የአቦ ሌንጮ ለታ የፖለቲካ አቋም እና መጪው ተስፋው።

           ?

                                  ከሥርጉተ - ሥላሴ 15.05.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)
     „ከእንቅልፍ የምትነሱበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቧልና። 
                                                                                            (ወደ ሮሜ ምዕራፍ ፲፫ ቁጥር ፲፩)

           ለሰሞናት ብቻ አይደለም ይህ የጥያቄ ምልክት ስለ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር በህሊና ቦታ ሊሰጠው ይገባል የምለው ለቋሚነት ነው። ዝም ብል በወደድኩኝ ግን የምሳሳለትን የለማ አብይ ገድ „የኢትዮጵያዊነት ሱስ ነውን“ „የሚሊዮኖችን ድምጽ“ ከአደጋ ለመከላከል የሚሰማኝን ከመግለጽ መቆጠብ አይገባም ብዬ ስለማምን ነው። የማልደራደርበትም ቀን ከሌትም ዕንቅልፌን ትቼ አቅሜን ያፈሰስኩበት የዘመኔ የማግስት ጮራዊ ፈለጌ ነውና። ተፈጥሮዬም ይኸው ነው። በተያያዘም ለማከብራቸው ለጸሐፊ አቶ ግርማ ካሳ የምለው ይኖረኛል።




  •            እንዴት ባጁ?
    ጤና ይስጥልኝ የማከብረዎት አቶ ግርማ ካሳ እንዴት ሰነበቱ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። በወርሃ መጋቢትመጨረሻ       ይመስለኛል ግንቦት 7 ከኤርትራ ጋር ያለውን ግንኙት እንዲያቆርጥ በጻፉት ጉዳይ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ጹሑፍ ስጽፍ በቀላል    የፖለቲካ ድርድር ሊሆን እንደማይችል ጽፌ ነበር። እርግጥ ነው ሥመዎትን አላነሳሁትም። ምክንያቱም በዛ ጹሑፍ ላይ ክብርት 
       ወ/ሮ አና ጉምዝን ጨምሮ በርከት ያሉ ወገኖቼን አንስቼ ስለነበር እንዳይበዛ በማሰብ ነበር። አሁን መቼም ክብርት ወ/ሮ አና ጉምዝ ቃል ብቻ አለመሆኑን በዬቀኑ እንደ ተንዠረከከ የወይን ዛፍ ተግባርን የሰነቀው ድንቅ አዲስ ጉዞ መረጃ ይደርሳቸዋል ብዬ አስባለሁኝ „ቃል ብቻ በቂ አይደለም“ ሲሉ ያጣጣሉት አንደበት ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አጀብ እያሰኘ ነው። ምንም ግርዶሽ ሊሠሩለት አይችሉ ነገር።

የሆነ ሆኖ ጸሐፊ አቶ ግርማ ካሳ ግንቦት 7 ጓዘ ቀላል አይደለም ብዬ ጽፌለወታለሁኝ። በአሁን ጹሑፈዎት ይሄን አስተካከለዋል። ይህም ተመስገን ነው። ስለ ወጣት ጆዋር መሃመድም እንዲሁ መሰል ምኞታዊ ነገር በአሁኑ ጹሑፎት አንስተዋል። እሱም ቢሆን እንዲህ በቀላል የሚሆን አይደለም። ኤርትራ ሦሰት ሚና ነው የምትጫወተው። ኢትዮጵያኒዝም ለሚለው አንድ ሃይል አጉልታ ማውጣት ቀዳሚ ተግባሯ ነው ሚደያን ጨምሮ። በዚህ ላይ ልዩ ጥንቃቄዋ ጎልቶ የሚወጣው የአማራ የፖለቲካ ሊሂቅ እንዳይሆን በብርቱ መስጥራ የያዘችው ሲሆን ከአማራ ውጪ የሆነ በአለባሶ የተሠራ የኢትዮጵያኒዝም አቀንቃኝ አሰናድታ መንፈስን መቆጣጠር ከቻለች ይህ ታላቁ ህልሟ ነው። ከአማራ ውጪ ሆኖ ጠንከር ያለ የኢትዮጵያኒዝም መንፈስ ያለውንም አትሻውም። ይሻክርታል ሞረድ ስለሆነ። የሚዲያዋ ተግባርም በዚህ ስሌት የኼው ነው። በብርቱ በበላይነት የምትቆጣጠረው መስክ ይሄው ነው። ይህ እንግዲህ ተንክባክባ እስከ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ የሠራላት መንገዷ ነው።

ሁለተኛው የዚህን ተፃፃራሪ በአለባሶም ሳይሆን ኢትዮጵያኒዝምን በቀጥታ የማይበቀበል ማሰናዳት ነበር ምኞቷ፤ ይህም ተሳክቶላታል። አይዋ ተስፋዬ ከይሴም አሉ። ድርጅቱ ህቡ ነው አዬር ላይ ነው ያለው፤ እከሌ ሊ/ምንበሩ እክሌ ጸሐፊው አይባልለትም። ቀኝ ጌታ ሚደያ ኔት ወርክ ነው የሚባልላት። በመንፈስ በተሟላ አቅም የተደራጀ ነው። ለዚህም እንደ ግንቦት 7 አቅሟን፤ ጉልበቷን፤ መዋለ ንዋያውን አፍሳለች። የኋዋላ ደጀኗ አከርካሪዋ ነው። ቢከፋኝ ብመለስ የምትለው መተማማኟዋ ባለርግጧ ሰንዷ ነው። ስለዚህ በዚህ በኩል ቢሆን በቀላሉ መላቀቅ የሚቻል አይሆንም።

ሦስተኛው በራሷም ሰዎች፤ በሌሎችም ሰዎችም ማለት በራስ ወገንም፤ የሌላ ሐገር ተወላጆችን በገንዘብ ገዝታ ቢሆን ተጨማሪ ሊንክ የሚፈጥርላት የስለላ መረብ ኢትዮጵያ ላይም ውጪ አገርም ማዘጋጀት ነው። አሁንም እኮ ልብ አላላችሁት ይሆናል እንጂ ባለከረባት ተስፋዬ ገብረከይሲን የሚወክል ጮሌ አምሳሉን በገበርዲን እና በከረባት ዲሲ ላይ ይንጎራደዳል። ይህ ረቂቁ የመንፈስ ሊንክ ነው። ሁለቱን የሚዲያ አውታሯን ቀጥ አድርጎ የያዘ ሰቅ ነው አዲሱ ባለገበርዲን። የሆነ ሆኖ በዚህ ዙሪያ ጊዜ የሚፈታውም፤ ላይፈታውም የሚችል ድሎችን አሳምራ ትቆጣጠራለች እቴጌ ኤርትራ። ይህን አስተውለነው የማናውቀው የሃቅ ማህደር ነው። ብናስተውለውም የደሙን ሥር አይደለም። የእኛ ነገር ወንዝ ሲሞላ እና ሲጎድል ዘንብል ቀና ስለምንል፤ ንፋስም ስለሆነ የፖለቲካ ፍላጎታችን የሚመራው እንጂ በሳል ተግባርን እስከ አሁን በዝምታዋ ውስጥ ከውናለች። የቆዬ ቂሟን ሁሉ በብዕር ሳተና ላይ አወራርዳበታለች። ወደፊትም ዓራት ዓይናማ መሪዋ በህይወት እስከ ቆዩላት ድረስ ይቀጥላል። እኛ ደግሞ በጥልቀት ሂደቶችን የምናይበት ተመክሯችን እንብዛም ነው። ምክንያቱም ኢትዮጵያዊነት ያለው አቅሙ እንደ ጽዮናዊነት ሆኖ የመውጣት በስልስል ስለተካሄደበት። ለወጣቶች እኔ በአጋጣሚው የምመክረው እኔ በልጅነት ወደ 15 ጊዜ ያነበብኩት ወጥ አይደለም ትርጉም ነው „ምጽአተ እስራኤልን“ እንዲያነቡት ነው። የራሳችንም ይዘን ማለትም ብሄረሰባችን ግን ውብ የሆነው ኢትዮጵያዊነትን ቅዱስ መንፈሳችን ስለሆነ ጉልበት ብናደራጅለት፤ ብናጎለበት ሁሉንም አካባቢዎች የእኔ የማለት እና ስለ እናት አገር ሁሉም የደህንነት ሠራተኛዋ ለመሆን ይቆርጥ በነበር። የሰው ልጅ አገር ያስፈልገዋል። እኛ ወፍ ዘራሾች አይደለንም። አገር አለችን ኢትዮጵያ!

ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ ያጣችውን የበላይነት ለማስከበር የምታደርገውን መፍጨርጨር በጥበብ እና በስልት ከፍ ባለ ብሄራዊ ስሜትም መቋቋም ያስችለን በነበር ብሄራዊነታችን ላይም አትኩሮታችን ቢደላደል። አሁን የሚያስፈልገው ጣምራ የተጋድሎ መስመር ህፃፁን ለማጽዳት እንደ ወል የቤት ሥራ ይሄ ቢሆን፤ እንደ መስታውት ሁሉንም የጥቃት መስመር ለማዬት አቅሙ ይኖራልና። ሁላችንም ከቤታችን ውጪ ነው ያለነው። በቤታችን አለን ቢባልም ወቅቱን የማደምጥ አቅሙ ጭራሹን በሌለ የተደመረ ነው። አሁን ካለው የወጣቱ ሥነ - ልቦናዊ ምልክታ በጭራሽ አፈንጋጭ ከሆነም ኢትዮጵያኒዝምን አፋፍቶ ለመቀጠል ጋዳ ነው የሚሆነው። ኢትዮጵያ እኮ ጎሰኝነትን በፖሊሲ ደረጃ የምታራምድ አገር ናት። ስለሆነም በአንድ ጀንበር ብን የሚል አይደለም። ህብረ ብሄር የሚባለውም ተልዕኮው ስንኩል የሆነውም ከጊዜው የተፈጥሮ ሥነ - ልቦና ጋር መቀራረብ ስለሚያነሰው ነው። እንደ ተኖረበት በዚህም ብቻ እኔ በምልህ ብቻ መስምር ቀርቷል። ይህን እንከተላለን ብንል ከባህር የወጣ አሳ ነው የሚያደርገን። ይህ ቅናዊ እሳቤ ጥቃትን በጥቃት ለመመከት ሳይሆን፤ ጥቃትን በጥላቻ ለመበቀል ሳይሆን፤ ራስን ለመከላከል የሚያስችል አቅም ይኖራል። ቢያንስ የሂደት ጅራት አይኮንም።

የእትጌ ኤርትራን ነገረ ምስጥረት እንዲህ በወቅታዊ ሞቅ ደመቅ እንድርቺ እንድርቺ፤ ቀዝቀዝ ድንዝዝ በሚለው የቅልሞሽ ትዕይንት ላይ ብቻ በማተኮር ራስን መጠበቅ አይቻልም። አጅሪት ሳተናዊት ኤርትርሻ ሰሞናዊትም አይደለችም። ባለጥንግ ድርብ መሪ አላት። ሃላፊነት የሚሰማው ለተነሳበት ርዕዮት። እቴጌ ኤርትራ ዘለግ አድርጋ ታስባለች፤ እርምጃዋ ከዘለግነት ጋር አዋዳ ትከውነዋለች፤ ብዙ መንገዷን እንኳን ባሊህ ብለነው አናውቅም። ትንሽ ግን ብርቱ ሞጋች ጎረቤት አገር ናት ኤርትራ። ሁለመናችን ዝርግ ስለሆነ በሁለመናችን እንዳሻት ትረማመዳለች እስከ ፈለገችው ድረስ። እዛው መሬቷ ላይ ብሄራዊ ሰንደቃችን ሲጠቀጠቅ ብሄራዊነት ስለመቃጠሉ አይሰማንም። እያንዳንዳችን በዚያ ብሄራዊ ሰንደቅ ውስጥ ስለመረገጣችን አይሰማንም። አይመረንም።
ኢትዮጵያ መሬት ላይ ደግሞ የለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵውያን ባልተፈቀደላቸው ቦታ እንሱ ብሄራዊ ሰንደቃቸውን እያውለበለቡ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርጉ ይፈቀድላቸዋል። ያልተመጣጠነ ብቻ ሳይሆን ራስን ገድሎ የጠላትን ክብር ገዢ መሬት ላይ ማስቀመጥ ነው። ውርዴትም ውርዴም ነው። የእኛ ብሄራዊ ሰንደቅ ባልተከበረበት ሐገር የሌላውን ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ የማክበር ግዴታ የለብንም። ለዛውም ኢትዮጵያ መሬት ላይ። የትኛውንም ብሄረሰብ፤ ሃይማኖት፤ ፆታ፤ ክ/ ሀገር፤ ዘመን ሊወክል የማይችል ግን የዓለም ጥቁሮችን ገደል የሚዘክር ቀለም ብቻ ነው አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ብሄራዊ ሰንደቅ እስር ላይ ሆኖ ነው ኤርትራውያን ብሄራዊ ሰንደቃቸውን ይዘው በአደባባይ ኢትዮጵያ መሬት ላይ ሰልፍ የሚወጡት።

