#እንፈላለግ።

 

"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
 Image
 
ማህበረ ቅንነት እንሆ ምዕራፍ ፱፮ ተጀመረ። አቤቶ ብልጽግናም ስብሰባ ላይ መሆኑን አዳምጫለሁኝ። ግን እንዴት አደራችሁልኝ አዱኛወቼ የአገሬ ልጆች። መነሻዬ አቶ ኦባንግ ሜቶ ይሁን እንጂ ተያያዥ ጉዳዮችንም ላነሳሳ እችላለሁኝ። ድምንምን ብሏል። ዛፎችም ባልስ ላይ ናቸው። እርግቦቼም የሉም። ካፌያ ቢጤ መጣሁ ሄድኩኝ ይላል። አጤ ሚያዚያ እንደልቡ ነውና።
 
#ውስጤ ለዛሬ የሰጠኝ።
 
ሰሞኑን አቶ ኦባንግ ሜቶን በተደጋጋሚ #በህልሜ አዬዋለሁኝ። ስለሆነም #የፌስቡክ አካውንቱን እና #የኤክስ አካውንቱን መጎብኜት አስፈለገኝ። ሁለቱም አልተዘጋም። ይህ መልካም ነገር ነው። እኔ የኤክስ አካውንቱም ሆነ የፌስቡኩ #ተከታይ አልነበርኩም። ምክንያቱም በዘርፋ አክቲብ አልነበርኩም። ዘግይቼ ነው የጀመርኩት። የሆነ ሆኖ በፌስቡኩ ወደ 340ሺህ ተከታይ አለው። በኤክስ አካውንቱም ቀላል የማይባል ተከታይ እንዳለው አስተውያለሁኝ። ለመጀመሪያ ጊዜም ነው የጎበኜሁት። 
 
አቶ ኦባንግ ሜቶ በሰባዊ መብት ጉዳይ ላይ አተኩሮ የሚሰራ፥ በዲፕሎማሲው ማህበረሰብ በቂ ዕውቅና የነበረው፤ ብዙ ኢትዮጵውያን እኔን ጨምሮ ከውስጣችን የምንቀበለው ትጉህ እና ታታሪ ወንድማችን ነው። በክፋ ቀንም ፈጥኖ ደራሽ። በዚህ በመጋቢት 2/2023 ፌስቡኩ ላይ የፃፈውን ኤክስ አካውንቱ ላይ ካጋራ በኋላ ሌላ ሼር ያደረገው ሃሳብ የለም። ምን ሆኖ ይሆን???
 
እኔ "የኢትዮጵያዊነት ሱሴ ንቅናቄን" በቅርበት ከሚከታተሉት አንዷ ስለነበርኩኝ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ሲመጡ በድፍረት፤ በግልጽነት ወጥቶ "የእኔ ጠቅላይ ሚር" ያለ ብቸኛው እና ቀዳሚው ሰው ነበር። በወቅቱ ቅንነቱ ግርም ብሎኝ ጽፌበትም ነበር። በሁለተኛ ደረጃ አወንታዊ ምላሽ የሰጡ እውቅ ፖለቲከኞች እና ልዑላንም ነበሩ። በእነሱም ላይ በእያንዳንዳቸው ውሳኔ ላይም ጽፌያለሁኝ።
 
አቶ ኦባንግ በነሐሴ 2010 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ካቀኑት ወገኖቻችን ውስጥ አንዱ ነበር። አቀባበሉም በክብር እና ሞገስ ነበር። ባልሰነበተ አንድ ኮሚሽን ውስጥም ተሹሞ እንደነበር አስታውሳለሁኝ። በተለያዩ መድረኮችም እዬተጋበዘ ማነቃቂያ ንግግር ሲያደርግ ነበር። ይህ መልካም የነበረ ሲሆን፦ የአሁኑ መሰወሩ ግን እጅግ በጣም #ያስጨንቃል። ቀን ስለማስበው ይሆናል ሌሊት በህልሜም የማዬው።
 
