ዓለማችን ህግን የማህበረሰቡ ዕውቀት እንዲሆን ልትሰራበት ይገባል።።

 

ዓለማችን ህግን የማህበረሰቡ ዕውቀት እንዲሆን ልትሰራበት ይገባል።።
"የሰው ልጅ መንገድን ያዘጋጃል
እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።"
(ምሳሴ ፲፮ ቁጥር ፱)
 May be an image of 5 people, people smiling and textMay be an image of 1 person and text that says 'POLEICE VIOLENCE- the STOP The world Shoul know the brave and the H Hero Asmra Her Name is Asmira Shumye! She escaped from the Oromo Terrorist Group n Ethiopia & spent 3 nights in a jungle hanging on a tree! She is now a voice for the remaining kidnapped 13 girls and 4 Boy University students.'May be an image of 5 people, slow loris and text
ህግ ሥርዓት ነው። ሥርዓቱን የሚያስጠብበት ድንጋጌወች አሉ። አፈፃፀሙን የሚከታተሉም ተቋማት አሉ። የህግ ትምህርት ቤቶች፤ ኮሌጆች ዩንቨርስቲወችም አሉ። በወል ኮርስም ላይ ህግን ሊያስወስድ የሚችል አጋጣሚ ሊኖር ይችላል። ህግ መማር አንዱ ምኞቴ ነበር። ጥቂት ፅንሰ ሃሳቡን በነፃ ከሚያስተምሩ ወገኖች ለጠብታ ያህል ቀማምሻለሁ።
በቤትም መሬትን ተጠንቅቃችሁ እርገጡ ከሚል ቤተሰብ ስላደኩኝ ሃይማኖታዊው ቀኖና ዶግማ ታክሎ ራስን ገዝቶ ለመኖር አግዞኛል ብዬ አስባለሁኝ። ይህ ማለት ግን መብቴን አውቄ ግዴታዬን ለመወጣት የሚያስችለኝ የህግ መሰረት አለኝ ማለት አይደለም። ኢትዮጵያ ማደግ በራሱ ይሉኝታ እራሱ የሚሰጠው በረከትም ቢኖርም።
ዓለማችን ካልሠራችው የቤት ሥራ አንዱ ህገ ነክ ጉዳዮች የፕሮፊሽናል ሰወች ማድረጓ ይመስለኛል። ህግ የጥቂት ሙያተኞች ብቻ በመሆኑ ዓለማችን "በወንጀለኞች" ትቀጣለች።
1) የዬአገሮች ህጎች እና ዓለም ዓቀፍ የሰባዕዊ መብት ድንጋጌወችን የትምህርት ሥርዓት ካሪክለም ነድፋ ከመዋለ ህፃናት ጀምሮ እንደ እንዲማሩት ለሁሉም ልጆች ብትፈቅድ፦፦፦፦
2) ማህበረሰቡ የዬአገሩን እና የዓለም ዓቀፍ የሰባዕዊ መብት ድንጋጌወችን ከቀበሌ ጀምሮ እንዲማረው፤ እንዲወያይበት ብታደርግ፦
3) ዓለማችን በዬአገሮች ህገ መንግሥት ህግጋት እና በሰባዕዊ መብት ዓለማቀፍ ድንጋጌወች ላይ አጀንዳዋ ሆኖ ብትመክር፦
4) ወንጀል ከመፈፀሙ በፊት ወደ ወንጀል ሊወስዱ የሚችሉ ማህበራዊ ቀውሶችን ማስታገሻ ላይ ቀድማ ብትሠራ፦