ይህ በውነቱ የኢትዮጵያን ህዝብ ክብር የሚዳፈር እርምጃ ነው። እስከ አሁን በነበረው ኢትዮጵያ እንደ ዩክሬን፤ ኤርትራ ደግሞ እንደ ሶብዬት ህብረት አንቀጥቅጣ ተውናለች። መቼም ይሄ አሊ አይባልም። ሁላችንም ጸጥ አድርጋ መርታናለች። በራሳችን ቋንቋ እና ሥነ - ልቦና ሚዲያዋን ከፍታ አሹራናለች። በተለዋዋጭ የስልት አያያዝ እና ጥበብ ቀኝ ግራ እያሰኘች የሰልፍ እርገጥን ጭናናለች። አስረግጣናለች። ከእንግዲህ ደግሞ በሰቢሉም ሆነ በመለዮ ለባሹ በጥምር ግሎባል የደህንነት አቅም አቻውን የምታመጣጥንበት አቅም እና ጉልበት አሁን እናት ኢትዮጵያ መዳፏ ላይ አለ። ተመስገን! ለዚህ ነው ጫጫታው የበዛው። ሁከቱ ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ እንዳልረጋ የዛር ሾተላይ ሲያምሰን የባጀው። እነሱም አሁንም ማመሱ እንዲቀጥል መሬት ላይም ሌላ አዲስ የትውና ምዕራፍ ከፍተዋል። ምን አለ ቢተውን? አገር ብለዋል። ሆኖላቸዋል። እዛው እንደ ፍጥርጠራቸው … ለእኛ እንደ ኬኒያ እንደ ጁቢቲ እንጂ እኩል ፖለቲካዊ ተሳትፎ ጠይቂና አግኚ ሊሆኑ አይገባም። ለዛ ነው አሁን ያለው ከፍ እና ዝቅ። ለእነሱ ካቢኔ እኛ ባዕዳ እንደሆነው ሁሉ እንሱም ለእኛ ካቢኔ ፍርፋሪ መንፈስ እንዲኖራቸው የማንፈቅድ ሚሊዮኖች ነን። ከእንግዲህ እንዲጫኑን በሁለት ቢላዋ እንዲያርዱን አንፈቅድላቸውም። በተለይ በፖለቲካ እና ኤኮኖሚያዊ አመራር ቦታ ላይ። ይሄ ግልጽ የሆነ የፖለቲካ ውሳኔ ሊሰጥበት ይገባል። አይተኙልንም። ተጨቋኝ እና ጨቆኝዋ ቀረ። እድሜ  „ለኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ሰውሩ ሴራ ሁሉ አፈር ግጧል። ትቢያ ለብሷል። ጤነኛው መስመር ድሮም ያለው ወደፊትም የሚቀጥለው ሃይማኖታዊ ትስስራችን ነው። ይህ ፍቅርን - ጽናትን - መተሳሰብን - በጸሎት መረዳዳትና ያቀና ቅናዊ ዓውደ ምህረታችን ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ ጋብቻው ቢታከልበት መልካምነት ነው። በብልጠት የተኖረበት ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ያልተገባ ተዛነፍ ድራማ ግን … እእ።

በግልጽም በስውርም የኤርትራን እጅ ጠባቂው ሁሉ በአንድም በሌላም ወጊያው ደርቶ የሰነባበተው በዚኸው አንኳር አመክንዮዋ ምክንያት ነው። ይህ ግን እናትን በስለት ቢላዋ የማረድ ያህል ገዳይ መንፈስ ነው፤ በሌላ በኩልም የብሄራዊነት ስሜት ዱካነትም ነው። በታሪኳ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ስውር አመራር እና አደረጃጃት የወጣችበት ዘመን አሁን ብቻ ነው። ይህ የእኛ ልዩ ጌጠኛ ዘመናችን ነው። ለዚህም ነው እንደ ብሌናችን ጥበቃ የምናደርግለት ለኦህዴዱ ዓራት ዓይናማ መንገድ። ቀደም ባለው ጊዜም ቢሆን እቴጌ ኤርትራ የምትፈጽመው ሰውር ብሄራዊነትን የማስለል ዘመቻ ሳይታወቅ ቀርቶ አልነበረም። የእኛ የራሳችን ቀደምት ጠረን ባትሆን ፍንዳታው በዬቦታው በሆነ ነበር። የሚታወቁ ነገሮች እንኳን እንዳለዩ የሚታለፉት በዚህ ብልህነት ነው። ተገፍቶ የተወጣውም አሁን ከመሼ ነው „አድጊ“ እያለች ለምትመጻደቅበት አማራ መሪውም - አደራጁም - ለድል ያበቃሁትም እኔ ነኝ ብላ መንደላቀቅ ስታበዛ ነው። ስለቀረና ሴራዋ። በተጠላው አማርኛ እና በምትጸዬፈው አማራዊ የህልውና ተጋድሎ ላይ „የሻብያ ተላላኪ ወያኔ ሃርነት ትግራይ እንጂ እኛ አይደለንም“ ብሎ የወጣው ያ ዘመነ ገናና የአማራ የህልውና የማንነት አመክንዮዋ ተጋድሎ በልኳ እንድትቀመጥ ማድረግ ግድ ስላለ ብቻ ነው ሃቅ እንዲነጥር የሆነው። የመግደያ ገመዱ የነፃነት ትግሉን አንኮላሽታ የራሷ ገድል ለማድረግ ያሰበችው መንገድ ደረጃውን እንድታውቅ አድርጓታል። መንገዷም እርቃኗን አስቀርቷታል።  
  • ·         የአቅም ዕውነት። 
ሰዉ ፕ/ ኢሳያስ አፍወርቂን በጣም ቀላል መሪ አድርጎ ነው የሚያቸው። እሳቸው ማለት ፕሬዚዳንት ፑቲን ምስጋን ይንሳው። በዓለም ካሉ፤ በተለዬ ሁኔታ አቅም ካላቸው መሪዎች ውስጥ አንዱ ናቸው። የማይደክሙና የማይሰለቹ ትግሉን ወደውት እና በፍጹም ሁኔታ አክብረውትም የሚተጉ ሲባዛ ታታሪ መሪ ናቸው። ለዛውም የድህንት አፍቃሪ። ይሄ የግል ምቾት፣ ድሎት፣ የቀይ ምንጣፍ ራሮት የሚሉትን የማያውቁ። ስለዚህም ሲለኩ፤ ሲመዘኑ በግርድፍ ሳይሆን በጥልቅነት ሊሆን ይገባል። የሚከተሉት ርዕዮት የዛገም ቢሆንም፤ ዘመነ የሰዋዊነት ባይሆንም፤ በቋሚነት በሚከተሉት ርዕዮት ውስጥ የሚፈልጉትንም ሆነ ማድረግ የሚችሉትንም ጠንቅቀው በሚገባ ያውቃሉ። በጣምም ሩቅ ናቸው። የመካከለኛው አፍሪካ፤ የአፍሪካ ቀንድ ጉዳይንም ሆነ፤ መስጥረው ጥልት የሚያደርጓትን የኢትዮጵያዊነት ወላፍን በሚመለከት በሞቀ እና በቀዘቀዘ ቁጥር ከፍ ዝቅ አለማለታቸው እራሱ የመሪነት እርጋታቸውን ውስጥትን ያሳያል። ለመፈተሽም በዝምታ ውስጥ ስለሆኑ ይከብዳል። በዬተገኘው ማይክ ላይ ከሆነ እብድ የዘራው አዝምራ መሆን አይቀሬ ነው፤ በተለይ መስጥረው የሚጠሉት ማህብረሰብ፤ መስጥረው የሚጠሏት ሀገር ሚስጥራቸው ለሆኑ እንደ ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ላሉ ፖለቲከኞች። ተክድኖ ለመኖር መፍቀድ ከብልህነት በላይ ነው።


የሳቸው አያያዝ እጅግ ቁጥብ ነው። ሰፊው የተግባር መስካቸው ከመሪነቱ ይልቅ በደህነነት ሙያቸው ነው አትኩሮት ያላቸው። አብሶ ኢትዮጵያን በሚመለከት ሌላ የደህንነት ባልደረባ አያስፈልጋቸውም። እሳቸው የት ሄደው? በሌላ በኩል አቋማቸውን ማወቅ አይቻልም። የተቆለፈም የተከፈተም ነው ማለት አይቻልም። ሥም የለሽ ነው ብለው ይሻለኛል። በሳቸው ዙሪያ ራሱ ቃለ ምልልስ የሚያደርጉት ሆነ ከቦታ ቦታ የሚዘዋወሩት የማይጋፉት ነገር ሲገጥማቸው ወይንም የሚፈትናቸው ልዩ ጉዳይ ሲገጥማቸው ብቻ ነው። በአንድ ወቅት አንድ ኤርትራዊ ጋዜጠኛ ከአውስትራልያ ይመሰልኛል ያደረገው ረጅም ቃለ ምልልስ ጎራ ብለው የውስጣቸውን ስሜት የነካውን ጭብጥ ለማመጣጠን በOMN ነበር የታዩት፤ በውስጥ የሰላም አስከባሪና ጠበቂያቸው። በ90ዎቹ መጨረሻ አካባቢም የ12 የምንቅናቅ፤ የአንድ የግል ታጋይ ድርጅቶች እና ግለሰብን አስተባብሮ ጀብሃ ጠንክሮ መውጣት ሲያሰጋቸው በተገኙበት ቦታ በፍጥነት ተገኝተው ደጋፊዎቻቸውን አረጋግተዋል። 

እነዚህ ገጠመኞች እጅግ በጥቂቱ ናቸው የሚከሰቱት። በቅርቡም ግብጽ ላይ ያደረጉት ጉብኝት አቅሙ በመሰሉ ሊታይ ይችላል። እሳቸው ወደ አደባባይ የሚወጡበት መሥመር ልክ እንደ ጸሐይ የግርዶሽ ተፈጥሯዊ ሥርዓተ ህግጋት ነው ማለት እችላለሁ። ምን ለማለት ነው፤ አዬር ላይ ጩኸት በበረከተ ቁጥር ብቅ ጥልቅ የሚሉ ወጣ ገብ መሪ አይደሉም። ውስጣቸው በፍጹም ሁኔታ የተረጋጋ ነው እንደ ሥርጉተ ሥላሴ ዕይታ። ለመሪነት የሚያበቃ ክህሎት ብቻ ሳይሆን ጸጋም፤ ቅብዕም አላቸው ብላ ሥርጉተ ታምናለች። ሚዛኑ ግን ከመሪነት አዲስ ሃሳብ አፍልቆ አቅጣጫን ከማስተካከል ይልቅ በነጠረው የደህንነት ሙያቸው ላይ የበለጠ ዝንባሌ እንዳላቸው ነው እኔ የሚረዳኝ።
  
ችሎታቸው እና ብቃታቸው አክሎ አቅማቸው ሙሉ ነው - እንደ እኔ። ሚዲያ ላይ ብዙ ስለማይታዩ ወይንም በሃብት ጣሪያ ህዝባቸውን ዘርፈው ሰርቀው፤ በሥልጣን ባልገው ድሎት ተራራ ላይ ስላልወጡ ልናያቸው አልተቻለንም። ለግምገማም የሚያስቸግረው ተፈጥሯዊ ባህሪያቸው ይህም ይመስለኛል። ስለሆነም በዝምታቸው ውስጥ ያለ ዕምቅ ተመከሯቸው ጥንድ ድርብ ነው። ተመክሯቸውን ለማዋል የሚሰናዱት ለታላቋ ኤርትራ ላዕላይ ልዑላዊነት፤ ለታናሿ ኢትዮጵያ ህልም ቅስም ሰበራ ታህታይነት ነው። ኢትዮጵያን እንደ አንጡራ ጠላታቸው እንጂ እንደ ጎረቤት አገር አለመያታቸው አልበቃ ብሎ መሪነቱን መንበር አለቅም ማለታቸው ነው ገራሚው ነገር። ወያኔ ሃርነት ትግራይም ኢትዮጵያን አይወድም መሪነቱንም መልቀቅ አይፈልግም። ይሄ የሾሻሊዝም እንቅርታዊ ሞራል ይምሰለኛል።

የ43 ዓመቱ የፖለቲካ ትርምስ ደርግም አልመራውም፣ በውስጡ በሰገሰጋቸው የሻቢያ ልዑክ ነው የተመራው፤ ወያኔ ሃርነት ትግራይም አልመራው በውስጡ በዝንቅ በቀዬጣቸው የሻብያ ሰላዮች ነው ኢትዮጵያዊነትን የተዳፈረው፤ ኢህአፓም አልመራውም በመሰሉ መንገድ፤ ኦነግም አልመራውም ብሄራዊ ስሜቱን ወና አስቀርቶ፤ ግንቦት 7 በደረሰበት ዘመን አልመራውም ሙሉ ጥገኛ ስለሆነ ቀጥ አድርገው የመሩት ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ብቻ ናቸው። ሚደያውንም በዓለም አቀፍ ደረጃ በጣምራ በሦስት ቋንቋ በርካታ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ አሰማርተው በበላይነት እስከ „ጣና ኬኛ“ ድረስ አሳምረው መርተውታል።

