#የጨመተው ደቡብ እና ስኬቱ። • እቴጌ ጎንደር ሆይ! ከዚህ የብልህነት #ልዕልና ምን ተማርሽ?
• #የጨመተው ደቡብ እና ስኬቱ። • እቴጌ ጎንደር ሆይ! ከዚህ የብልህነት #ልዕልና ምን ተማርሽ? #ምዕራፍ ፲፯ "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። #መቅድም ። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ክስተታዊ ውሳኔ የወሰነ የፖለቲካ ኢሊት የሚገኝበት የደቡብ ክልል ነው። የቀድሞው ጠቅላይ ሚር አቶ ኃይለማርያም ደስአለኝ ብዙወቹ ቁምጥ የሚሉለትን የ፬ ኪሎ የክብር፤ የማዕረግ ሥልጣን፤ የጠቅላይ ሚኒስተርነትን ቦታ በፈቃዳቸው የለቀቁ ታላቅ ሰው ናቸው። የተከበሩ አቶ ኃይለማርያም ደስአለኝ ለትውልዱ የፖለቲካ ሥልጣን ማለት ከህዝብ ፍላጎት በላይ እንዳልሆነ ተቋም፤ ሐዋርያ ሆነው በተግባር አሳይተዋል። አብነትም ናቸው። በዘመናቸው ለአጎደለቱ፤ ለጠቀሙት ጉዳይ ዘመን የሚፈታው አመክንዮ ነው። እኔ እራሴ ብርቱ ሞጋቻቸው ነበርኩኝ። አቶ ኃይለማርያም ደስአለኝ በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን ካለምንም ቅድመ ሁኔታ መልቀቃቸ ግን የሚያሸልም የልዩ የታሪክ ክስተት መሥራች ናቸው። #የደቡብ ህዝብ። የደቡብ ህዝብ ለስላሳ ህዝብ ይመስለኛል። የደቡብ ህዝብ የማይቸኩል ዝግ ያለም ይመስለኛል። የደቡብ ህዝብ ያስተዋለም ይመስለኛል። የደቡብ ህዝብ #ዕድሉን #የማያፈስ ይመስለኛል። ይመስለኛል እምለው ኑሬ ስላላየሁት፤ በጥናትም መረጃውን በዳታ ሰለአላቀነባበርኩት ነው። በኮርስ፤ በሥራ ዓለም ግን ደቡቦችን በተወሰነ ደረጃ አውቃቸዋለሁኝ። ለዚህም ነው #የጨመተ የሚለውን ኃይለ ቃል የተጠቀምኩት። የደቡብ ህዝብ ኢሊቶች ህዝባቸውን #በመገበር አይታወቁም። የደቡብ ህዝብ የፖለቲካ ኢሊቶች የህዝባቸው የውስጥ ሰላም እንዲታወክ አይፈቅዱም። ይልቁንም መሻታቸውን፤ የት...