ክፋነት ስለምን ዓለምን ገዛት? ለምን? ክፋትን ጭካኔን የሚቋቋም ተቋም ለመገንባት ሃሳቡም ስሌላት።
ክፋነት ስለምን ዓለምን ገዛት? ለምን? ክፋትን ጭካኔን የሚቋቋም ተቋም ለመገንባት ሃሳቡም ስሌላት። "ጥበብን አግኝ ማስተዋልን አግኝ አትርሳም፦ ልጄ ሆይ ከአፌ ቃል ፈቀቅ አትበል፦ አትተዋት ትደግፍህማለች" ምሳሌ ምዕራፍ ( ፬ ቁጥር ፭) ክፋነት ዓለምን እያስተዳደረ ነው። ጭካኔም ዓለምን እዬናጣት ነው። ምክንያቱን ለዘጠኝ ዓመታት ያህል መረመርኩት። የመፍትሄ ሃሳቡን እንደመጣልኝ #ለተመድ እና #ለአውሮፓ ህብረት ላኩኝ። የተከበሩት ተቋማት አክብረው መልስ ሰጡኝ። ግን ምንም አክሽን የለም። 10 ፖስተር አሰርቼ መለጠፍ ፈለግሁኝ። ግን ፕሮፌሽናሎች ቢሠሩት ብዬ አማከርኳቸው። ሽልንጉ እናቴ በምን አንጀቴ። ከዛ አንድ ቀን ዩቱብ ቻናል ከፈትኩኝ። እንዴት እንደሚሠራ አላውቅም። ባለሙያ እንዲያግዘኝ ጠዬኩኝ። ሲዊዝሻ ላይ ባለሙያ ውድ ሆነ። በቃ ዋናው የቃላት ፖስተር መሥራት ነው። እኔ ሳልፍ አንድ ቅን ሰው ዓለምን ሞግቶ ዕውን እንዲያደርገው ነበር ሃሳቡ። በቃ አዌርነስ መፍጠር። የፍቅር ተፈጥሮ ካሪክለም ተነድፎለት ልክ እንደ ማህበራዊ ሳይንስ እና የተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ትምርት ይሆን ዘንድ ነው ሙግቴ። መነሻዬ አንድ ጀርመናዊ ወጣት #ታዋቂ ለመሆን ያሳፈራቸውን የጀርመን ዊንግ አውሮፕላን ተሳፋሪወች እሱ ፓይለት ነው ፈቅዶ ከተራራ ጋር ማጋጨት ነበር ህልሙ። አሳካ። ሙሉ 15 ቀን CNN (ሲኤንኤን) ላይ የሚገርም ሽፋን አገኜ። ልዕልት አንጌላ ሜርክል ጠቅላይ ሚር ነበሩ የጀርመን። ሰፊ ሃዘን ነበር። አውረፕላን ውስጥ የነበሩ ለልምድ ልውውጥ የሚጓዙ #ተማሪወች ነበሩ። አስከሬናቸው ሲለቀም #አንሰፈሰፈኝ ። ዓይኔ ቅል ቅል እስኪያክል ድረስ አለቅሳለሁ። እንቅልፍ አጣሁኝ። ያን ጊ...