„የልቤ ሽልማቴ የእኔ የነፃነት ድምጽ“ እስኪባል ድረስ። የወያኔ ሃርነት ሚዲያዎችን በሙሉ አቅሙ እንዳይሰራ እንኩትኩት አድርገው ከጥቅም ውጪ አድርገውት ነበር። በአንደበታችን እዬተናገሩ ውስጣችን አንበርክከው በሰውር ገዝተውታል፤ ነድተውታል። ዕድሜ ለመጋቢቱ 24 ቀን 2010 ዓ.ም የወያኔውን ሃርነት ሥርዕዎ መንግሥት ሚዲያ ከተረሳበት አቧራውን አራግፎ ትንሽ እንዲደመጥ በር ተከፈተለት። እርግጥ ነው „ከጣና ኬኛ!“ በኋዋላ የኦሮምያ ሚዲያ ትንሽ ቀደም ብሎ የአማራ ማስ ሚዲያ ተፎካካሪ ሆነው መውጣት ሲጀምሩ ሌላው ስልት ተነደፈ። ያን ቅስም ለመስበር የአገር ቤቶቹ የኤርትራ ልዑካን አንዴት ኢትዮጵያዊነት ዘለግ አለ ብለው አካኪ ዘራፍ ሲሉ ኢትጵያዊው መንፈስ ጉልበት እያገኘ መምጣቱ ስላስደነገጠ ነበር። አሁን ባለው ሁኔታ አቅም ያለው ሞጋች ጋዜጠኛ ማዬት ባያቻልም ዶር ነገሬ ሌንጮ የነበሩበትን ቦታ የተኩት ወጣት ድማፃቸው የሄሮድስ መለስ ዜናው ቢመስልም ተግባራቸው የአዲሱ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሸዴ ግን ስክን ያሉ ሃላፊነታቸውን ማስተር ያደረጉት ይመስላል።

እስከ አሁን ባለው መግለጫቸው ክሽንነት፤ ክውንነት፤ ልቅምነት፤ አጭር እና ግልጽነት መሆን በጅምር ደረጃ የሚያበረታታ ሲሆን በዚህ አያያዝ እንጨት እንጨት የሚለውን ጥንዙል የሙጃ መንገድ ከልተው ተደማጭ እና ለህዝብ የወገነ የዕውነት ሚዲያ ሊያደርጉት ይችሉ ይሆናል የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ሲዘፍንበት የከራረመውን ማዲያታዊ ሚደያ ተብዬ። ከላይም ባለቤቱ ባለቅኔው ጠ/ ሚር ስላሉበት። የOBN ጽዑም - ለዛ - ቃና - ምት - ጭብጥ አናት ብሄራዊነት እኮ ሌልኛ ነው የነበረው። ያን ሳቢ ክህሎት ብሄራዊ ከሆነ ተደማጭም ተወዳጅም የመሆን ዕድል ብቻ ሳይሆን ከህዝብ ዕውነተኛ የዕንባ ራሮት የመነሳት አቅም ሊኖረው ይችል ይሆናል፤ እንደ ካሬታ በወያኔ ሃርነት ትግራይ ቅዠት „ህዳሴ፤ አገሪቱ“ እያለ ልብ ውልቅ የሚያደርገው፤ ሙሉ ቀን ሲያንዘላልጠው የሚውለው ድብተኛና በቃሉ ጸንቶ የማያውቀው የወያኔ ሃርነት ትግራይ የማንፌሰቶ ልሳነ - ሚዲያ ።  
  • ·         ህልም።
ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ እሳቸው የታይታ ነገር አይወዱም። እሳቸው ከንቱ ውዳሴ አይፈልጉም። „ታሪክ የለኝም“ ሲሉም አዳምጫለሁኝ። ግን ለሚፈልጉት ዓላማ እና ግብ ኢትዮጵያዊ ቼጎቢራ ናቸው፤ እትብታቸውን እናት ሐገራቸውን ኢትዮጵያን ቢችሉ ጠቅጥቀው ላይ ለመሆን አስገድዶ በመዳፈር፤ ካልቻሉ ደግሞ በማመስ ታላቋን አፍሪካዊቷን ሲንጋፖርን ኤርትራን የልዕለ አፍሪካ እጬጌ ማድረግ ነው ህልማቸው። ለዚህ ደግሞ እስከ ህልፈታቸው ድረስ የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመክፈል የተሰናዱ፤ ሌብነትን አብዝተው የሚጸዬፉ፤ እንደ ተርታ ዜጋ ለመኖር የፈቀዱ ናቸው። ውስጣቸውን ፈታቶ ማዬት የማይቻል፤ በፖለቲካ መስመር አዘረጋግ፣ አመራር እና ሂደት ለያዙት ዓላማ እና ግብ ብርቱ የሚባሉ መሪ ናቸው። ታማኝ ወዳጅም ጓደኛም ሊኖራቸው የማይፈቅዱ፤ ሊኖራቸውም የሚችልም ነው ብዬ ባላሰብም ቁጥብነታቸው በራሱ ግን ውበታቸው ነው። ድርጁ ግን ልበ ክፍቶችንማ የወያኔ ሃርነት ትግራይ መሳለቂያ እና የቂም መወጣጫ ሆነው ነው ያዬናቸው።
    
ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ እንዳሰቡት ሊሳካላቸው ባልሄደ ቁጥር እልኽቸውን ዋጥ አድርገው በስንፍና ሳይሆን በትጋት፤ ተስፋ በመቁረጥ ሳይሆን በይቻላል ያለ የሌለ ሃይላቸውን ሁሉ የሚጠቀሙ ለጠላቶቻቸው የማይተኙ፤ የማይመቹም፤ ለወዳጆቻቸውም ልባቸውን በፍጹም ሁኔታ የማይሸልሙ፤ ራሳቸውን ያልተዋሱ፤ ልብ እንዲገጠምላቸው በጭራሽ የማይፈቅዱ የራሳቸው ሰብዕና ያላቸው ፈንገጥ ብለው የተፈጠሩ መሪ ናቸው። በተጨማሪም በራሳቸው ሰብዕና ላይ በርስትነት የጸኑ፤ ወለም ዘለም የማያውቁ ዝግና ብርቱ መሪ ናቸው። ማንም ሰው እሳቸውን አውቃለሁ ማለት አይችልም፤ ድፍረት ይሆናል፤ የሚመርጧቸውም ሰዎች መሰሎቻቸውን ነው።

በቅንነት እኛ እናውቃቸዋለን ብለን የምናስባቸው ሰዎች ሊሂቃንም ቢሆኑ የማናውቃቸው መሆኑን የምናውቀው ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ድጋፋቸውን በቀጣይነት ሲሰጡ እና ሳይተናኮሏቸው ሲቀሩ ብቻ ነው። ከዚህ የመረጃ ምንጭነት በምልሰት ወደ ቅኝት ምልሰት ሲደረግም የነገሩን ፍሬ ነገር ማስተዋል ይቻላል። ይህ ካልተገጣጠመ ማናቸውም የስምምነት ዓይነት በፈለገው ጊዜ ቅጽበታዊ በሆነ እርምጃ በድርብ ቅጣት ማህል ላይ ይቋረጣል። በአንድም በሌላም። ቤሳ ቤስቲ ርህራሄ፤ ይሉኝታ በሳቸው ጥርጣሬ ያለበት ማንኛውም ግለሰብ ይሁን ድርጅት አይጣልለትም። ድጋፍ ሲያደርጉም ለጊዜዊ ሊሆን ይችላል፤ ከግብ በኋዋላ ግን የአሮጌ አካፋ እና ዶማ ያህል ክብር የለውም። እርምጃው አለመኖሩ ከተፈቀደለት ዕድለኛ ነው። ስለዚህ የወጣት ጆዋር መህመድ ጉዳይም ከዚህ አንፃር ነው የሚታዬው ልለወት ነው ጸሐፊ አቶ ግርማ ካሳ። ስለሆነም ጸሐፊ አቶ ግርማ ካሳ ያቀረቡትን ዕይታ በዚህ መልክ ነው እማዬው እኔው።

ወጣት አቶ ጃዋር መሃመድ በዚህ መጠራቅቅ ውስጥ ያስገባው በእኛ የተለመደው ጥቃት፤ እንደ እኛ ተመስሎ አምቀን እንደያዝነው ገመና ተመሰሎ ዘው ተባለ። እኛ ለነፃነት ትግሉ ሞራል እንላለን በእሱ ቤት ግን ከራስ በላይ ንፋስ ባይ ነው። ስለሆነም በእጥፍ ድርብ ቀለሙን አሳዬ። የእሱ ጥንካሬ ደግሞ የሚታዬው ጥቃትን ለመቀበል አለመፍቅድ ብቻ ሳይሆን አቅሙን እኩል አመጣጥኖ ፖለቲካዊ ሰብዕናውን በመገንባት እረገድ የሚሄድበት መንገድ ሆነ ውሳኔ በሚዲያው አጀማመር እና እርምጃ ውስጡን ማዬት ይቻላል - ጥንካሬውን። አንዲህ ዓይነት የውስጥ ጥንካሬ የአልገዛም ባይነት መንፈስ መልኩ ከግራጫማ ይልቅ ውሃማ ቢሆን ለአገር እና ለወገን ጥቅሙ የት እዬለሌ በነበር። በዚህም ውስጥ የታዬው ጥቃትን ሳይቀበሉ ደረጃን አስጠብቆ የማስቀጠል ክህሎት ከአንድ ወጣት ለዛውም በዛ ዕድሜ የሚጠበቅ አይደለም። የወጣቱ ውስጥ የተደራጀ እና ጉልበታም መሆኑ ያሳዬናል። ይህን መሰል ሰብዕና ለፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ የስለት ልጅነት ነው። ጠረኑ አሽትተው ነው ያገኙት። ለሳቸው የተፈጥሮ ተልዕኮ የተመቸ እና ምሩጥ ነው።
  • ·         „ወደ ቀደመው።“
በስተመጨረሻ ለመናጆነት ማከያ የተሰናዳው የአማራ የሚባል ሲኦላዊ ድርጅት ነው። ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ አማራን አያምኑትም እንዲያምኑትም አይፈቅዱትም። አማራን አይወዱትም እንዲወዱትም አይፈቅዱትም። ዘመን የማያስታርቀው የጥላቻ የደም ነቀርሳ አለባቸው። አንጡራ ጠላታቸው ነው። ባዕድ ቀመር ነው። ማናቸውም የጦር አውድማ እና ቀጠና የቀወስ መናህሪ የማይናገር ተጎታች ማሳቸው ማድረግ የሚሹትም አማራ ነው። ለዚህ ነው አማራ መሬት ላይ ትጥቅ ማስፈታት ኢትዮጵያን አንጋሎ ለሻብያ ክብረ ልዕልና የመስጠት ያህል ነው የምለውም። ለአማራው መሳሪያ ልክ እንደ ገዳ ባህላዊ ትወፊቱ ነው። ትጥቅ ከፈታ ቁጣው እሳተ ጎመራ ነው። ያኮርፋል! ወኔውም ይንተከተካል! የትዳር አጋርም አያገኝም! በዚህ ጊዜ በስልት ገብታ እቴጌ ኤርትራ የልብኛ ትሆናለች ማለት ነው። በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ልቡ ይሸፍታል - ኗሪው።

በሌላ በኩል ደግሞ ትግራይን አይደፍሯትም። በእናትም በአባትም የደም ጥርኝ አለበት። እነ አጅሬ መቆራረጥ የለም። አፋርም ዘር አለ። ለስሜታቸው ለጠረናቸው ቅረበኝ ተብሎ የሚፈቀድለት ነው፤ በዛ ላይ ዘረ አማራ አይደለም፤ ያው „እንኳንስ እኛ ግመላችን ብሄራዊ ሰንደቃችን ያውቀዋል“ ይህ የውስጣቸውን ሰላም ቢያውከውም ከአማራ ቀረብ ያለም የተሻለም ስሜት ይኖራቸዋል ብዬ አስባለሁኝ - በግሌ። አፋር እና ኢሳም ሦስት ጎረቤታማ አገሮችን የሚያገናኙ ሌላ ቅኔ አለበት።

