መሞገት፤ አክብሮ መታገል፦
9) ለተሰሩ ተቋማት መሪ፤ አስተዳዳሪ ጠባቂ እኔ ነኝ ብሎ መወሰን፤ ጠባቂ መሆን፦
10) ህፃናት፤ ታዳጊወች እናንተን ስለሚዩ ዬእነሱን ቀጣይ ህይወት በማሰብ መነቃነቅ፤ ጥፋትን ማውረስ እሾህ ነውና።
11) መራራውን ዘመን ለመቋቋም ከአላህ፤ ከፈጣሪ ጋር ሰርክ በፀሎት በድዋ መገናኜት፤
12) ማድመጥ፤ ማድመጥ፤ ማድመጥ፤ ማድመጥ፤ ማድመጥ።
13) የራስ ዬጥሞና ጊዜ መውሰድ።
14) እያንዳንዱ ወጣት በራሱ የመረጃ ሠራተኛ መሆን። ሁሉንም ነገር በድምጽ፤ በፎቶ መሰነድ።
15) ስለሚሰው፤ ስለሚታገቱ፤ ስለሚታሰሩ፤ ስለሚደፋሩ፤ ስለሚፈናቀሉ ሁሉ መረጃውን መሰነድ። ለይቶም ማስቀመጥ።
ይህን ለማድረግ ስኩን ህሊና ይጠይቃል። ቁጣን በቅጡ ያስተዳደርን ከሆነ በዛሬ ውስጥ ነገን ማደራጀት፤ በዛሬ ውስጥ ነገን መምራት ይቻላል። በዛሬ ውስጥ ነገን እንዴት መምራት ይቻላል??? ቀጣዩ መሰናዶዬ ይሆናል።
"ዬሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል
እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።"
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
08/04/2023

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።