ልጥፎች

ከኦገስት 26, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

Amhara Movement: Advocacy & Diplomacy

ምስል

ህፃን ሔቨን የመፍትሄ ንቅናቄ #ውክል #ዓርማ ናት። መደፈር፤ ጥቃት፤ ፍትህ፤ ጥበቃ፤ Vergewaltigen, Ang...

ምስል

ህፃን ሔቨን የመፍትሄ ንቅናቄ #ውክል #ዓርማ ናት ልክ እንደ አና።

ምስል
  ህፃን ሔቨን የመፍትሄ ንቅናቄ #ውክል #ዓርማ ናት ልክ እንደ አና።   "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም።"     እንዴት አደራችሁ ውድ ቤተሰቦቼ? ደህና ናችሁ ወይ?    የአንድ ሳምንት የህፃን ፌቨን ንቅናቄን ትርጉም ባለው ተቋማዊ የተግባር መስክ መቋጫ ቢያገኝ ምኞቴ ነው። ንቅናቄው #ግሎባል ነበር። የብዙ ወገኖችን የህሊና በር አንኳኩቷል። ካለ ምንም የደንበር ልዩነት አብዛህኛው ኢትዮጵዊው #በርህርህና ድምፁን አሰምቷል። በጎውን - አወንታዊውን - የተጋድሎ ምዕራፋን እኔ ሳስተውለው #ክስተት የመሆን አቅምም አግኝቷል ብዬ አስባለሁኝ።    በአሉታዊ የተነሱ ኃሳቦችን አልፎ አልፎ አዳምጫለሁኝ። አቅም፤ ጊዜ መንፈስ ሊጠፋ የሚገባው የሚገጥሙንን ፈተናወች ለመፍትሄ አቅርቦታቸውን በመጠቀም ብቻ ሊሆን ይገባል። ለአንዱ ግን መልስ ልሰጥ ወደድኩኝ።    ይህም ለምን አሁን ለሚለው ጥያቄ። #እግዚአብሄር ሥራውን የሚሠራበት ጊዜ ስላለው ነው። ፈጣሪ #የፈቀደው ሰዓት እና የወደደው ጊዜ ይህ ስለሆነ ነው። ዕድሉን መጠቀም ደግም የሩህሩኃን ተግባር ነው።   እርግጥ ነው የተለያዩ #አሉታዊ ሃሳቦች ተነስተዋል። በተለይ አንድነቱን፦ ህብረቱን የተመለከቱ ማዋጋቱን አጋግለውታል። ከማይነካካ አመክንዮ ጋር እያነካኩ ላባቸው ጠብ እስኪል ሲናገሩ ሰምቻለሁኝ። ይህ ለእኛ አይጠቅመንም።    እኛ #በሰዋዊ ስሌት ለትውልዱ ሊጠቅሙ በሚችሉ የርህርህና፤ የአይዟችሁ ሰብዕና፦ እና የአጽናኝ መንፈሶች ላይ ብቻ ልንተጋ ይገባል። በጎ ስለማያስቡ ግለሰቦች ዕውቅና ሰጥቶ ጊዜ ማቃጠል አያስፈልግም።    #ጉዳዩ የደነደነ ፈርዖናዊ ልብ ያለውን ...

ጠለምት።

ምስል
 

#ነፍስ ይማር።

ምስል
  #ነፍስ ይማር።      ሟቹ አርቲስት ጌታቸው እጅጉ ዬአዲስዬ የልደቴ ልጅ ነበር። ከ15 ዓመት በጥበብ ውስጥ ቆይቷል፤ ፊልም ቤት በትርጉም ሥራ አተኩሮ ይሠራ ነበር። ከ60 በላይ በፊልም ሥራ ተግቶ ሰርቷል። በሃይማኖቱም ጽኑ እንደሆነ ተገልፆዋል።   በአዲስ አድማስ በአምደኝነት ሠርቷል። ከ4000ሺህ በላይ መፃህፍት በቤቱ እንደሚገኝ የጊዜ ዘገባ ይገልጸዋል። 14 ሺ መፃህፍት ማንበቡ ተገልፆል። በበጎ ተግባርም ይሳተፍ እንደነበር ዘገባው ገልፆል። ዘገባው የጊዜ ሚዲያ ነው። ከሚዲያ ላይ እንደተረዳሁትም ግልጽ እና ቀጥተኛ ሰብዕና እንደነበረውም ተረድቻለሁኝ።   ለቤተሰቡ - ለሚወዱት - ለሚከተሉት ሁሉ እግዚአብሄር ጽናቱን ይስጣቸው። አሜን።   https://www.youtube.com/watch?v=hqFV66PIlco&t=601s ልብ ይሰብራል 60 ፊልም ሰርቶ የሚበላውበ አጥቶ በችግር ምክንያት ሞተ(‎@gizemedia1974)Ethiopia|Elisa Degenet|25 August 2024