ተሳክቶ እርቀ ሰላም ቢመሰረትም አማራን ዘለል አድርገው ጉዞውን በአፋር ማድረጉ ለእኛም ለሳቸውም መልካም ነው። ቀደም ባለው ጊዜ አንድ የክ/ ሀገር የገበሬ ማህበራት የቁጥጥር ኮሚቴ ሊቀመንበር የሚሉት ነገር ነበር። „ሲጠሉት የወደዱትን ያህል መገበር ጅልነት ነው“ ይሉ ነበር። እኔም የምለው ይሄውን ነው። „ሲወዱም እስከ ንፍጥ ልጋጉ ሲጠሉም እንደዛው“ ይላሉ ጎንደሬዎችም። ሲጠሉን ምርታችንም መሬታችንም ጠረናችንም ሁሉንም እርግፍ አድርጎ መሆን አለበትም። ወሎም እኛው ነን፤ ጎንደርም እኛው ነን እና አማሮች። በዛ ላይ የዋጋው ንረትም አለ። አሁንም አልተቻለም የተያዘ የተረዘዘው ሁሉ ትግራይ ስለሚጫን።   
  • ·         ምልሰት ወደ አቦ ሌንጮ ለታ።
እኔ እኮ በተደጋጋሚ ተናጋሬያለሁኝ ጋራንቲ የለም ብዬ። የስብስቡ መፈጠር መልካም ነገርን በአሉታዊ ማዬት አይገባም ብዬም ጽፌአለሁኝ። ሰው ወደ ፍቅር ሲመጣ፤ ወደ ስምምነት ሲመጣ ቅንድቡን ብሎ ማሸማቀቅ አይገባም ብያለሁ ሲጀመር። ግን  እንደ ትልቅ የፖለቲካ ትርፍ፤ በድካም፤ በልፋት፤ ተወጥቶ ተወርዶ እንደ ተገኘም፤ በፖለቲካ ብስለት እና በጥበባዊ አያያዝ እና አማራር በብልህነት ብሂላዊ ዕውቀት እንደ ተፈጠረ ተደርጎ ሲታይ ግን እያቅለሸለሸኝ በተደጋጋሚ ጽፌ ነበር። ኢሳት በቃ ከሰማይ ጨረቃ ዱብ ብላ ብርሃን የለገሰች ያህል ነበር የላቀ ጉልላት አድርጎ ሲነግረን የባጀው። የፈጠሩት እነሱ እንኳን እያለ ማጠፋጫ፤ የመልካም ነገር ማውጫ ድርሳን፤  የኢትዮጵያዊነት ልዩ ሰንድቅ ዓላማ አድርጎ ሲያቀርባቸው ነበረ። ይህም ብቻ ሳይሆን እነሱ አቅማቸው ጎልብቶ ሀገር እስኪረከቡ ድረስ „አገር አድኑ ንቅናቄን“ ማለት ነው ቢመረንም ወያኔ ሃርነት ትግራይ በያዘው ይዞ ኢትዮጵያን ይዞ መቆዬቱ አማራጭ ስለመሆኑ ሁሉ ይገልጽ ነበር። እኔም በተገኘው አጋጣሚ እጽፍ ነበር። አሁን ባለው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አንዱ ከአገራዊ ንቅናቄ ከወጣ ለግንቦት 7 አደጋ ሊሆን ስለሚችል፤ ግንቦት 7 ለወ/ሮ አና ጉምዝ የሚነግረውን፤ ሚዲያው ኢሳት የሚለውን፤ ጸሐፊዎቹ የሚሉትን፤ ግንቦት 7 እንደ ድርጅት የሚለው በጣም የተለያዩ ስሜቶች እዬተስተናገዱበት ስለሆነ ወጥ አቋም መያዝ አለበት ብዬ ነበር። ሳይቀደም መቅደም። 

ግን አልሆነም። አቋሙ መንታ መንገድ እንደ ዋለለ የሆነው ሆነ፤ እንኳንስ ይሄ የአቶ ሞላ አስገደሞ ገና ጮርቃው ክህደት ስንት ነገር እንደ ናደ ይታወቃል። ገና ሳይጀመር ስለቀጣዩ የወታደራዊ አቋም፣ ምልምላ፣ ስልጠና ሁሉ ማብራሪያ ተስጥቶ ነበር። አብዩ ነገር የሰከነ ጥናትን መሠረት ያደረገ የህሊና ሥራ መሥራት ነው አንድን ድርጅት በጽናት ሊያስቀጥሉት የሚችሉት። አርበኛ አትሌት ሊሊሳ ፈይሳ ጀግንነት የዓለም መነጋገሪያ ስለሆነ ያ ተቀባይነት የግንቦት 7 የቤት ሥራ ሊሠራለት አይችልም። አንድ ማንነት ያለው የፖለቲካ ድርጅት ተጽዕኖ ፈጣሪ በመጣ ቁጥር ያን በመልቀም ስልት እና ስትራቴጂ አድርጎ ከወሰደው ጣሪያ የሌለው ቤት ነው የሚሆነው። 
ድርጅት ራስህ መሬት ቆፍርህ፤ መሰረት ጥለህ፤ ግድግዳ አቁመህ፤ ማገር አዋቅረህ፤ ባላ ሰርተህ፤ ምርጊት አሟልተህ፤ ናሱን አሳምረህ ገንብተህ ቆርቆሮ መትተህ በርና መስኮትህን አጠንክረህ፤ ግቢህን ማስጠበቅ ስትችል ነው ቤትህ ሊሆን የሚችለው። ከዚህ የተረፈው ግን አንዱን እንኳን ብትስት በአንድ አውሎ ሁሉም ሳይውል ቀትር ላይ „ጨዋታው ፈረስ ዳቦ ተቆረሰ“ ይሆናል። ማህል ላይም ከጥምረቱ ማግሥትም አቦ ሌንጮ ለታ ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር። የአመራር ድክመት አለብን ብለው። አሁን እስራኤል የምር ወዳጇ አሜሪካ ናት። አሜሪካ ትስራለኝ አለች ብላ የቤት ሥራዋን ካልሰራች እስራኤል አገራዊ ፋይዳው በከንቱነት ይወራረዳል። ተጨማሪ ነገሮች፤ ቅንጥብጣቢ ነገሮችን ዕለታዊ ክፍተቶችን ቢሸፍኑ እንጂ ለዘላቂ ለፖለቲካ ድርጅት አገነባብ እና አመርቂ አማራር ቋሚ ስክነታዊ ጉዞ ጸር እና አስናፊ፤ ትጥቅ አስፈቺ ደንቀራዎች ናቸው። መታመን በራስ ውስጥ በተሰራ የብቃት አቅም ብቻ ነው። በራስ ሃሳብ ውስጥ መዝለቅ። ለራስ ሃሳብ ሞጥሮ መትጋት።

በዚህ „በኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ልብ ገዝ፤ ህሊና ገዝ ፤መንፈስ ገዝ፤ አትኩሮት ገዝ፤ ፍቅር ገዝ፤ አብሮነት ገዝ፤ ማግስታዊ ጉዞ ላይ ከማነጣጠር ይልቅ ግንቦት 7 ቢያንስ ትኩረቱን በወያኔ ሃርነት ትግራይ ላይ አድርጎ ቢሆን ኖሮ፤ መልካም በሆነ ነበር። ቢያንስ የፖለቲካ ብስለት አቅሙን ምልከታ ብቃቱን፤ አሻግሮ የማዬት አቅሙን ማቆዬት በቻለ በነበረ። የቆዬውን አሻግሮ የመተንበይ አቅሙን ስስነት ረስተን ማለት ነው። አሁንም ቢያንስ ቢቀጥልም ባይቀጥልም ለራሱ ለታሪኩ መጠንቀቅ ይገባዋል። በእሱ ሥም የሌሉበት መከረኞች ሁሉ እንደ በግ ታርደዋል። የፍርድ ውሳኔ ተምልሶ የሚታዬው በቀነ ገደቡ ልክ ነው። ያ ካለፈ አለፈ ነው። በዛ ወቅት ይወጡ የነበሩ ጹሑፎች፤ መግለጫዎች፤ አንዲት ከዚህ ግባ የማትባል መረጃ ተንጠልጥላ የነበረው ትርምስምስ፤ አቀጣጣይ ለኮሽ ቅንጣቶች ጎልብተው ወጥተው ህውከት በመፈብረክ የነበረው ስንጥር ሁሉ ከአንድ ብሄራዊ አውራ ፓርቲ የአማራር ብሰለት ጋር መነጻጻር ቀርቶ ማጠጋጋት አይቻልም ነበር። አንድ የፖለቲካ የፓርቲ አባል መጀመሪያ የፓርቲውን ደረጃ በሙሉ የራሱ ሰብዕና ውስጥ አብነታዊ ማድረግ ግድ ይለዋል። ድርጅት የግጥምጥሞሾ የጭራሮ ቤት አይደለም። ውስጥን መዘርግፍ ግብ ሊሆን አይችልም። ያን የባከነውን ጊዜ መንፈስ ለመሰባሰብ በወል ቢሰራበት የተሻለ በነበረ።

ያ ሁሉ የዘማቻ ጹሑፍ ቢሰበሰብ እኮ ትግሉ ከወያኔ ሃርነት ጋር መሆኑ ቀርቶ አሁን የሰፊውን የኢትዮጵያ ህዝብ ካገኘው የትንፋሽ  ደስታ ጋር ከኦህዴድ ጋር ነበር ማለት ይቻላል። የውጮቹ አለቁና ወደ አዲሱ ተስፋ አንቴናው ዘለቀ። አሁን ባለው አገራዊ የለወጥ መንፈስ ላይ ጸሐፊዎቹን፤ ሃያሲዎቹን፤ ፕሮ ሚዲያዎችን፤ ራሱን እንደ ድርጅት ግንቦት 7 በወጥ መንፈስ መምራት ነበረበት እንደ አውራ ፓርቲነቱ ግን አልተቻለም። በአማራ ማንነት የህልውና ተጋድሎ ከወቅቱ ማህበራዊ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ባለመስማማት ምክንያት ያጣው የሥነ - ልቦና አቅም አልበቃ ብሎ አሁን በተገኘው አጋጣሚ ደግሞ ቀድሞ ለእኔ „አብይ ይሁን ለማ“ ሁለቱም እኩሎቼ ናቸው ባለው አቋሙ ላይ ጸንቶ ለመቆም እንኳን አልተቻለውም። አቅጣጫ የለሽ፤ አመራር የለሽ ሂደት፤ ብልሃት የከሳበት ተለዋዋጭ አቋም ነው እንደ ተለመደው የተስተዋለው። ቀደም ባለው ጊዜም ቢሆን በዘመነ ጥምረቱ ሌሎችም አሉኝ የሚላቸው ሁለት ድርጅቶች የአፋር እና የሲዳማው መልክዕ አቋማቸው ከአቦ ሌንጮ ለታ ከሚመሩት ድርጅት በእኩልነት አልነበረም። ሰፊውን የባለመብት ድርሻ የሰጠው ለአቦ ሌንጮ ለታ ፓርቲ ስለነበር፤ ለሌሎቹ ይሰጥ የነበረው አናሳነት ታክሎበት ለቀጣዩ ጊዜም ፈጣሪ ይሁነው ነው የሚባለው … የአመራር ክፍተት አለበት ድርጅቱ።
  • ·         ኧረ በህግ …
የአቦ ሌንጮ ለታ ፓርቲ የአቋም ለውጥ አደረገ ነው አሁን የለወጥ ታዳሚው የሚለው። የአቋም ለውጥ አላደረገም። ቀድሞም የነበረው አቋም ይሄው ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በዛ ሰቀቀን ውስጥ ሆኖ፣ ትንሽም ጭላንጭል በማይታይበት ሁኔታ ሆኖ እኮ በዛ አፋና ውስጥ እያለ እኮ ነው ወያኔ ሃርነት ትግሬ በደነደነው ልቦናው እያለ አብሬ እሰራለሁ ብሎ ኦዴግ ሄዶ አታስፈልገንም ስለተባለ ነበር ቦሌ ላይ የተመለሰው። አሁን ባለው ጤነኛ መንፈስ „የሚሻሻል“ ሲል ይደመጣል። ቅንጥ ነው ይሄ። በዛ ዱዳ ስርዓት እሳተፋለሁ ያለ የአሁኑማ ከገነትም በላይ ነው። ቅደም ሁኔታም አያስፈልገውም ዝም ብሎ መቀላቀል። የስለት ጊዜው ነው። ሻንጣውን አዘጋጅቶ ነበር የቆዬው። ሻንጣ ስል የመንፈሱንም ያካታል። ስምምነቱ እኮ ከዛ የአማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎ፤ ተጋድሎውን የደገፍው በሰማዕቱ አርበኛ ጎቤ የሚመራው የጎበዝ አላቆችን ጠላት አረበድብድ ሞገድ ግንቦት 7 „የነፃነት ሃይል“ ነው የምን የአማራ ተጋድሎ ብሎ ውሾን ያነሳ ውሾ፤ „አማራ መደራጀት አሁን አይገባውም። ትክክለኛ ጊዜ አልመረጠም፤ የአማራ መደራጀት ለኢትዮጵያ አደጋ ነው“ ወዘተ ብሎ ያን የመሰለ የምክንያታዊነት አበወራ አብዮት በጉልበት ሲነጥቅ፤ በተጨማሪም ግንቦት 7 በአውሮፓውም ህብረት ባለው የአንድ ሰው ሙሉ ድጋፍ ምክንያት የሚሊዮችን ልብ የገዛው የአርበኛ አትሌት ሊሊሳ ወርቃም ድንበር ዘለለ ድጋፍ ከሰማይ ዱብ ሲል አጋጣሚውን በጣምራ ለመጠቀም አቋራጭ መንገድ ነው ኦዴግ የተጠቀመው። ከዛ በኋዋላ በመላ አውሮፓ መልካቸው አንድም ቀን ታይተው የማይታወቁ ሦስት የኦነግ መሥራች ሊህቃን ክብር እና ግርማ ታዞላቸው በትእዛዝ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲሰግድ ተደርጎ፤ እንደ ታቦት ሲከበከቡ አዬን ሰማን። ፍቅር ያዝልቅ ብለን በቀና ተመለከትን። ወደዳችሁም ጠላችሁም የእኛ ዓርማ በኦሮምያ በዘለቄታ ዬእናንተው ሰንደቅ ዓለማ ግን ለድምጽ ይቀርባል ተባልን። ያልነውን አልን በወቅቱ።
የሆነ ሆኖ አቋራጩን መንገድ ለመጠቀም ነበር እንጂ ልቡ ያለው ሚሊዮኖችን ከኑሮ ያፈናቀለው ያ ጠንቀኛ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌሰቶ አባኮአቶ አማራን ያገለለ፤ የተጠዬፈ፤ የደቆሰ አብረው ካጸደቁት ህገ መንግሥት ላይ ነበር።
  • ·         ጉዳት እና ትርፍ ስለ ግንቦት 7።
ከጉዞ ኤርትራ ጋር ይሄ ሦስተኛው መሆኑ ነው። የመጀመሪያው የተዋጠው የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር በቀደመው ኔት ክስምት በትርፍ ላይ ግንቦት ሰባት መንበር ላይ ይገኛል። ያዝልቅለት¡ የጎንደር  ዕንባ ፈሶ አይቀርም! አሜሪካ፤ አውስትራልያ፤ ኒዮዘላንድ፤ ካናዳ ላይ ስንቶቹን እንዳጦፈ አለስተዋለውም። ሥሙንም ዓርማውንም ማዬት አይፈለጉም። „ያመናል!“ ነው የሚሉት።
ሁለተኛው ልቡ ተንጠልጥላ የነበረችው ለግንቦት 7 እስከ 20 ሺህ ሠራዊት ብቻ ሳይሆን ሙሉ ትጥቅ ያለው የአክሱማዊት ኪንግ ደም ህልመኛው የአቶ ሞላ አስገዶም ጥምረት ነበር። እሱ ገና ከመባቸው እሳት በለበሱ ውጪ ሐገር በሚኖሩ የትግራይ ሊሂቃን  የአስታራቂነት ክህሎት ከሸፈ። እንግዲህ የወልድያ የሰማዕታት ደም የተረገጠበትም ከዚህ መንፈስ የውለታ የቀጣይነት ተጠማኝነት መሻት ነው ብለን እናስባለን እኔ እና ብዕሬ።