ከእኔ ጋር አንድ ጊዜ እርጅን ብሎኝ "ደወል" የምትባል ርዕሰ አንቀጽ ነበረቻቸው - የድርጅቱ። ያን በወር ሁለት ጊዜ በፀጋዬ ራዲዮ አቀርብ ነበር - በንባብ። በፀጋዬ ድህረ ገጽም አጋራት ነበር። ቡድኑ የሴቶችን ተሳትፎ የሚያከብር እና የሚያደንቅ ትሁት ነበር። እኔ የኢትዮጵያ ሴቶችን ተሳትፎ ከውስጡ አክብሮ የተቀበለ ድርጅት አላውቅም። ማሳደዱ ቢቀርብን ምንኛ በታደልን ነበር። 
 
……… ወደ ቀደመው ሃሳቤ ስመለስ ያው እኔ በዬትኛውም ንቅናቄ፤ የፖለቲካ ድርጅት በአባልነት በአካልነት በቋሚ ደጋፊነት የመሳተፍ ቅንጣት ፍላጎት ስለለኝ፤ በተጨማሪም የጸጋዬ #ብራንድም ጥንቃቄ ስለሚሻ እንጂ እንደ አቶ ኦባንግ ዓይነት የሰባዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት አይደለም ጠይቆኝ እራሴ ለምኜ - ፈቅጄም ብቀላቀል መልካምነት ነበር። በህይወት ዘመኔ የዬትኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባልም፤ አካልም ላለመሆን የወሰንኩት ስደትን ስመርጥ ነው።
 
የሆነ ሆኖ በርዕሰ አንቀፃቸው ጭብጥ ዙሪያ ለመነጋገር አቶ ኦባንግ ሜቶን በስልክ አልፎ አልፎ አገኜው ነበር። እዚህ ዙሪክ መጥቶ በአካል ከተገናኜን በኋላ #ደውሎልኝ አያውቅም ነበር። በለውጡ ሰሞን ግን ጥንቃቄ እንዲያደርግ እራሴ ደውዬለት ነበር። እኔ ስልክ መደወልም፤ ስልክ ማንሳትም አልወድም። ለእሱ ግን ደወልኩለት። የነበረን ተስፋ እና ውጥኑ #ብርቱ ጥንቃቄ እንደሚጠይቅ ላሳስበው። በዛው ወር ኢትዮጵያ መግባቱን ሰማሁኝ። በጣም #የተባ ተስትፎም ነበረው። ያ የተባ ተሳትፎ ምን #አነቀው? ማን #አነቀው ነው የዕለቱ ጉዳዬ። ጠንካራ ሃሳቦችን ልክ እንደ ካናዳ ቆይታው ሲያቀርብም አዳምጫለሁኝ። 
 
አንድ ሰው አንድ ውሳኔ ሲወስን በብዙ ነገሮች ውስጥ እራሱን ለማስገዛትም ሊሆን ይገባል። አንድ ምሳሌ ላንሳ ከዚህ ላይ። የእኔን ዕምነት ነው እኔ እማነሳው። አንድ ሰው ሲፈጠር 100% ነፃነት ይዞ ይፈጠራል ብዬ አምናለሁኝ። ሲያገባ 50% ነፃነቱ ለትዳሩ ስለሚያጋራ ይቀንሳል። ሲወልድ ቀሪው 50% ነፃነቱ ይጠናቀቃል። በእጁ የእሱ ወይንም የእሷ መኖር እስትንፋቸው የሆኑ ትርታወች ይኖራሉ። ስለሆነም ይህን ቀመር መቀበል፤ በዚህ ውስጥ ለመኖር መፍቀድ ይገባል ባይ ነኝ። 
 
አገር የገቡ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ይሁኑ ባተሌ ዜጎች ጥንቃቄ በሚሹ ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል። ነፃነትን በማስተዳደር ዘርፍ ነው ጥንቃቄው። ሃዋርያው፤ ድንግሉ አባታችን ቅዱስ ጳውሎስ " ሁሉ ተፈቅዶልኛል፤ ሁሉ ግን አይጠቅምም" ያለው የማይጠቅም ክስተት በመኖር ውስጥ ምርጫ አይሆንም አይመስለኝም ሚስጢሩ። እንደ እኔ የቁም ንባብ የሚጠቅምም ሆኖ፦ ግን ይለፈኝ ሊባል የሚችል አመክንዮ ሊኖር ይገባል ነው። ከወዳጅ ዘመድ ጋር መሆን፦ አገር መግባት፤ ማግባት መውለድ፤ ብልጫ ያለው ጉዳይ ነው፤ ለህይወት አደጋ ከሆነ ግን #ጥንቅር ይበል፦ መገደሜ ይመቸኛል ብሎ፤ ያንም የሐሤት መገኛ አድርጎ መፍቀድ ይገባልም ባይ ነኝ። ከጥንቃቄ ትርፍ እንጂ ኪሳራ የለምና።
 
