የሙጣጭ ኤሉሄ ህቅታ። oct 20.2020

 

የሙጣጭ ኤሉሄ ህቅታ።
በትናንትናው የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊ የዲስኩር ውሎ እንጥፍጣፊ አልቦሽ የሆነ ግዙፍ አመክንዮ አስተዋልኩኝ።
በግዜ ስለነበር የተኛሁት እኩሌሊት ነቃሁ። ሌሉትን ሁሉ አሰብኩት። አወጣሁት አወረድኩት። በልቦናቸው፣ በህሊናቸው፣ በመንፈሳቸው ውስጥ አማራ የሚባል ማህበረሰብ እርሾ አልቦሽ እንጥፍጣፊ ሙጣጭ ቤተኝነት አልነበረውም። ሳያኖሩን አመናቸው እናም አመከኑን።
የክደታቸው፣ የውሸታቸው ቋት መሰረቱ መጪው መከራ አስፈርቶኛል። ግደሉ እያሉ ያሰማሯቸውን የቀኝ እና የግራ ክንፎቻቸው መንትዮሾቹ የቤንሻንጉል ጉምዝ እና የኦሮምያ መስተዳድር ቁንጮዎች ጆከሩን የአማራውን ካባ ሸላሚ እና አመስጋኝ ጨምሮ በጭካኔያቸው ይቀጥሉ ዘንድ ግፋበት ብለዋል። ትንሽ እንጥፍጣፊ አዘኔታ? ኦ! አምላኬ።
በትናንቱ ውሎ ኦነግ ሸኔም ነፃ አውጥተውታል። በደሉን ሱዳንን ሄዳችሁ ጠይቁ ተብሏል። በትናንቱ ንግግራቸው በአማራ ላይ ንፁህ ዲስክርምኔሽን ፈፅመዋል። ከዚህ ቀደም አልፈፀሙም ማለቴ ግን አይደለም።
የአማራ ደም ጅረት እና ውቅያኖስ ቢኖረው፣ ንግሥናቸውን ሥርዓት በዛ እዬዋኙ ይፈፁሙ ነበር። ሰባዕዊነት ቀርቶ ጨካኝ መሪ ሆነው አልታዩኝም። ጨልመው ታዩኝ።
ትዕቢታቸው፣ ልግጫቸው፣ መስቃቸው የት ሊያደርሳቸው እንደሚችል እጬጌው ሂደት ይመስክረው። መጋቢት 18/2010 በማን ሙሉ ድምፅ ይህን የሚመኩበትን ቦታ እንዳገኙት ያውቃሉ።
ዛሬ ያ ተረስቶ፣ ያ የጭንቅ ቀን ተክዶ ለዚህ መከረኛ ህዝብ ለሞቱ፣ ለጥያቄዎቹ ዕውቅና ለመስጠት ታበዩ። በጣም ተንጠራሩ። ከሳቸው በላይ ፈጣሪ ስላለ መጨረሻውን ይጠበቃል ችሎቱ።
የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ፣ የአማራ ወዳጅ እንደ ወገን የትናንቱን ክህደት ከልብ በማድመጥ ለዚህ ቅን ህዝብ ከሄሮድስ አመራር የሚላቀቅበትን ብልኃት ፈጣሪ እንዲያቀብል ቢያንስ በፀሎት ሊረዱት ይገባል። አማራን አልባ አገር የለምና።
አማራ የቆረጠ ቀን የኢትዮጵያዊነት የመጨረሻው ዕለት ይሆናል። ብዙ ተሸክሟል፣ ብዙ ችሏል በእሱ ደም እና አጥንት እስከ መቼ? የሚለው መልስ ሊሰጠው ይገባል። የማይደፈሩ አመክንዮዎች ተደፍረው ሊጠዬቁ ይገባል።
አማራ ተቆርቋሪ መሪ፣ አዛኝ መሪ፣ አይዞህ ባይ መሪ፣ ተስፋ ሊሆነው የሚችል መሪ የለውም። ለዚህ የዬለምነት ዘመቻ የአማራ ህዝብ ቁርጡን አውቆ ተጋድሎውን አጠንክሮ መቀጠል ይኖርበታል።
ተጋድሎ የቃታ ጉዳይ ብቻ አይደለም። ፀሎት፣ ስግደት፣ ሱባኤ፣ ጥሞና ማለትም ነው። አገር አልባው አማራ ምን ቅን ቢሆን፣ ምን ሁለመናውን ቢገብር አይደለም እራስጌ እግርጌውን ማግኜት አልቻለም። ጠቀጠቁት።
ተጋሩ የሚከበረው አቅሙን ቆጥቦ ስለሚያስተዳድር ነው። ስለማይለማመጥ ነው። ከጅልነት ቅንነት ስለሚቆጠብ ተፈርቶ፣ ዕውቅና አግኝቶ አገር ያለው ስለመሆኑ እዛ ያሉ ህዝቦቼ እንዲሰቃዩ አልሻም ይባላል።
ከአንገት ይሁን ካንጀት በግራጫማው የሲቃ የጠቅላዩ ሰብዕና ልኩ ባይታወቅም። ቢያንስ የሥነ - ልቦና ጥቃት አይደርስበትም። ሊቃናቱ መዳፍ ላይ ቢገኙ ግን አፍታ አይቆይም። ይታጨዳሉ።
የአማራ ልጅ ለእሾህ ሰብዕና አደገደገ፣ ደገፈ፣ ካባ አለበሰ፣ ወደቀ ተነሳ በጠቅላዩ ልቦና ግን ልሙጥ ነው። አማራ የለም። "ልብ ያለው ሸብ" እንደ ጎንደሮች።
አማራን እያዛሉ፣ እያደነዘዙ፣ እዬከፋፈሉ ለዚህ ውርዴት ላበቁት ማህበር ዕብናውያን ፈጣሪ የእጃቸውን ይስጥ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ፈጣሪ ሆይ! የአማራ ህዝብ በችግሩ ልክ ዕውቀት ይኖረው ዘንድ ልቦናውን ፏ ፍንትው አድርገህ ክፈትለት። አሜን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።