አሁን ለሦስተኛ ጊዜ የልብ ቅርደዳው ለሰሚውም፣ ለደጋፊውም፣ ለፍታውራሪ ተስፋ ለሚባለው ቅን ጠበቂም ቢሆን ጥሩ የነበረው አብረው እንደሚሆን ቢሆኑ ነበር እነ የትንሳኤያችን በትረ ሙሴዎች አገር አድኖች። በዚህ ሂደት ግንቦት 7፣ ክብርት ወ/ሮ አና ጉምዝ፣ ኢሳት፤ በትልቁ የኤርትራ መንግሥት ከስረዋል። የተሰጠው የሽፋን ጊዜ፤ የተሰጠው የፖለቲካ ዕውቅና፤ የፈሰሰው ጉልበት እና መዋለ ንዋይ፤ የተሰጠው ቦታ ራሱ አንድ የሥ/ አስፈጻሚ ሰብሳቢነት፤ አንድ የተባባሪ ሊቀመንበርነት ነው። 

በሥነ - ልቦናም በፖለቲካ ትንተናም በሰጡት የብስለት ዕወቅና ልክ በኪሳራ ተወራርዷል። መቼስ ትንተና ወርዶ ፈጭ ብሏል ዘንድሮ። የፖለቲካ ትንተና ይባል ትንበያ ሁሉ 2018 አይሆኑ ነው የተሆነው። ቀይ ሲባል ጥቁር፤ ጥቁር ሲባል ቢጫ፤ አረንጓዴ ሲባል ቡኒ እዬሆነ ድብልቅልቁ ነው የወጣው። በእነ ሳጅን በረከት ስምዖን በጊዜያዊ ኮሜቴ የሚመራው ሰብር የውስጥ አዋቂ መረጃም ባላንባራስ አቦይ ስብሃትን ሳይቀር ማዕበሉ ጭጭ እያደረጋቸው ብቻ ሳይሆን የትናንቱ የባለቅኔው ጠ/ሚር የዶር አብይ ቢሮ የማያዋላዳ የአቅም ልቅና ቅኔ ቤት ያሰኛል።

በሌላ በኩል እነ አቦ ሌንጮ ለታ ከግንቦት 7 ጋር ሲጣመሩ በመንፈስ ሃብት ሲገቡም ባዶ እጃቸውን ነው ሲወጡም ባዶ እጃቸው ነው። ለግንቦት 7 ይዘውለት የገቡት ሥም ብቻ ነው „አገር አድን ንቅናቄ“ ሲቀጥል“ ትንሳኤ፤ ብርሃን ህይወትም እኛ ብቻ ነን“ ይህንም ትንሳዔ ከእናንተ አልጠብቅም ብላ ሥርጉታሻ ሞግታለች። በዬትኛው ፈንድ ራይዚንግ፤ በዬትኛው ዲሞ፤ በዬትኛው ህዝባዊ ስብሰባ፤ በዬትኛው ሚዲያ ለብሄራዊ ነጻነት የሚታገል አቅም አፍስሰው? የሚታገሉት ለዛው ለማኒፌስቷቸው ነው። ግንቦት 7 እራሱ ለዚህ ሁሉ ክብር እና ልዕልና ያደረሰው መጠን ያልገደበው አማራ ነው እንጂ ትግሬው፣ ኦሮሞው፣ አፋሩ፣ ሲዳማው፣ ከንባታው፣ ጉራጌው ወዘተ አይደለም። ያን ክብር እና ልዕልና ለአቦ ሌንጮ ለታ ድርጅት ተሸለመ፤ ኦሮሞ ንቅናቄም መዳፍ ላይ ለማስቀመጥ። የአማራ ተጋድሎ ተነጠቀ፤ የኦሮሞ ንቅናቄ ተንጎብሶ እጅ ተነሳለት፤ ምን እንዳርግላችሁ ተብሎም ተሰገደለት። አማራ በቅንነቱ ውስጥ ረቂቅ አቅሙ አምላኩ የማይረሳው መሆኑን ነው። መቼውንም ልዑል እግዚአብሄር አንደ ልቦናችን ንጽህና፤ እንደ ብርቱው ቅንነታችን፤ እንደ ለእናት አገራችን ስለምንሰጠው ትህትና፤ ንዑድ ልቦና ብሎ አይረሳንም። ፈጣሪያችን ከእኛ ጋር ነው።
  • ·         አቦ ሌንጮ ለታ እና የተሻለ ናፋቂው የኢትዮጵያ ህዝብ ምን እና ምን ናቸው?
አገር ቤት ብዙ ቃለ ምልልስ ሳዳምጥ በሌሎች ጉዳዮች ጭራሽ ምንም የማያወቁ ሰዎች አንዳሉ ሁሉ ነው የማስተውለው። ቂቅ ብለው ተላብሰው ግን ህሊና ላይ ምንም። ኑሮ የሚባለውን የማያውቁ ሁሉ አሉ። ትንሹን ቅንጣት ነገር እራሱ አያውቁም። ስለሆነም ሚዲያ ላይ ውጪ ሀገር የነበረው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ወስኖ ኢትዮጵያ ገባ ሲባል እንደ ገድል ሊያው ይችላል ህዝቡ። እነሱም ሚዲያ ላይ ጎራ፤ ኮራ ብለው በተለበጠ ብሄራዊ ስሜት የሚሉትን ይላሉ። እነሱ የሚፈልጉት ሚዲያ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብም ከመረጃ ውጪ ስለሆነ ደስታው ጣሪያ ሊነካ ይችላል። እኔ ሲቀላቀሉም አልሞቀኝም አሁንም አይሞቀኝም። ለአዬር ላይ ለሚዲያ ፕሮፖጋንዳ ትርፍ ሊሆን ይችላል። ለነጮችም እንዲሁ። ነገር ግን ይዘውለት የሚሄዱት የመንፈስም፤ የሃሳብም፤ የተሻለ ብሄራዊ ራዕይም የላቸውም። አዲስ የምሥራችም የለም። ራሳቸውን ይዘው ወጡ ራሳቸውን ይዘው ይመለሳሉ። ያን ሚሊዮን ተሰውቶበት ግን በከንቱ ብክነት ቃጠሎ ለበዬኑበት የኦሮም ህዝብም ኢትዮጵያዊነትን አጥብቆ የሚጸዬፈውን ዓርማ ብቻ ይዘውለት ይሄዳሉ እንጂ  ኢትዮጵያ ለጀመረችው አዲስ ብሄራዊ ቅን የሰብዕዊነት እና የተፈጥሯዊነት ህብራዊ የምህረት ጉዞ ግን በአቋሙ አንድም ቀን ጸንቶ የማያዋቅ ፓርቲ ለጉርብትናም አይበጅም እንኳንስ ከፍ ላለው ለሀገራዊ ራዕይ። ያው እንደ ሻብያም እንደ ወያኔም ኢትዮጵያን በጠላ መንፈስ … ቀጣዩ ይታያል። በዛ ላይ ግልጽነቱም ድፍን ነው። በአሶሳው ጭፍጨፋ ላይ የሰጡት አስተያዬት የሚገርም ነበር። ኤም አይደለም፤ ቢም አይደለም፤ እኛም አይደለነም፤ የሰማይ መላእክ ወርዶ ህጻናት በር ዘግቶ አነደደ ዓይነት ነው። እሳቸው የኖረውን ታሪክ መርሄ ሲሉ በእኛ ዘመን የተፈጸመውን ሽምጥጥ አድርገው ክደው ነው።

ስለሆነም ከ700 ሺሕ በላይ የመፈናቀል ጉዳት የደረሰበትን ህዝብ እየመሩ፤ ቁስላቸውን ቻል አድርገው በበዳዩ ቦታ ተገኝተው "የሁላችንም ውርዴት ነው" ያሉትን ድንቅ መሪን የአቦ ለማ መግርሳን መንፈስ ረቶ ለድል እእ። ራሱ ብሄራዊ መሪ ለመሆን አቅሙ የላቸውም። እዛው ካዘጋጇት ስኮዬር ኦሮምያ ውስጥ የተጣበቀ ርዕዮት ከማራማድ በስተቀር ዕድሉ የላቸውም። ብሄራዊ መሪዬ ለመባል እጅግ ይከብዳል። መሃል ሰፋሪ ፖለቲካ ለዬትኛውም ድርጅት አይጠቅምም። ለዬትኛውም ህዝባዊ ዕሳቤ ጠንቅ ነው። የፈለገው ዓይነት ይሁን ባሰበው ልክ በዛው ጸንቶ መታገል ያስከብራል። እንደ እስስት መገለባባጥ ግን ለዕለቱ ይሆናል ሰሞናዊ ነው። አሁን አቶ ሞለ አስገዶምን የት እንዳሉ፤ የት እንደ ወደቁ ማን ያነሳቸዋል? እኔም ያን ጊዜ ጽፌ ነበር ደግምን ሚደያ ላይ እንደ ማናያቸው። የሆነው ይሄው ነው። ኦህዴድ ከዚህ ድርጅት ጋር ጋብቻ ከፈጸመ በቅድሚያ ጥቁር ልብስ የምትለብሰው ሥርጉተ ሥላሴ ትሆናለች። ልክ አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ ሲታሰር ሁለት ወር እንደ ለበሰቸው። የአቦ ሌንጮ ለታ መንፈስ ብቻውን ሜዳ ተስጥቶት አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት መድረክ ማመቻችቱን ግን አልቃወምም። ይገባልም። 