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል እና ያለው የነፃነት ማሳ እንደ ምዕራብውያን አይደለም። በራሱ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል እራሱን ችሎ የራሱ ማንነት እና ባህሬ አለው። በመኖር ውስጥ የፖለቲካ መሻትን ለማጣጣም #ጥንቁቅነት #ከዊዝደም ጋር ማጋባት የሚያስፈልግ ይመስለኛል። እራስን መመስጠርም ይገባል ባይ ነኝ። 
 
ሥልጣን ላይ ያለን የፖለቲካ አካል ለመሞገት ይሁን ለመተቸት፤ ለመታገል አገር ውስጥ ሆኖ ከሆነ #ወሰን አለው። #ደንበር አለው። የሚፈቀድ እና የማይፈቀድ ሁነት ይኖራል። ያን ጠንቅቆ መረዳት እና በዛ መስመር ልክ መራመድ፤ ስሜትን በቅጡ ማስተዳደር ይጠዬቃል። እንደ ልብ፤ እንደ አሻ ለመሆን ባዕቴ ትናፍቀኝ #እዬሳሳኋት በስደት ልኑር ብሎ የመወሰን ቁርጠኝነት ይጠይቃል። አገሬ ላይ ሆኜ በጠንካራ ሙግት የፖለቲካ ህልሜን አሳካለሁ ዳጡ የምጥ ያህል ይመስለኛል። ዱር ቤት ካልተመረጠ። ይህም በራሱ ራሱን የቻለ ውስብስብ ፈተና አለው። 
 
ሌላው ቀርቶ #ስደት ላይ ቢሆን ጥንቃቄ የሚጠይቁ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች አሉ። በተለይ #የዘመኑን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህሬ ማወቅ፤ የጠቅላይ ሚር አብይን የአይቲ ባለሙያነት፤ የኢንሳ መሥራችነት፤ በሚሊተሪ የነበራቸው ቆይታ፤ በመንግሥት ሥርዓት ውስጥ ያላቸው ሙሉ መረጃ እና ልምድ፤ በዞጋዊ (ኦነጋዊ) መንፈስ የተፈጠሩበት የፖለቲካ ሁነት፤ የሰብዕና አገነባባቸው ከአስተዳደጋቸው ጀምሮ፤ ውህድ ማንነታቸው የሚፈጥረው ጫና እና ፈተና፤ የስሜታቸው ተለዋዋጭነት እና አቅጣጫ #ብልጽግና የተገነባበት ዕውነት ነው። አገር ሲገባ በዚህ መዕቀፍ ውስጥ እራስን ለማስገዛት ማሰብ። ማሰብ። መወሰን። መወሰን። መቁረጥ። መቁረጥ ይገባል።
 
ፓርላማው፤ ካቢኔው፤ ፌድሬሽን ምክር ቤት፤ የጸጥታ አካላቱ፤ የሲቢል ተቋማቱ፤ የፖለቲካ መወቅራዊ ሰንሰለቱ ቀመሩ ሲደመርም ይሁን ሲባዛ፤ ሲካፈልም ይሁን ሲቀነስ፤ ይዘቱ ይሁን ቅርጹ፤ ዲያጎናል ይሁን ሦስትም ማዕዘን፤ አራትም ይሁን ባለ አምስት ጠርዝ ግርፋ የሚገራው #በአብይዝም ሙሉ መንፈስ ስለመሆኑ መቀበል ግድ ይላል።
 
አብይዝም ደግሞ ስስ የሚሆንበት። በችሎት የሚያልፈው። በብስጭት የሚያስተናግደው። ትዕግስት አልቦሽ ሆኖ ግብታዊ የሚያደርገው ካልኩሌሽን አለው። በብዙ እኔ እማስተውለው አብይዝም ለእኔ #አሳቻ ነው። አይደለም ለማመሳጠር በቁሙ ለማንበብም ይፈትናል። ለመተርጎምም - እንዲሁ። አቃለው፤ አጣጥለው የሚናገሩ ፖለቲከኞችን አብዝቼ እገረምባቸዋለሁኝ። እንደዚህ ዘመን ብርቱ ጥንቃቄን የሚሻ ከባድ ዘመን በፖለቲካ ሕይወት ዘመኔ አላዬሁም።
 
