ልጥፎች

ከኤፕሪል 1, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#የስብሰባ ባለሪከርዱ የአቤቱ ህወሃት የእግር #ጥፍር ጉዞ፤ ጫፍ - ለጫፍ! አፋፍ - ላፋፍ።

ምስል
  #የስብሰባ ባለሪከርዱ የአቤቱ ህወሃት የእግር #ጥፍር ጉዞ፤ ጫፍ - ለጫፍ! አፋፍ - ላፋፍ።   "ህግ ተላላፊወችን ጠላሁኝ።"       #መቅድም ።   መሸነፍን መቀበል ማሸነፍም ነው። በመሸነፍ ውስጥ የማሸነፍ ብልህነትም አለ። እልህ ጥበብ አይደለም። እልህ ስልትም መሆን አይችልም። እልህ ስትራቴጅ እና ታክቲክ ሊሆንም አይችልም። እልህ ልቅናም አይደለም። እልህ ልዕልናም አይደለም። እልህ ዊዝደምም አይደለም። እልህ ለዬትኛውም ፖለቲካ ድርጅት ዓላማ የግብ መዳረሻ ምርኩዝ መሆንም አይችልም። እልህ ገረጭራጫ ግራጫማ፦ ኮቴ የለሽ #የሲቃ ወኔ ነው።   #እፍታ ።   ህወሃትን በሚመለከት መንበረ ሥልጣኑን ፈቅዶ ከለቀቀ በኋላ ሞግቼው አላውቅም። ከዚህ በላይ ከህወሃት እምጠብቀው ቁልፍ አመክንዮ አልነበረኝምና። በዚህ አቅሙ እና ብቃቱም አመሰግነዋለሁኝ። ለምንጊዜም። የተቀበለውን መልሶ ፍልስልስ ቢያደርገውም ቅሉ። ትርፍና ኪሳራውን የመመዘኛ ዳታ ባልሠራም በወቅቱ ሊገጥም ይችል ከነበረ ውስብስብ ችግር የመፍትሄ አካልነቱን ህወሃት በድርጊት አስከብሯል ብዬ አምናለሁኝ። መደበኛ የፕሮፖጋንዳ ተግባራቸው ህወሃት ብቻ ለነበሩ የአዲሱ አመራር የአብይዝም ደጋፊወች እራሱ አዝንላቸው ነበር። ስለሚያባክኑት ጊዜ።    በሌላ በኩል እላፊ በሄዱ ንግግሮች እና ፋክክሮችን ተከትሎ ለመጣው ፍጥጫ፦ በጦርነቱ ዋዜማም ጦርነቱ #ሊያዋጣ እንደማይችል አበክሬ በተከታታይ ሞግቻለሁኝ። ጦርነቱንም ፊት ለፊት ወጥቼ አውግዣለሁኝ። ጉዳቱን ብቻ የዓለም ዓቀፍ ሚዲያ ተቋማት የሚሰጡትን መረጃ ተመርኩዤ በሃዘን ውስጥ ሆኜ ስዘግብ ነበር።    በሌላ በኩል ህወሃት ትንፋሽ አግኝቶ ከጫካ ወደ መቀሌ ከተመለሰ በኋላ፤ ...

#ዕውነት #ጋራጅ #አያስፈልገውም!

  #ዕውነት #ጋራጅ #አያስፈልገውም ! ሥርጉትሻ 2025/03/31  ዕውነት የሚታይ - የሚጨበጥ - የሚዳሰስ - ከልብ የሚደመጥ- ሲውጡት ለተሟላ ጤና ቅዱስ መድህን የሆነ፤ አሉታዊ ሆነ አወንታዊ ፕሮፖጋንዲስት የማይቀጥር፤ እራሱን ችሎ መቆም የሚችል፤ የራሱ እንደራሴ፦ #የማይዝግ - #የማይወይብ - #የማይጠነዝል - #የማይዝል ፤ #የክት እና #የዘወትር የሌለው፤ #የማይጎሽ - #የማይስረከረክ ፤ #ያልጎረና - #የማያጎራ ፤ #የማይኩረፈረፍ - #የማያጎፍር ፤ የማያብል - #ያላመለ ፤ ያማይከስል - የማያስከስል፤ ያላነከሰ - የማይጎብጥም ቀጥ ያለ ቀጥተኛ፤ የማይለዋወጥ፤ የማይረሳ - የማያዘናጋ፤ የማያዳልጠው፤ የፋክት ጉልላት፤ አድሮ የሚገኝ የውል - የኪዳን - #ምስባክ ፤ በልኩ - ለልኩ የተፈጠረ ጠፈፍ ያለ የነጠረ ሰማያዊ ፀጋ፤ ምሩቅ የተፈጥሮ ልዩ ፍጹማዊ ክስተት ነው። ሥርጉትሻ 2025/01/04