#ኢትዮጵያ "ጋለሞታ" አይደለችም። አበስኩ ገበርኩኝ! ስለአገላለፁ። oct 20.2020
#ኢትዮጵያ "ጋለሞታ" አይደለችም። አበስኩ ገበርኩኝ! ስለአገላለፁ። "ህግ ተላላፊወችን ጠላሁኝ።" #ኢትዮጵያ የማንም "ውሽማም" አይደለችም። ማህከነ። "ለአንደበቴ ጠባቂ አኑርልኝ።" • ይኽው ሊንኩ።አገር ከበለጠባችሁ፤ ዬጊዜ አታሞ ካልረታችሁ። https://www.youtube.com/watch?v=jaaelCVVHic&t=451s የአሁን ዋና ዋና መረጃዎች!DereNews Oct. 19 2022 #derenews #zenatube#Ethiopiannews# ኢትዮጵያ "ጋለሞታ" ስትባል፣ ኢትዮጵያ "ዬማንም ተወሻሚ" ስትባል አይጎረብጥም፣ አይቆረቁርም? ስለማን የምን ንጥረ ነገር ይሆን ዬሚተነፈሰው? ውስጣችን ለእናታችን እንዲህ ሸካራማ፣ ኮረኮንችማ፣ አሜኬላ በቀል። ከእናት አገር ጠረን ዕለታዊ ሰብዕና በልጦብን ይሆን? #በር ። ኢትዮጵያ ከቅኔም፣ ከስዋሰውም አልፋ እና ንራ ኢትዮጵያ #ሰማያዊ #ምስባኽክ ናት።።።።።።።።።።።።። ቫወልም ናት። አናባቢ። ኮንሰነትም ናት ተነባቢ። #ቅምሻ ። ጎንደር ላይ ሲዘንብ የባጀው የዲን በረድ አሁን ኢትዮጵያ ላይ ደግሞ መጥቷል። በተለይ "ኢትዮ" ብላችሁ ምንም ተቋም የምትከፍቱ፣ የምትጀምሩ ወገኖቼ በልኳ ለመሆን እሰቡበት። ኢትዮጵያ ረቂቅ መንፈስ ናት። የራሷ ዬሆነ አንጡራ ማንነት ያላት የድንቅነሽ ድንቅ ናት። ዲስፕሊኑን የመጠሪያዋን ዬሚመጥን፣ የሞራል አቅም ይጠይቃል። የአውራ አገር መጠሪያ ነውና። ዬማይፋድስ፣ ዬማይነጥፍ ፏፏቴ ሥም ነው ያላት ኢትዮጵያ አገራችን። ይህን ብዬ ዬፃፍኩት በ2014 ደጉ ዘሃበሻ እና ደጉ ሳተናው ላይ ነበር። በፀጋዬ ራዲዮም በተደጋጋሚ አቅርቤዋለሁኝ። በቅርቡም ጹሐፋን በንባብ ዩቱብ ቻና...