አብይዝምን ለመሞገት --------ማስተዋልን ውጦ፤ እራስን አድምጦ፤ ሌላውንም አድምጦ ከተኖረበት ፖለቲካዊ ባህል በባህሬውም ሆነ በሂደቱም ብርቱ ጥንቃቄ የሚጠይቅ መሆኑን ተቀብሎ የሃሳብ ሙግቱንም፤ ትግሉንም በጥበብ ለመምራት መሻት ብቻ ሳይሆን በዛ #ዲስፕሊን እራስን ማስገዛት ይጠይቅ ይመስለኛል። ሙሉ ዕድሜ አህጉራዊ የችግር መፍቻ ተመክሮ የነበራቸው ሻለቃ ዳዊት ሰሞኑን የሰጡትን የግንባሩ አፈጣጠር እና ሁነቱን ሂደት ሲገልፁ አንዲት ብርጭቆ የተሰበረባቸው አይመስልም። በሌላ በኩል የ፬ኪሎ ምኞት እና ስኬታቸውን ያቀረቡበት ሁነት እጅግ በጣም ነው የገረመኝ። ሻለቃ ዳዊት እራሳቸው ማንነታቸው በተመክሮ የከበረ ማንነት ያላቸው ግን አብይዝብን መዝነው የተነሱበት መንገድ እና ውጤቱከተመክሯቸው ጋር በፍጹም ሊመጣጠንልኝ አልቻለም።
 
የዘመኑ የፖለቲካ ባህሬም ሆኖ የፖለቲካ ስኬቴ ብልጥነት ሳይሆን #ብልህነትን በጥንቃቄ ይጠይቃል። ቅጽበታዊነትን ሳይሆን ተረጋግቶ ማሰብን ይጠይቃል። ግብታዊነትን ሳይሆን ሰክኖ መራመድን ይጠይቃል። ይህም ሆኖ መኖርን አስቀጥሎ፥ አደራን ማስቀጠል ከተቻለ በውነቱ ዕድለኝነት ይሆናል ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ማህበረሰብ። አቶ ያሬድ ኃይለማርያም ጥሩ ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ ይመስለኛል። ሞጋች ናቸው፤ ከሚሞግቱት አመክንዮ ይልቅ #ጠንቃቃነታቸው ያመዝናል። ለአቶ ያሬድ ኃይለማርያም ጥንቁቅነት #ካሪክለማቸው ይመስለኛል። ይህም ሆኖ ተቋማቸው ታግዶ ነበር። ይለፍ ተሰጠው ይሆን???
 
የሆኖ ሆኖ ጹሁፌ መነሻዬ አቶ ኦባንግ ሜቶ የት ነው ያለው ይሁን እንጂ፤ እሳር ቅጠሉ ፖለቲከኛ በሆነበት ዘመን ኢትዮጵያ ለመኖር ትናንት የወሰኑ፤ ዛሬም ላቀዱ "ላም እረኛ ምን አለን" ለማጠዬቅ ነው መነሻዬ። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል በቅንነት እና በሰባዊነት አልተፈጠረም። በማድመጥ እና ግድፈትን በማረም አላደገም። በርህርህ እና አጽናኝነት አልጎለመሰም። የአቅም ምንጩን በቅጡ ዕውቅና ሰጥቶ የማስተዳደር አቅሙም ያን ያህል ነው። ሁልጊዜ አፍሶ መልቀም። ለቅሞ ማፍሰስ ነው። በሂደቱ ትውልድ ታጨደ። የትውልድ ተስፋ ባከነ። አብነት ሆኖ የሚዘልቅ እና የሚያዘልቅ መሻታችንም ከሳ።
 