ኦሮምያ አገሬ ላለ እዛው ተወዳድሮ በልኩ መጠኑን ማወራረድ ይችላል። የእኛ ኦህዴድ እኔ ለማውያን ነኝ ለማ መባቻዬ ነው፤ "መሃላ መሃላ ነው" አብይ የእኔ / የእኛ ነው፤ የሎሬቱ ታቦት ነው ላለችው ሥርጉተ ግን ቅልቅል ቢኖር የሞት ሞት ነው። ኦህዴድን ተውጦ ወደ ቀደመው እልቂት ወደ ቀደመው ፍርሻ እንደሚያመራ በእርግጠኝነት መናገር ግድ ይላል። የሶሻሊዘም ብክለት ተፈጥሮው እፉኝት ነው። ሲረገዝ አባቱን ሲወለድ እናቱን መግደል። ስለሆነም ኦህዴድ አደራችን እንዳይበላ በጽኑ አንክሮ በግልጽ ቋንቋ ልገልጽለት እሻለሁኝ። ብአዴንም የሰጠውን ሙሉ ክብር እና ልዕልና ለኦህዴድ በዚህ ቅድመ ሁኔታ ማዋዋል አለበት። የገዱ መንፈስ ከሥር ከሥር መከተል ሳይሆን በአቻነት አቦ ለማ መግርሳ ጋር ግልጽ ውይይት በማድረግ፤ ግልጽ አቋም ውሳኔ ላይ መድረስ አለበት - በፍጥነት። የገዱ መንፈስ ወደ ፈተና ራሱን መቀርቅር የለበትም። ለማንም ለምንም የሚሆን ድርጅት አይደለም። እንደ ሽንብራ ቂጣ ሲገላበጥ ነው የኖረው። የተጀመረውም ህብረት „በኦሮማራ“ ህመሙ ነው ከወያኔ ሃርነት ትግራይና ከሻብያ ባላነሰ።    
  • ·         ጥንግር ፋይዳ።
ኦነጋውያን ያ ሁሉ ሰው የተገበረበትን የረጅም ጊዜ ተጋድሎ ሜዳ ላይ ለበላህሰብ አስረክበው፤ ታጋዮችን ካለምንም መጠለያ በትነው ለጥቃት አጋልጠው፤ አባላት ካለምንም ጥግ ለቂመኞች ሸልመው፤ እነሱ አክተሮች ህይወታቸውን አትርፈው አሁንም በገብርዲን እና በከረባት ተኮፍሰው በቀይ ምንጣፍ ቢንጎባለሉ ከግለሰብ ክብር ባሻገር ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈይዱት አንዳችም የፖለቲካ ትርፍ በፍጹም የለም። ለዛ የሚሊውን ደም ለፈሰሰበት ተጋድሎም አልሆኑም። እስተዚህች ቀን ድረስ እኮ በእንሱ ሥም አሁንም እስራት፣ አሁንም መከራ፣ አሁንም ግርፋት አለ፣ በኦሮም ልጆች ላይ። እናመሰግናለን እንኳን ለቤተሰብ የለም። በዚህ ሁሉ ሂደት ነው  የኢትዮጵያ እናቶች ለሌሎች የሥም ዝና፤ ለሌሎች ውዳሴ ሁልጊዜ የሰው ብርንዶ ሲያቀርቡ እና ሲያመርቱ የኖሩት። አሁንም ነገ በለመደባቸው ምን ሊያመጡ እንደሚችሉ አይታወቅም። ልባቸው ንጹህ አይደለም። ጽናታቸው ራሱን ችሎ መቆም የተሳነው ከንቱ ነው። ለራሳቸው ድርጅት ደሙን ላፈሰሰው ህዝባቸው እንኳን አልሆኑም ጥለውት ነው የሄዱት። እስቲ ተመልሰው ደግሞ የሚያደርጉት ይታያል። ወርቅ ከሰማይ የሚያሳፍሱ ከሆነ። እንኳንስ ለኢትዮጵያ ህዝብ።  የኢትዮጵያ ህዝብማ ጠላታቸው ነው። የቄሮ ትውልድ እነሱን ብቻ አምልኮ በታሪኩ አፍሮ እና ተሸማቆ ከፌድራል ሃላፊነት ተገሎ፣ ከወገኖቹ ተለይቶ በበርሊን ግንብ ውስጥ ጥቁር ቀን እንዲቆጥር ያደረጉት እነሱው ናቸው። የነገረ አማራ ተከድኖ ይብሰል። የሚጠበቅ ፍርፋሪ የፍቅር ጠብታ አይኖርም። የሁለቱን ግንኙነት በተመለከት ሌላው ዳገት ነው። ተሞርዶ አይድንም። እንኳንስ እነሱ አንድ የኦሮሞ ልጅ ባሊህ ባላላቸው ጊዜ ከጎናቸው የነበርነውን ዛሬ የዘነጉን ፖለቲካዊ ሳይንቲስት „ዘመዶቻችሁ ነን ይሉናል ዕውነት ይሁን ሃሰት አናውቅም“ እስከ መባል ማድመጣችን ምን ያህል የልባችን ግድግዳ እንደ ሰነጠቀው ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያወቀው።

ይልቅ ይህ የእነ አቦ ሌንጮ ለታ ጉዞ የኦሮሞ ህዝብ ዛሬ ተስፋ የተጣለበት „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነውን“ ያቀዳጀውን ክብር ግርማ እና ሞገስ ለመቆራረጥ ይመቻቸው ይሆናል። ሶሻሊዝም የኢንትሪግ ፋፍሪካ ነው። ኦህዴድም ከተሰጠው ክብር ዝቅ ማለት ከጀመረ የራሱ ጉዳይ ነው። ክብሩ ኢትዮጵያ ብቻ ናት። ክብረቱ ያልተበረዘ ያልተከለሰ ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው! ብርሃኑ ደግሞ ለዚህ ቀን ያደረሰው ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማው የቀደምቱ ልሙጡ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ነው። ከቱርክ፤ ከፖርቹጊዝ፤ ከጣሊያን፤ ከሱዳን፤ ከሱማሌ ታድጎ ያቆዬለት አገሩን እሱ እንጂ የአቦ ለንጮ ለታ ምስል አይደለም። ይህ የታሪክ ክብር ስላከበረ ነው በገፍ ግርማ እና ሞገስ ያጎናጸፈው ኦህዴድን „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ብቻ እና ብቻ ነው። በዚህ ውስጥ አረንጓዴ ቢጫ እና ቀዩ ሰንደቁ ነው መሪው ነው የዘመኑ። 
  • ·         መቻልየለሽ።
አቦ ለማ መግርሳ እና ዶር አብይ እኮ ታች ሆነው እዬተሰለቁ ነው በችሎት፤ በእውቀት ልቅና እና በጥበብ እዚህ የደረሱት። አሁን እንዳደማጥኩት ከውስጥ ቃጠሎ አልፎ ብልዘቱ ውጭ እስኪታይ ድረስ አንድ ሊሂቅ እ! እ! እ! እያሉ ወንድ ልጆች እንደ ሴት አምጠው ነው በዛ በወጀብ እና በሞገድ ሁሉ አልፈው ለዚህ ቀን ሁላችንም ለብሥራት ዜና ያበቁን። ሸሽተው አይደለም። ጀግኖች ናቸው የጥምር ስብዕና! ይህም የሆነው እነሱ „ኦሮምያ“ እያሉ እነ አቦ ሌንጮ ለታ ሺህ ሚሊዮን ጊዜ ታሪክ እያሉ ልባችን ለሚያወልቁት የ43 ዓመቱ የአብርሃሙ በግ አማራ በከፈለው መስዋዕትነት ነው። ቀድሞ ነገር በግለሰብ ደረጃ የነበሩ ቅን ኢትዮጵውያን በዬትኛውም ማህበረሰብ ቢኖሩም 27 ዓመት ሙሉ አማራ የታረደበት፤ የቆሰለበት፤ የተሰደደበት ኢትዮጵያዊነት ነው ለዛሬ ቀን ያደረሰው። የ27 ዓመቱ የአማራ በማተቡ ጸንቶ መቆም ነው ለዚህ የምሥራች የትንሳኤ ቀን ያበቃው። ባለውለታ ነው አማራ እንደ ማህብረሰብ። ለዚህ ቀን ታላቁን ድርሻ የዋለው በርግጥም ቻዩ አማራ እንደ ማህበረስብ ነው።


አገር አለኝ ብሎ በዛም ጸንቶ ስድቡን፤ ግልምጫውን ዱላውን ወቃሳውን የባሩዱን ጭፍጨፋውን ችሎ እና ታግሶ በዬቀዬው ዒላም ሆኖ በባድማው ባልተወለዱት በነሳጅን በረከት ስምዖን በኢንስፔክትር አዲሱ ለገሰ እና በሌሎችም ተሰቅዞ ተይዞ ግን ያችን ቡኔ ሳይረሳ ስለሷ ታረደ። ካለ አንድ ዋቢ ጠበቃ እና ሁነኛ። ሁሉ በዬጎጆው ሆኖ የተሰጠውን የቤት ሥራ እዬሠራ፤ አዲስ ትውልድ ሲወጣበት እሱ ግን በመሞከሪያ ጣቢያው በቁርሾ በአማራ እርድ ላይ ነበር የተበተነች ኢትዮጵያ 26 ዓመት የጠበቃት እስከ መጋቢት 24. 2010 ድረስ። ሊንኩ ተወደደም ተጠላም ያ ቻይ እና መከረኛ የአማራ ያልበገረም  ድምጽ ነው። አሁንም ቢሆን እንመጣለን፤ ልናያችሁ እንወዳለን ሲባል ፈቅዶ - አንጥፎ - ጎዝጉዞ እልል ብሎ ኩልል ብሎ በደስታና በፍስሃ ወገኖቹን ተቀብሎ ብድግ ቁጭ ብሎ አስተናግዶ እስከ መጨረሻዋ ደም ጠብታ ድረስ ደሙን ገብሮ ዛሬ ኦህዴድ የድል ርካብ ላይ ደረሰ። ከዚህ ማህበረሰብ ጋር ያለው ቅዱስ መንፈስ የማይደፈር ነው ቢታወቅ ኖሮ። ወደፊትም ፈንገጥ ያለች መዛነፍ ሲመጣ ቅጣቱ የሰማይ ነው …
ለዛሬ እኛ የብርሃን ቀን ለምንለው „ለሞኞቹ የተስፋ ቀን“ የተደረሰው በቻዩ፣ በታጋሹ እና በድንቁ የአማራ ህዝብ የጀርባ አጥንትነት ነው። ኢትዮጵያዊነት እኮ የሚያስስር የሚያስገድል እና የሚያሰድድ ነው የነበረው።

