ልጥፎች

ከኤፕሪል 26, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ማህበረ ነፃነት እንዴት ሰነበታችሁ? እንዴት ናችሁ?

  ማህበረ ነፃነት እንዴት ሰነበታችሁ? እንዴት ናችሁ?   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   የተከበረው የኢትዮጵያ የምክክር ኮሚሽን "አህያውን ፈርቶ መደላድሉን" እንዲሉ ብሄራዊ ሆኖ ግን የእስረኛ ፍቺን አስመልክቶ፤ የአማራ ክልል ላይ ጫና ለመፍጠር መሞከሩ ግርም አለኝ። #አዝኛለሁም ። በእድሜ ዘመኑ የ365 ቀናት በራሱ አቅም የመንቀሳቀስ ምንም አቅም የሌለውን አልቦሽ ክልል ላይ ሃሳቡን ማቅረብ በራሱ ኮሚሽኑን ግምት ውስጥ ይጥላል።    የሆነ ሆኖ አጠቃላይ የፖለቲካ እስረኞች የእስር ፍቺ #በብሄራዊ ደረጃ ቅድሚያ ተሰጥቶት፦ በበኽረ ጉዳይ አጀንዳነት ተይዞ ሊሠራበት ሲገባ እንደ ተራ #ተለጣፊ ጉዳይ፦ የአማራ ክልል እስረኞች ብቻ እንዲፈቱ መጠዬቁ ኮሚክ እሳቤ ሆኖ ነው ያገኜሁት። ቀድሞ ነገር የህወሃትን መንበረ ሥልጣን እንዲለቅ ምዕራብውያንን ያሳመነው መሠረታዊ አንኳር ጉዳይ የፖለቲካ እስረኞች ጉዳይ ነበር። ያንጊዜ ተደማሪ፤ #ተጠማኝ ፤ ተዋህጂ ስስ ስለነበር በዬትም ሁኔታ የሚደመጠው ድምጽ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ ነበር የትግሉ ሞቶ። እናም አሳካን።    የሆነ ሆኖ የአማራ ጉዳይ ብሄራዊ እንጂ ክልላዊ አይደለም። በብልጽግና ፓርቲ የሚመራው የአብይዝም መንግሥት በቆራጥነት ሊወስዳቸው ከሚገቡ መቅድመ እርምጃወች ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት የፖለቲካ እስረኞችን #ያለምንም #ቅድመ ሁኔታ መፍታት ለቀጣዩ የፖለቲካ ንግግር ይሁን ስምምነት በር ከፋች ይሆናል።   እንደ እኔ ምኞት እና ተስፋ በኢትዮጵያ ምድር ማንም በአስተሳሰቡ፤ በምልከታው፤ በፖለቲካ #አቅሙ እና #አቋሙ አንድም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሊታሰር፤ ሊንገላታ፤ #ቤተሰቡ #ሊጉላላ አይገባም። በእስር ምክንያት የመኖር ተስፋው ሊዘረፍ፤ ወጣትነቱን ሆነ የ...

#እንፈላለግ።

ምስል
  #እንፈላለግ ።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"       #ጠብታ ።   ማህበረ ቅንነት እንሆ ምዕራፍ ፱፮ ተጀመረ። አቤቶ ብልጽግናም ስብሰባ ላይ መሆኑን አዳምጫለሁኝ። ግን እንዴት አደራችሁልኝ አዱኛወቼ የአገሬ ልጆች። መነሻዬ አቶ ኦባንግ ሜቶ ይሁን እንጂ ተያያዥ ጉዳዮችንም ላነሳሳ እችላለሁኝ። ድምንምን ብሏል። ዛፎችም ባልስ ላይ ናቸው። እርግቦቼም የሉም። ካፌያ ቢጤ መጣሁ ሄድኩኝ ይላል። አጤ ሚያዚያ እንደልቡ ነውና።   #ውስጤ ለዛሬ የሰጠኝ።   ሰሞኑን አቶ ኦባንግ ሜቶን በተደጋጋሚ #በህልሜ አዬዋለሁኝ። ስለሆነም #የፌስቡክ አካውንቱን እና #የኤክስ አካውንቱን መጎብኜት አስፈለገኝ። ሁለቱም አልተዘጋም። ይህ መልካም ነገር ነው። እኔ የኤክስ አካውንቱም ሆነ የፌስቡኩ #ተከታይ አልነበርኩም። ምክንያቱም በዘርፋ አክቲብ አልነበርኩም። ዘግይቼ ነው የጀመርኩት። የሆነ ሆኖ በፌስቡኩ ወደ 340ሺህ ተከታይ አለው። በኤክስ አካውንቱም ቀላል የማይባል ተከታይ እንዳለው አስተውያለሁኝ። ለመጀመሪያ ጊዜም ነው የጎበኜሁት።    አቶ ኦባንግ ሜቶ በሰባዊ መብት ጉዳይ ላይ አተኩሮ የሚሰራ፥ በዲፕሎማሲው ማህበረሰብ በቂ ዕውቅና የነበረው፤ ብዙ ኢትዮጵውያን እኔን ጨምሮ ከውስጣችን የምንቀበለው ትጉህ እና ታታሪ ወንድማችን ነው። በክፋ ቀንም ፈጥኖ ደራሽ። በዚህ በመጋቢት 2/2023 ፌስቡኩ ላይ የፃፈውን ኤክስ አካውንቱ ላይ ካጋራ በኋላ ሌላ ሼር ያደረገው ሃሳብ የለም። ምን ሆኖ ይሆን???   እኔ "የኢትዮጵያዊነት ሱሴ ንቅናቄን" በቅርበት ከሚከታተሉት አንዷ ስለነበርኩኝ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ሲመጡ በድፍረት፤ በግልጽነት ወጥቶ "የእኔ ጠቅላይ ሚር" ያለ ብቸኛው እና ቀዳሚው ሰ...