አንድም ሰው አላዬሁም አቶ ኦባንግ ሜቶ የት ነው ብሎ የጠዬቀ። ድርጅቱም አይጠይቅም። እሱን ያበረታቱ የነበሩ ሚዲያወች ዝምታቸው እጅግ ያስፈራል። የኢትዮጵያ የምክክር ኮሚሽንም ጥቁሩ ሰውን ያህል እንዲህ ድምጹ ሲጠፋ የት ነው ያለው ብሎ አይጠይቅም። ታሞ ነውን? አልጋ ላይ ውሎ ነውን? ወይንስ በሌላ ምክንያት???? ኃላፊነት የሚጀምረው #ከመብት ሳይሆን ለእኔ #ከግዴታ ላይ ሊሆን ይገባል ባይም ነኝ።
 
የእኔ ክብሮች እንፈላለግ። እንጠያዬቅ። የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነት ለመኖራችን ደንበር ሊሠራ አይገባም። በተለይ ለሥልጣን የማንታገል ወገኖች ቅድሚያ ሰው ሆነን ስለመፈጠራችን ብቻ እናስብ። በሌላ በኩል ሥልጣን ላይ ያለውን አብይዝም መደገፍ፤ መቀበል መብት መሆኑን ዕውቅና መስጠት ይገባል። አብይዝንም በሃሳብ መሞገትም መብታችን ስለመሆኑ የአብይዝም ሥርዓት ደስ ብሎት ሊቀበለው የሚገባ አመክንዮ ሊሆን ይገባል። ብልጽግና ትምህርት የሚያገኜው ከእኛ ከሞጋቾቹ እንጂ ከደጋፊወቹ አይደለም።
 
በተለይ ክብርም፤ ዝናም ለማይነሽጠን ሰብዕናወች ቂምም፤ በቀልም መኖሪያ በዓታችን አይደለም እና አብዝተን ልንፀያፈው ይገባል። ቅን እንሁን። ርህርህናን እንጠጣ። ብልህነትን እንዋጥ። ሆደ ሰፊነትን እናበረታታ። እግዚአብሄር ይርዳን። አሜን።
 
ግን ወዳጄ አቶ ኦባንግ ሜቶ የት ነው ያለው?????
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
ደህና ዋሉ፤ ደህና አምሹ፤ ደህና እደሩልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
26/04/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
እንፈላለግ።
 
 

Obang MethoMarch 2/2023

"In the History of Mankind, there has never been any other black man like Menelik II, who had triggered a lasting fear and doubt in the mind of Europeans" #Ethiopia Augustus Wylde (Historian & Author
How can we get out from the pit that has been dug as a result of ethnic federalism or institutionalized tribalism and ethnic favoritism? Making ethnicity into an idol to worship is taking a toll on us as a society and as a nation. 
 
It is a deception based on ignoring the truth about the value of all human beings. So, how do we recover from this as a nation after so many have fallen victim to its deception and destruction that it would protect us; rather than the truth, that it endangers us? 
 
It will require self-examination, truth-seeking, moral strength, righteous living and moral leadership. This beautiful country of ours needs God-fearing leadership like the Emperor Menilek II who will boldly speak the truth, even if it is sometimes unwelcome.
 
It was that kind of leadership and the unity of the people around common values and goals that brought the victory at Adwa. Anything less than genuine fear and respect for the truth, will fail us as people and nation. 
 
Ethiopia needs visionary and highly principled leaders to bring the people together with common values that will lead to a real and sustainable victory for all. 
 
What Ethiopia needs now is to value the humanity of others, our strongest common bond.
We must create a social covenant among all our people to morally commit to valuing each other and their rights. This is a battle of ideas and principles where our Creator has given us truth and a conscience so we might better know the way forward. It not a struggle for “me or my ethnic group only,” but it is a struggle for “we the people of Ethiopia”
 
A genuine united Ethiopia will only rise up by committing to a new social covenant among us. That covenantal agreement must include a commitment to uphold the rights of all our people and to live lives of truth, justice and virtue towards each other. This would be a victory for the soul of our nation. This would be a victory that surpasses Adwa.
 
May God help us to see the deception and danger we face when we use our lesser identities like the ethnicity to destroy ourselves instead of our common identity as human beings to unite us.
Once again, Happy 127th Anniversary of Ethiopia’s Victory at the Battle of Adwa."
 
"Long Live Ethiopia."



  • አስተያየቶች

    ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

    ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

    እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

    የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?