ህም። ግራሞት ቀጥሏልoct 20.2019

ህም። ግራሞት ቀጥሏል። የኦሮሙማ ጠሚር አብይ አህመድ ሌጋሲ ቀለሙ ድንገቴ ነው። ለዚህም ነው ህም ቅደም የተባለው። በትናንትና በዛሬው የኦሮሙማ ሠርግና መልስ የታዘብኩት ጠሚር አብይ አህመድ ራሳቸውን ማምለካቸውን ብቻ አይደለም። ይልቁንም እንደ አምላክ እንዲታዩ ያለባቸውን የውስጥ ግብግብ አይቻለሁ። ይህ ማለት ምን ማለት ነው " አምልኮ አብይ የማምለኪያ ሥፍራም፣ አብያውያንም በአብይ አምላክ ሲሉ፣ አብይ ይሙት ሲሉ፣ " የሚደመጥበት ጊዜ እንደናፈቃቸው ነው ያዬሁት። ከዚህ ጋር ተያይዞ " ይህ በመካከለኛ፣ በአጭር ሞገድ የሚተላለፈው የአብይ የራዲዮ ጣቢያ፣ የአብይ ሾው፣ የአብይ ቴልቪዥን" ፋታ ከሰጣቸው የተፎካካሪያቸው የጃዋር መንፈስ በቀጣይ አይቀሬ ይመስላል። እንዲያውም ዜጋው ሁሉ ከግንባሩ ላይ አብይ እያለ ቢወቀር ይሻሉ። ሌት እና ቀን መስማት የሚፈልጉት፣ ሙገሳ፣ ውዳሴ፣ ምስጋና ብቻ ነው። አይሰለችም? አድማጩ እራሱ አይሰለቸውም። 19 ወራት ሙሉ የፕሮሚውን ወይንም የቢአይፒውን፣ የአርቲስቱን፣ የአክቲቢስቱን፣ የሰባኪውን ቦታ ሁሉ አራጠው ይዘው በቃ መፈንደቅ ነው፣ ልጅ እያለን አዲስ ልብስ ሲገዛልን ለብሰነው ካላደርን እያልን ወላጆቻችን እንደምናስቸግረው። መዲናዋ አዲስ አበባ ግን አካባቢዋ ግን ይህን መስላ ነው የዋለችው። ለመክደኛም ይሁን እጬጌው ህም።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።