የሆነ ሆኖ ከሎቢ አቅም እንኳን እነሱ አይደለም እኮ የደገፉት „ጣና ኬኛን የወጣቶችን ፤ አባይ ኬኛን የኦሮሞ ማህብረሰብን፤ ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው የውጥ መሪ ሞተር መርሁን፤ የአማራ እና የኦሮሞ ሙሁራን ኮንፍረንስ ሊንኩን OBN ሲሰራ የባጀውን ልዩ ዝግጅት“ የትኛውም ሚዲያ ይሆን በወጥነት የደገፈው፤ ማናቸውንም ቅንጣት መልካም ነገር እዬለቀመ ሲለጥፍ የነበረው አንድ የሳተናው ሚዲያ በቋሚነት ነው የነበረው። በፌስ ቡክም ቢሆን አብዛኛው አማራ ነው ሰፊ ድጋፍ እና ሽፋን የሰጠው። አቶ ለማ መግርሳ ብሎ ለመጥራት እንኳን ሚዲያቸው አቅም አልነበረውም። የዶር አብይ አህመድ እማ ተከድኖ ይብሰል። እቴጌ ኬኒያ ስለካሰች ያ ትንግርት ትዕይንት ሁሉንም እርቃኑን በመንፈስ አስቀርቶታል። ሁሉንም በልኩ ለክታላች ትባረክልኝ እንጂ እቴጌ ኬኒያ፤ ወደር የለሽ ፍቅሯንም በያለንበት ልካልንአለች። የራሷ ንጉስ ነበር ያደረገችው „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነውን።“ ደግሞ ጠ/ ሚር አብይ አህመድም አያሳፍሯትም። የኬንያ ሚዲያውም በጣምራ ተግቶላቸው ነበር። ወሸኔ የተሳካ ዘመቻ!
  • ·         ልብ ላለው።
በሌላ በኩል በመጀመሪያ ደረጃ የአቦ ሌንጮ ቡድን ዛሬ ትናንትም ሆነ ዛሬ“አገር አለኝ“ ብለው እንዲሄዱ ያደረጋቸው የክብር መቅድም ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማው ልሙጡ አረንጓዴ ብጪ ቀዩን ሰንደቃችን ብለው በወደቁ አርበኞቻችን እና በቀደሙ ብልህ መሪዎቻችን ብርታት እና ጀግንነት ነው። ድርጅታቸው እንደ ድርጅት እሳቸውም እንደ ግለሰብ በዚህ ላይ የጠነከረ ጥላቻ ነው ያላቸው። በአማርኛ ቋንቋ ላይም ቢሆን ቀደም ባለው ጊዜ ከአምስተርዳሙ ኢሳት ጋር በነበራቸው ቆይታ በእንግሊዘኛ ነበር ቃለ ምልልስ ያደረጉት። በሦስተኛ ደረጃ በአማራ እና በኦሮሞ ግንኙነት ላይ „ኦሮማራ“ መንፈስን ያፈለቀው ወጣት „በገበታ ሚደያ ቃለ ምልልስ“ ባለፈው ሰሞናት ሳዳምጠው የኦሮሞ አክቲቪስት አቶ አሚን ጁንዲ በኦሮማራ አብሮነት ላይ የኦነጋውያን ምሥራቾችን ሲያማክሯቸው „ያልበሰለ ነው፤ ያልተሸ፤ ገና ጥናት የሚያስፈልገው“ እንዳሉ ነበር ያዳመጥኩት። ውስጣቸው እንደተቋጠረ ነው። ዕምል አለበት። ለዚህ ያበቃቸው እኮ ለዚህች ቀን ያደረሳቸው የአማራ ሙሉ ታማኝ ድምጽ ነው። በምዕራቡ ዓለምም የተሠራው የሎቢ ሥራም አለበት ተክድኖ የተቀመጠ። የሆነ ሆኖ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ ህመማቸው ነው። ስለሆነም ብሄራዊ መሪ የመሆን አቅማቸው በዬለም የተባዛ ነው። ፍቅርን ፈሪ ናቸው። ስምምነትን ለቀን መዳረሻ ድልድይ ብቻ ነው የሚሹት። የቋጠሩት ጥቁር እንቆቆ የት ሊያደርሳቸው እንደሚችል የሚታይ ሲሆን ኦህዴድ ግን ልባችን በዳግማዊነት አቁስሎ ቀሪ ዕድሚያችን በመከፋት እንዳይቀረደድ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል። ይህን „መባቻን“ ስጽፍ አስገንዝቤዋለሁኝ። ኦህዴድ እንደ ተፈጥሮ እንዲቀጥል እሻለሁኝ። እነሱን በጥምረት ይሁን በውህደት ካስጠጋ ምስቅልቅል እንደሚል ሊያወቀው ይገባል።
  • ·         ተመስገን።
እጅግ ፈጣሪ የሚመሰገንበት ዛሬ እንደ 66ዎቹ ዘመን አማራ በአንድ እጅ የሚያጨበጭብ፤ በግማሽ ሹርባ የተሰራ፤ ወይንም በአንድ ጆሮ የሚያጌጥ የሚሆን አንድም የአማራ መንፈስ መሬት ላይ የለም። የአማራ ብሄርተኝነት በተገባው አቅምን ሁኔታ በተሟላ እድገት እና ደረጃ ይገኛል። ለዚህም እጅግ ደስ ብሎኛል። በውጭም በአገር ውስጥም ያለው ድባብ እና ድል ሙሉ ነው። ሁሉንም ዓይነት ፈተና ሲቀበል የኖረው አማራ ላይመለሰብት ግዞትን፣ አንገት መድፋትን፤ መሸማቀቅን፤ በስውር መጣቃትን፤ መናጆነትን፤ በፖለቲካ ማድረክ መገፋትን፤ አሽቀንጥሮ ጥሎ ቀና ብሎ ለመሄድ ከሚያስችለው የማንነት ተክለ ቁመና ላይ ይገኛል። ማነው እቴ እህ ጦማሪ ፈቃዱ በሃይሉ የአማራ ተጋድሎ „ከስሟል“ ሲል ነበር፤ እኔም ጽፌለት ነበር ተጋድሎው የሚሊዮን መንፈስ ውስጥ እንደ ከተመ። አሁን ያዬው ይመስለኛል። ሌላው ፖለቲከኛ ያልነበረው አማራ ሁሉ ከጎንደር ጎጃም የአማራ የህልዋና ተጋድሎ ጀምሮ ያለው ሙቀት የሚገርም ነው ውጪ ሀገር። በግድ አማራ ሁኑ ተብሎ 24 ዓመት ሙሉ አልተቻለም ነበር። አሁን ከጎንደሩ የአማራ የማንነት የህልውና አብዬት በኋዋላ በጥንግ ድርቡ ባለፍቅራዊነት የጀርባ አጥንት በጎጃም ዘመን በሚዘክረው የደም ዋጋ አማራነት በልጽጓል። ለምቷል። ፋፍቷል። በሙሉ ዕድሜ ላይ ያለው ሁሉ „ስውለድ አማራ፤ ስኖር አማራ፤ ስሞት አማራ ነኝ፤ በአማረነቴ ኮርቼአለሁኝ“ የሚባልበት ዘመን ላይ ነው። ይህ መንፈስ የፈለገ ዓይነት የአቦ ሌንጮ ለታ ሴራ እና ማናቸውም የቀውስ ፈተና ጥሶ የመውጣት አቅም አለው። ያ መሰል በሞኞች ክንድ ከእንግዲህ ተንብርክኮ በአማራ ደም የሚዛቅ ዝና የሥም ብጣቂ ቃርሚያ አይኖርም።
በፈለገው አይነት ስሌት የማፍረስ ተልዕኮ ይዞ ቢነሳ ራሱን ከማጣት በስተቀር እድል አይኖረውም፤ ማንኛውም ድርጅት።

የአማራ ሙሁራን መሬት ላይ መሆን የሚገባቸውን ያህል ወደ ራሳቸው በሚገርም ፍጥነት ተመልስዋል። እኔም ስል የነበረው ይሄንኑ ነው በፍጥነት ወደ እራስ መመለስ። መፍትሄው ይሄው ብቻ ነው። ለነገም የአማራ ትውልድ ቀጣይነት ላልተጸነሱት ሳይቀር ተጋድሎው በስልት እና በተደራጀ ሁኔታ የመንፈስ ድልድዩን በጽኑ መሰረት ላይ ይገነባል። አሁን በግራ በቀኝ በአሉታዊነት የሚያጣድፍ የአብይ መንፈስ ስለሆነ ነው በዛ ላይ እርብርቡ እንጂ አማራን በሚመለከት ልንማረው የሚገባ ማንነት ስለሆነ ፊደሉ ይቆጠራል፤ አቡጊዳው ይከተላል፤ መልዕክተ ዮሖንሱ ይሰለሰል፤ በዳዊት ምስክባክ ይቀጥላል፤ ከዛ ቅኔ በቤቱ ይዘረጋል ይዘረፋል፤ ድጓው እንዲያ እያለ ይቀጥላል በዜማ በአቋቋም በወረብ በዝማሬ …  ስለዚህ የአቦ ሌንጮ ለታ ኢትዮጵያ መግባት ለኦህዴድ ስጋት ቢሆን እንጂ ለአማራ ፈጽሞ አይሆንም። የሰበሰበውን ቅን መንፈስ ትቢያ እንዳይለብስ „ይቺ ጠይም አፈር“ የብላቴ ሎሬት ጸጋዬ መንፈስ ታቦት እንዳይደፈር ተግቶ መሥራት ይኖርበታል ኦህዴድ። ለነገሩ የምዕቱ ባለቅኔ አቦ ለማ መግርሳ ግንዱ እዛው ስላሉ ብዙም አያሰጋኝም። እንደ ዓይኔ ብሌን የምመለከተው ድርጅት ስለሆነ ነው ማስታወስ ብቻ ነው የፈለግኩት። በተረፈ ከፍርሻ በመለስ ኦሮምያ እንኳንስ ለራሷ ልጆች ለሌሎችም ጎረቤት አገሮች ትተርፋለች ስላሉ ባለቅኔው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ቦታው ከበቂ በላይ ነው … እንዳሻቸው መስገር ይችላሉ እነ አቦ ሌንጮ ለታ ሆኖ እና አቦ ሌንጮ ባቲ ያው ስስት በሚሉላት „ኦሮምያ ጨፌ“
  • ·         አቋሜ!
ያው እኔ „የሽግግር መንግሥት የአደራ መንግሥት" ምንትሶ ቅብጥርሶ የሚለው አይመቸኝም። በመንፈስ እንኳን የተደራጀ ይሄ ነው የሚባል የለም። ወኔ አገር አይመራም። ተመከሮ ነው አገርን መምራት የሚችለው። እኔ በጠ/ ሚር ደረጃ ከጠብቅኩት በላይ አገሬ ኢትዮጵያ በቃሽ ብሏታል። ዕድሜውን ያርዝምልኝ እንጂ ከጠበቅኩት በላይ የልቤን መሠረት ሰጥቶኛል ልዑል እግዚአብሄር። እኔ እምሻው ንጹህ ሥርዓት እንዲዘረጋ ነው። ነፃ ምርጫ እንዲኖር ነው። ነፃ የምርጫ ቦርድ እንዲኖር፤ የጸጥታ ሃይሉ ሚዲያው ፍትህ ተቋማት ሲቢክስ ድርጅቶች ገለልተኛ ሆነው ህዝቡ በነጻነት የፈለገውን መምረጥ ይችል ዘንድ ሁኔታው እንዲመቻች ብቻ ነው የምሻው እንጂ የጨበራ ተዝካር ሁኖ አሁን የተጀመሩ መልካም ጅምሮች እንዲጨናገፉ በፍጹም አልሻም። የጸጥታ ሃይሉ ወደ ምሽጉ ተመልሶ የኢትዮጵያ ህዝብ ካለስጋት እንዲኖር፤ በዬቢሮው፤ በዬመንደሩ ያለው የስለላ መረብ ሁሉ ብጥስጥስ ብሎ የህዝቤ የውስጥ ሰላም እንዲጠበቅ ነው። በሌላ በኩል ነፃ ሚዲያ ሊጠነክሩ የሚገባቸውን እያበረታቱ ግድፈቶችን ካለምንም መሳቀቅ የሚገልጹበት የመተንፈሻ  ቧንቧ ነው። በጠ/ ሚር ደረጃ አቅም ያለውም ሰው ከለማ መንፈስ እና ከአብይ መንፈስ የሚደርስ እኔ እንጃ በሞራላዊ ሰብዕና ደረጃ እንደ ግለሰብ ልይ ከተባለ ሊሆን ይችል ይሆናል። በሁለገብ የአቅም የፋፋ ተመክሮ ግን እነኝህ ሁለት ወጣቶች ረቂቅ ናቸው።