5) ዓለማችን እራሱን የቻለ ህገ ነክ ድንጋጌወች በተለያዬ ቋንቋ የሚያብራራ
5.1 ዬቴሌቢዥን ፕሮግራም
5.2 የራዲዮ ፕሮግራም
5.3 መጋዚኖች ጋዜጦች በራሪ ፁሁፎች
5.4 ህግ እና ድንጋጌወች የሚከብሩበት ኢቬንቶችን ብታሰናዳ
5.5 እያንዳንዱ አገር ባህላዊ የህግ አፈፃፀም አለው እና ያ ታላቅ ተመክሮ ስለሆነ ከዘመናዊ ጋር ሊዋህድ የሚችልበት መንገድ ብታጠናው። ለምሳሌ ኢትዮጵያ "ይሉኝታ" የሚባል አላት። የገዘፈ ትውፊት ነው። እኔ ከአገሬ ርቄ እዬኖርኩ በማህበራዊ ኑሮዬ የሚገዛኝ የፈቃድ ህግ ነው። ሌላም የፀጥታ ኃይል በሌለበት በህግ አምላክ ሲባልም ጥፋቱን የሚያርም ባህልም ኢትዮጵያ በቀደመው ጊዜ ነበራት።
5.6 ሲምፖዚዬሞች፦ ፓናል ዲስከሽኖች፦ ሰሚናሮች እና ወርክ ሾፖች ላይ ብትተጋ ወንጀልን ጨርሶ ማጥፋት ባይቻል ማመጣጠን ወይንም መቀነስ ይቻል ነበር። በወንጀል ክስ የሚንገላቱ ቤተሰቦችም የሥራ መስተጓጎል አይገጥማቸውም ነበር። ብዙ ሃዘንንም መቀነስ ይቻላል።
ከሁሉ አውቆ ማጥፋት እና ሳያውቁ ማጥፋት ልዩነት አለው። መብት እና ግዴታን ለማወቅ ካልተቻለ መብት አልባ ግዴታ፤ ወይንም ግዴታ የሌለበት መብት ወደ አናርኪዝም ዓለማችን ሊያመራት ይችላል።
እርግጥ ነው ዓለማችን የተለያዬ የመንግሥት ሥርዓት ያላቸውን አገሮች ወጥ ህግ አውጥቶ ተመሩ ለማለት ይከብዳታል። ነገር ግን ህግ የሁሉም ዕውቀት እንዲሆን ከሠራች በዬአገሩ መብቱን አውቆ ግዴታውን የሚጠይቅ፤ ግዴታውን ተወጥቶ መብቱን የሚጠይቅ የተስተካከለ ማህበረሰብ ዓለማችን ሊኖራት ይችላል።
#ከሃይማኖቶች ጋር አብራ ዓለማችን ብትሰራ።
እኔ በበዛ ሁኔታ ጀርመኖች በትውልድ ላይ የሚሠሩትን እከታተላለሁ። ጥናት ባላካሂድበትም ከእስያ የመጡ ወጣቶች ቲም ወርክ ላይ በጣም የተረጋጉ እና ምቹ ሆነው ብዙ ጊዜ አያለሁኝ። ይህ ሳስበው እራስን ከመግዛት የመጣ ጥበብ ይመስለኛል። እያንዳንዱ ሃይማኖት የራሱ ዶግማ እና ቀኖና ስላለውም በዚህ ጉዳይ ላይም የተገባው ትኩረት ቢሰጠው የሚል ዕይታ አለኝ።
እኔ ስታዘብ አብዛኞቹ ህግ የተማሩ የዓለም ዜጎች እጅግ ጠንቃቆች፤ በሳብዓዊነት ላይ ትጉኃን ናቸው። እሰቡት ህግ የማህበረሰቡ ቢሆን ምን ዓይነት #ምርጥ #ዘር ዓለማችን እንደሚኖራት።
መከወኛዬ ጥያቄ ነው። እኔ የአንድ አገር ህገ መንግሥትን ሳላውቅ ጥሼ ብገኝ ወንጀለኛልባል እችላለሁን?
የኔወቹ እንዴት አረፈዳችሁ? ደህና ናችሁን? ስክን ያለ ዕለትይመስላል። ለዚህም ነው ፁሁፋ ለለቱ።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
21/06/024
ጊዜ ራዲዮ ነው።
የህግ ዕውቀት ለሰው ልጅ ሁሉ ሊሰጥ ይገባል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።