#ጥበብ #ከእስር #ትፈታ።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
አፅናኝ መሪ ላጣችው ኢትዮጵያ፤ አይዟችሁ ባይ ሙሴ ለራባት ኢትዮጵያ ጥበብ አንደበቷ ተከፍቶ አይዟችሁ ብትል፦ ብታጽናና የድርሻዋን ብትወጣ ዛሬን በተስፋ ማሳደር ነገን በተስፋ ማስቀበል ይቻላል።
በሌላ በኩል ትውልዱ ጥበብን እንዲፈራ፦ ፀጋውን እንዲሸሽ ማድረግም #ዳፍንታም ዘመን ዘመኑን ያደርጋል። #እሰቡበት። #አማናችነን ፍቱት። ዕውነትን አትፍሩ። መድፈር ቢያቅታችሁ ዕውነትን ደፋሪወችን #ዘር #እዬቆጠራችሁ አታሳዱ። እኔ #ቅናትም ይመስለኛል። አሜሪካ ሲገባ #ካሊሙን ለብሶ ነበር - ተፈጥሯዊ የሆነ ሳተና። እዛው መቅረት ሲችል አገሬን እናቴን ብሎ ተመለሰ። ከዛ አሜሪካ ያያትን ቤቱ በር ላይ ሠርቶ መፀሐፍ ሼር የማድረግ ልምዱን ወስዶ በሩ ላይ ያችኑ ሠራ። ይህ #ቅን እንዴት ይታሠር?
በሌላ በኩል በእረኛ ተፈጥሯዊ ትዕይንት የተመሰጡ ዕውቅና ሰጥተውታል። ያን ማሰር የሰማይን ፀጋ መበቀልም ይሆናል። ኮንፊደንስ የነሳው ሥርዓት ለራሱ አይበጀውም። ኮንፊደንስ ስለአጣችሁ እንጂ ሁለት ፍሬ ሥንኝ እንዲህ አያስበረግጋችሁም ነበር። በድንገት የታጡ አርቲስቶች የተፈሩበት አመክንዮ ይኽው ነው። ለዛውም ተዋህዶወች ተመርጠው። እኩል ለኩል ተብሎ አርቲስት አጫሉም አርቲስት ማንዲጎም የሆነው ሆነ።
የኢትዮጵያ ተውኔት ድርቅ መቶታል። ጥበብም በካቴና። ጥበብ ያጣች አገር???? ትውልድ እና አደራ መዳረሻቸው ይታሰብ። አማን አማን ነው። ብቃቱም ልቅናውም የእዮር ነው። እዮርን ለካቴና???
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉትሻ 21/06/025
ጊዜ ራዲዮ ነው።
ዕውነት ጋራጅ አያሰኜውም።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