የሆነ ሆኖ ቅኖች ማስተዋል ያለባቸው እጅግ በርካታ የማናውቃቸው አጀንዳዎች ሁሉ መኖራቸውን ነው። ፍርሻ ጠረናቸው የሆነ ለሁላችንም ሳይሆን የተገበረው መስዋዕትነት ፈሶ እንዲቀር ያደቡ የጉም ዝግኖች አሉ። በሌላ በኩል አፍርሶ መገንባት ከዜሮ ጀምሮ መዳከርም ኢትዮጵያ ላይ ከእንግዲህ ማብቃት አለበት። ይሄ የሁላችንም አጀንዳ ሊሆን ይገባል። ሊፈርስ የሚገባው ነገር ሲኖርም ተጠንቶ በሚገባ ተመርምሮ እንጂ በዘመቻ ፍርሻ እና ንደት፤ የሰው ሃይል የመዋለ ንዋይ፤ የጊዜ፤ የትውልድ ብክንት ከእንግዲህ ማብቃት አለበት። ስንት ጊዜ በገፍ እንሰደድ። ስደት እኮ ሽርሽር አይደለም። ስደት የመከራ ስጦታ ነው። ለዚህም የጠ/ ሚሩ ቢሮ መልካም ጅምር ላይ ነው። ዛሬ ያደጉ፤ የበለጸጉ ሀገሮች በዚህ መስመር ስለቀጠሉ እርሿቸውን ስላማያሰፍረሱ እንዲያውም ለቱሪዝም ይጠቀሙበታል፤ በነባሩ መልካም መሰረቶች ላይ አንደ ዘመኑ አጠናክረው ስለሚቀጥሉ ነው ማደግ የቻሉት። እኛ  ከእንግዲህ የወገንን አጽም ይዞ በዬዘመኑ መዞር ሊያሸማቀቅን ይገባል። ስለዚህ ከሥነ - ልቦና ጀምሮ ያለው ብክንት በቋሚነት መታነጽ እንጂ ንደት ሊኖርበት አይገባም። የህሊና ላውንደሪ ያስፈልገናል። እኔ ይሄንን በጉልበተኞች ታግዶ የተቀመጠውን 7ኛ መጸሐፌ „ርግብ በር“ መግቢያው ላይ በሚገባ በአጽህኖት ጽፌያዋለሁኝ። ማፈረስ እኮ አንድ ግሪደር እና አንድ ሹፌር በተወሰነች ደቂቃ ሊተገብረው ይችላል። መገንባት ግን የሂደት፤ የማህበረሰብ የወል ውጤት ነው። ለዛውም ደም የተገበረበት ከሆነ ደግሞ ዋጋው ከፍ ያለ ነው። ማፍረስ ሆነ ማቃጠል ጀግንነትም ጤነኝነትም አይደለም። ለእኔ እንዲያውም የታሪክ ስርቆት፤ የትውፊት ጸርነት ይመስለኛል። የእኛ ነገር የቀደመውን ታሪክ እና ትውልድ አርክስን የአሁንኑም እናፍርስ ነው … ተደግሞብናል።
  • ·         ስለዕምነት እና ቆቆር ዕጣው። 
የኔዎቹ … በጣም ከትክት ብዬ የሳቅኩት ደግሞ እስቲ ላወጋችሁ። አቦ ሌንጮ ለታ እና አጋራቸው አፍሪካ ላይ የታደሙበት ጉባኤ ነበር። እናም አገራዊ ንቅናቄው ከኢሳት ጋር በወል በነበራው ቆይታ ከጥምረቱ ተለይታችሁ አንዳንድ እንቅስቃሴ እያደረጋችሁ ነው የሚል ጥያቄ ሲያነሳባቸው እነሱ አትነካኩን፤ እንዳሻችን እንድንሆን ነፃነታችን አትጋፉ አይነት፤ ጥያቄው ኮሰኮሳቸው፤ ውይይት ላይ ግንቦት 7 ደግሞ አምነዋለሁ ጓዴን ብሎ ማህተሙን ገጭ ሲያደርገው፤ በቃ ጣሪያው እስኪነቃናቅ ነበር የሳቅኩት። ቤት የሚያደባልቅ ሳቅ በሁለት ዓመት አንድ ጊዜ ይከሰትብኛል። በዕውን ይህ የፖለቲካ ብልህነት ቁመናው የት ነው ያለኸውም አስብሎኛል በወቅቱ። ያስብላልም። በፖለቲካ ህይወት እኮ ሰው የሚገመገመው አንተን ስለተቀበለህ ብቻ አይደለም። ቀድሞ ነገር ቢተማማኑ እማ ከሦስት ሰብሳቢነት አንድ ሰብሳቢ ይኖራቸው ነበር። ብቻ መታመኑንም ማመኑንም አይነው። አሁን የአቦ ለማ መግርሳ ይሁን የጠ/ ሚር ቢሮ እንደ ትልቅ የፖለቲካ ትርፍ ባዬዬው መልካም ነው። ግን ለጡሮታ ጊዜም ቢሆን ሐገሬ ወደ ሚሉት ኦሮምያ እንኳን አበቃችሁ ከሆነ አቀባባሉ መልካም ነው። በስተቀር ግን ልብ የሚጣልባቸው፤ አዲስ ሃሳብ አፍልቀው „ ከኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ በላይ የሚመጥን አቅም አምጠው ወልደው፤ ለዛው ለሚመኩበት ኦሮምያ ይሆናሉ ብዬ አላስብም። እሰከ አሁንም አላደረጉት ወደፊትም እንዲሁ።
ኦህዴድ አቅም የለውም የሚሉ እንዳሉ እስማለሁኝ። አቅም የሌለውማ አዛው ዶክኮ ነው የቀረው። አቅሙ ነው የሚሊዮኖችን ልብ ገዝቶ ገበርም ሸማማ ዘሃም ፈትልም የሆነው። ብሄራዊ መሪዬ ተባለ እኮ። 

ኦህዴድ እኮ የጎሳ ድርጅት ሆኖ ነው ይህን ያህል ከሊቅ አስከ ደቂቅ ያለውን መንፈስ በርስትነት የተሸለመው። ሚሊዮን መንፈስ ምራኝ ንዳኝ ግዛኝ ብሎታል። ቀረህ የሚባል፤ ጎደለው የሚባል የአቅም ስስነት እኔ በግሌ አላዬሁበትም። ከሥጦታም ከሽልማትም ከጸጋም በላይ ነው። በዛ ላይ ግሎባሉን ዓለም ለማዬት የሚያስችል ሙያዊ የሆነ አቅም ብቻ ሳይሆን ከደህንነት ጋር በሲቢሉም ይሁን በሚሊተሪው ይህንም ቀደም ብዬ ዘርዘር አድርጌ ስርቼበታለሁ አንቱ ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያ ለብሄራዊ ደህንነቷ ጥብቅ መሰረት አላት።  
መሬት ያያዘ አቅም ነው ያለው ኦህዴድ። ባንዘናጋ ጥሩ ነው። በህብራዊነት ሆኖ ኢትዮጵያን ለመምራት ብልህ ብቁ አቅም አለው፤ ብልሃቱም፤ ስልቱም ከሙሉ ሥነ - ምግባር፤ ከእውቀት ጋር፤ ከበቃ የጥበብ ተስጥዖ ጋር ነው፤ በዛ ላይ ለስላሳ ትሁት ነው፤ እስከ አሁን ባሳዬው ትጋት ግልጥ ነው። ይልቅ ራስን ማደራጀት ይጠይቃል። አንድ ቢሮ ፋይል አደራጅቶ ለመመራት አለመቻል እና በህብራዊነት ውጥንቅጡ የወጣን የሚሊዮን ፍላጎት መልክ አስይዞ ሀገርን መምራት የማይገናኝ ስሜንና እና ደቡብ ፖሎች ናቸው።
  • ·         መከወኛዬ የኢሳቱ ጋዜጠኛ የጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም አጭር ጹሑፍ ይሆናል።
እንዴት ነህ ቂም አያወቁ። ደህና ነህ ወይ አባ ዝምታ። ፖለቲካ እንዳልከው ትርፍ እና ኪሳራ ቢሆን ስታትርፍ በልኩ ከሆነ ስትከስርም በልኩ ለማመጣጠን አይቸግርም። ዓመት ሳይሞላ „ህይወት እና ትንሳኤነት“ ይሄ ዱብ ዕዳ ሲመጣ በአገነንከው ልክ የፖለቲካው ሙቀት ቁልቁል ይወርዳል። በአቶ ሞላ አስገዶሙ ደምሂት ጋር በነበረውም የሰራዊት ቀጣይ የአገነባብ የችኮላ ንድፍ ትልም እና የአሁኑ የሽግግር መንግሥትነት የሰነድ መሰናዶ ዓለምአቀፍ ተቀባይነቱ ስትመዝነው አሁን የአቦ ሌንጮ ለታ ፓርቲ የወሰደው እርምጃ እኔ በግሌ፤ ብጠብቀውም ጽፌበታለሁም ብዙ ተስፋ ያደረጉ ቅኖችን ግን ልባቸው በቀጥታ ተሰባሪ ይሆናል። ለዛውም ወቅቱን እዬው ኢትዮጵያ እኮ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ሆና ነው አንገባለን አገር የሚሉት። ፖለቲካ ትርፉ መቅደም ነው ዳታ አለማብዛት።
አቻየለሹ ውጭ ሐገር ያለው አስተማማኝ የወያኔ አባወራ ተደራዳሪ እኮ ነው የወለቀው፤ መንገድ ላይ የቀረው። 

የቄሮ ትግልም አለንበት በተባለ በBBC ጉልበታም ሙግት ማግስት ይህ ሲመጣ ያንቀጠቅጣል። አንተ ራስህ ስታገኘው ደስ ብሎህ ፏ ብለህ ዜና የምትሰራውን ያህል ይህን መርዶ ለመሥራት „እንኳንም ሆንክ“ መቼም አትለውም። ዕውነቱ ይሄ ነው። ደግሞም መራራ ነው። በዚህ ሙግትም የጠፋው ጊዜ፤ መንፈስ እሰበው። የተከመረውን ተስፋ እሰበው፤ ያ ሁሉ ነው የታናደው። በዬጊዜው በሚደርሰው በተስፋ ስበራት እንኩት የሚለውን የተስፋን ሥነ - ልቦና ለካው። ከቅንጅት መራራ ስንብት በኋዋላ ግንቦት 7 ወደ መድረክ ቀና አድርጎ ለማምጣት ሁላችንም ደክምንበታል መቼም ይሉኝታ የሚባል ባይሰራለትም። ፖለቲካ አትራፊና አክሳሪም ቢሆንም ስታገኘው በልክ መያዝ ይገባል፤ ሊሆንም ላይሆንም፤ አብረን ልንቀጥልም ላንቀጥልም እንችላልን ማለት ሲገባ ያደረጉ ቢያደርጉ አምናቸዋለሁ ብለህ ፊርማህን ካተምክ በኋዋላ ማህል ቤት ይህ ሲመጣ የፖለቲካ ሙሉ አቅም ሁሉ ሊፈተሽ ግድ ይለዋል። የፖለቲካ የብስለትህ ጮርንቃነት፤ ጎልማሳነት፤ አዛውንትነት ሁሉ እንዲበረበር ግድ ይላል። ኢትዮጵያን ያህል የችግሯ መጠን ከልክ ያለፈ፤ የታሪኳ ማህደር ህብር የሆነ ህዝብ የሚኖርባት ምድር፤ በዓለም አቀፍ ይሁን አህጉር አቅፍ ያላት ተቀባይነት ደግሞ የዚያኑ ያህል የከበረች አገር ለመምራት ብቸኛ አማራጭ ሆነህ ቆይተህ አሁን ሲሟሽሽ ቀላል አይደለም። ምርጫ ላይ ብትሆንም እኮ በዚህው ተክለ ቁመናህ ልክ ነው የምትለካው።

ስንት ጊዜ ደጋፊው አንገት ይድፋ? ስንት ጊዜ ቀዶ ጥገና ይደረግ? ስንት ጊዜ ሰንጥሩ ይደፈን? ይህን እሰበው። ቀጣዩስ ህልውናው እንዲህ በግራና በቀኝ ተወጥሮ ያን ያህል ቅራኔ የባጀበት ድርጅት ተክለ ቁመናንም ውስጡን ራስህን አግልለህ ተመልከተው። ለማትረፍ ስተደራደር ለዕለታዊ መሆን አይገባውም። ዘላቂ ሰብዕናህን በመገንባት ነው መጀመር ያለበህ። መረጃው እያለህ፤ እያወቅክ ያን ያህል መለጠጥ የተገባም አልነበረም፤ ያን ያህል ተስፋ መጣልም የተገባ አይደለም፤ ያን ያህል እርግጠኛ መሆንም የተገባ አልነበረም። ሰው ስንት ጊዜ ይውደቅ? በዬዘመኑ ፔናሊቲ ይሰጣል ሁልጊዜም መሳት፤ ችግሩ የት ነው ያለው? ካሰልጣኙ ነው ወይንስ ከሰልጣኙ? ወይንስ ከዳኛው ጊዜ? ስለምን ይህ ሊሆን ቻለ? ምንስ ጎድሎ ነው? ብለህ እንደ ጋዜጠኛ ስሜትህን ዋጥ አድርገህ ከራስህ አርቀህ ውስጥህን መፈተሽ ቤትህ አንዲገባህ ማደረግ ይገባል። መውደቅ በባዛ ቁጥር ቀዳዳ ወትፈህ አትዘልቀውም፤ ቀጣዩ በመንፈስ መሰረዝም ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ያስፈልጋል። 

„ትእግሰት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል“ ብዬ የዛሬ ሁለት አመት ግድም ጽፌ ነበር። አሁን ትናንት አንጠራርተህ ላይ ያንጠለጠልከውን አውርጄ በቅጽበት እፈጠፍጠዋለህ ብትልም አይቻልም። የህዝብ መታምን በአንድ ምሽት እንዳለገነባኸው ሁሉ እነሱንም ከተረሱበት መዛቸሁ፤ ያዋጣናል ባላችሁት ማእድ ሁሉ ከፍ አድርጋችሁ መንበር አሰረከባችሁ፤ የረገጣችሁትን ረግጣችሁ፤ ያገለላችሁን አግላችሁ አሁን ይሄ ሲሆን በቀላል ቆራጣ ራፖር የሚለሰን አይሆንም። ፋክት ፋክት ነው። ይልቅ የሚያስረሳ አምጣ የነበረው ጸሎት ደርሷል። አሁን ከባለቅኔው ጠ/ ሚር ወረድ ተብሎ ይኼው ይሳሳል፤ ይባዘታል … 
እስቲ አዲሱ ጥሎ ሄጅ እንዳይኖር ብልህነት ይሰነቅ …  

በተረፈ የኔዎቹ የኼው ነው የዕለቱ ዕይታዬ በሚኖራችሁ ጊዜ ሁሉ kenebete (ቀንበጥ) ብትጎበኙ በህሊና ሃዲድ መገናኛው መስመር የመንፈስ ይሆናል። ለነበረን ልልስል ያለ ዘንጣፋ ዝቀሽ ጊዜ ዝቅ ብዬ ኑሩልኝ ሸልሜ ልሰናበታችሁ ወደድኩኝ።

ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው ከሚስጥሩ የተነሳ አራት አይናማው መንገዳችን ነው!
ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።