የሰውን ልጅ መኖር በግፍ መቀማት #ስርቆት አይደለምን?
የ ሰውን ልጅ መኖር በግፍ መቀማት # ስርቆት አይደለምን ? " የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፦ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል። " ( ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱ ) # መቅድም ። እ ንዴት አላችሁልኝ ክቡራት እና ክቡራን የልቦቼ። ደህና ናችሁ ወይ ? ኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጠሩ አገዛዞች የሚቆሙት ባላ እና ወጋግራወች ኢትዮጵውያን በሚከፍሉት መስዋዕትነት ነው። የኢትዮጵውያን አብራክ እና ማህፀን ቄራ ነው ዘመን ከዘመን። እግዚኦ። በተለይ አማራ። እኔ ከተፈጠርኩ፤ ነፍስ ካወቅኩበት ጊዜ ጀምሮ በተፈጥሮ አደጋ ከምናጣቸው ቤተሰቦቻችን በላይ በድህነት፤ በአስተዳደር ብልሹነት፤ በጦርነት የምናጣቸው ወገኖቻችን ይበልጣሉ። በተፈጥሮ ሞት የምናጣቸውም ቢሆን በድህነት የሚሞቱ ወገኖች አሉን። ድህነት እኮ የበሽታ ምንጭ ነው። ጭንቀት ይፈጥራል። ለበርካታ በሽታወችም ያጋልጣል ድህነት። በተስተካከለ የህክምና እጦት ምክንያት የምናጣቸው ወገኖች አሉን። በእስራት፤ በአፈና የምናጣቸው ወገኖች አሉን። ይህ ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት በሰው ልጅ መኖር ላይ የፈፀመው ስርቆት አይደለምን ? የቀደሙትም ቢሆን ሊጠዬቁበት የሚገባ ነው። ሚሊዮን ተረጂ አልበቃ ብሎ ማደህዬትም ታቅዶ እዬተሰራበት ነው። ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ሰባዕዊ ጉዳዮች እያሉ ሚሊዮኖች ከጎርፍ ጋር እያደሩ አንድ አይሉ ሁለት # እዮቤል ቤተ - መንግሥት እና በዛ ዙሪያ ለሚሰባሰቡ ድሎተኞች ሽሙንሙን ቢሮ መገንባት የዜጎችን የመኖር ተስፋ መቀማት አይደለም...