ልጥፎች

ከሜይ 16, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የአቦ ሌንጮ ለታ የፖለቲካ አቋም እና መጪው ተስፋው።

ምስል
           ?                                   ከሥርጉተ - ሥላሴ 15.05.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)      „ከእንቅልፍ የምትነሱበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቧልና።                                                                                              (ወደ ሮሜ ምዕራፍ ፲፫ ቁጥር ፲፩)             ለሰሞናት ብቻ አይደለም ይህ የጥያቄ ምልክት ስለ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር በህሊና ቦታ ሊሰጠው ይገባል የምለው ለቋሚነት ነው። ዝም ብል በወደድኩኝ ግን የምሳሳለትን የለማ አብይ ገድ „የኢትዮጵያዊነት ሱስ ነውን“ „የሚሊዮኖችን ድምጽ“ ከአደጋ ለመከላከል የሚሰማኝን ከመግለጽ መቆጠብ አይገባም ብዬ ስለማምን ነው። የማልደራደርበትም ቀን ከሌትም ዕንቅልፌን ትቼ አቅሜን ያፈሰስኩበት የዘመኔ የማግስት ጮራዊ ፈለጌ ነውና። ተፈጥሮዬም ይኸው ነው። በተያያዘም ለማከብራቸው ለጸሐፊ አቶ ግርማ ካሳ የምለው ይኖረኛል።             እንዴት ባጁ?      ጤና ይስጥልኝ የማከብረዎት አቶ ግርማ ካሳ እንዴት ሰነበቱ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። በወርሃ መጋቢትመጨረሻ       ይመስለኛል ግንቦት 7 ከኤርትራ ጋር ያለውን ግንኙት እንዲያቆርጥ በጻፉት ጉዳይ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ጹሑፍ ስጽፍ በቀላል    የፖለቲካ ድርድር ሊሆን እንደማይችል ጽፌ ነበር። እርግጥ ነው ሥመዎትን አላነሳሁትም። ምክንያቱም በዛ ጹሑፍ ላይ ክብርት         ወ/ሮ አና ጉምዝን ጨምሮ በርከት ያሉ ወገኖቼን አንስቼ ስለነበር እንዳይበዛ በማሰብ ነበር። አሁን መቼም ክብርት ወ/ሮ አና ጉምዝ ቃ