ህፃን ሔቨን የመፍትሄ ንቅናቄ #ውክል #ዓርማ ናት ልክ እንደ አና።

 

ህፃን ሔቨን የመፍትሄ ንቅናቄ #ውክል #ዓርማ ናት ልክ እንደ አና።
 
"እግዚአብሄር በአንድም በሌላም
ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም።"
 
May be a doodle of 7 people and textMay be a graphic of 4 people and textMay be an image of 4 people and text
 May be an image of 7 people, slow loris, television and text
እንዴት አደራችሁ ውድ ቤተሰቦቼ? ደህና ናችሁ ወይ? 
 
የአንድ ሳምንት የህፃን ፌቨን ንቅናቄን ትርጉም ባለው ተቋማዊ የተግባር መስክ መቋጫ ቢያገኝ ምኞቴ ነው። ንቅናቄው #ግሎባል ነበር። የብዙ ወገኖችን የህሊና በር አንኳኩቷል። ካለ ምንም የደንበር ልዩነት አብዛህኛው ኢትዮጵዊው #በርህርህና ድምፁን አሰምቷል። በጎውን - አወንታዊውን - የተጋድሎ ምዕራፋን እኔ ሳስተውለው #ክስተት የመሆን አቅምም አግኝቷል ብዬ አስባለሁኝ። 
 
በአሉታዊ የተነሱ ኃሳቦችን አልፎ አልፎ አዳምጫለሁኝ። አቅም፤ ጊዜ መንፈስ ሊጠፋ የሚገባው የሚገጥሙንን ፈተናወች ለመፍትሄ አቅርቦታቸውን በመጠቀም ብቻ ሊሆን ይገባል። ለአንዱ ግን መልስ ልሰጥ ወደድኩኝ። 
 
ይህም ለምን አሁን ለሚለው ጥያቄ። #እግዚአብሄር ሥራውን የሚሠራበት ጊዜ ስላለው ነው። ፈጣሪ #የፈቀደው ሰዓት እና የወደደው ጊዜ ይህ ስለሆነ ነው። ዕድሉን መጠቀም ደግም የሩህሩኃን ተግባር ነው።
 
እርግጥ ነው የተለያዩ #አሉታዊ ሃሳቦች ተነስተዋል። በተለይ አንድነቱን፦ ህብረቱን የተመለከቱ ማዋጋቱን አጋግለውታል። ከማይነካካ አመክንዮ ጋር እያነካኩ ላባቸው ጠብ እስኪል ሲናገሩ ሰምቻለሁኝ። ይህ ለእኛ አይጠቅመንም። 
 
እኛ #በሰዋዊ ስሌት ለትውልዱ ሊጠቅሙ በሚችሉ የርህርህና፤ የአይዟችሁ ሰብዕና፦ እና የአጽናኝ መንፈሶች ላይ ብቻ ልንተጋ ይገባል። በጎ ስለማያስቡ ግለሰቦች ዕውቅና ሰጥቶ ጊዜ ማቃጠል አያስፈልግም። 
 
#ጉዳዩ የደነደነ ፈርዖናዊ ልብ ያለውን መንፈስን ገርቶ ለመልካምነት ካተነሳሳም መልካም ዕድል ነው። ማቆላመጥ፤ ማባበል ያለብን የችግሩን ጥልቀት የተረዱ ንፁኃን ሌት እና ቀን እንደምን እንደ ተጉ እና #ህመሙ #ተፅዕኖ ፈጣሪ ሆኖ ሊወጣ መቻሉ፦ የድል ርካብ ስለመሆኑ ነው ልናስብ የሚገባው። በዚህ ዙሪያ የታተሩ ሚዲያወች፦ ወገኖች ሁሉ ሊመሰገኑ ይገባቸዋል።
 
#ስለ ህፃን ሔቨን ወላጅ እናት ወ/ ሮ ሲስተር አብቄለሽ።
 
እኔ አስግቶኝ የነበረው የሲስተር ወ/ሮ አበቄለሽ የመኖር ዋስትና #በቀጣይነት ነበር። መልክ የያዘ ይመስላል። በአኗኗራቸው ዘይቤ ግን በግላቸው አሁንም ብርቱ #ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ በአጋጣሚው አሳስባቸዋለሁኝ። #የጥሞና ጊዜ ቢኖራቸውም ምርጫዬ ነው። ልጅ ስላላቸው ለልጃቸው ቀጣይ ሕይወት መኖር ስለአለባቸው በዝግታ መራመድ፤ አመጋገብ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ፤ በብዙ መቆጠብ፤ በጊዜ ቤት መግባት፤ ጓደኛን መወሰን ይገባል።
 
#ቀጣይ የተጋድሎ ምዕራፍ።
 
እኔ የኢትዮጵያ #ህፃናትን በሚመለከት ባለቤት አልባ ስለሆኑ አቅም ያላቸው፦ #የህፃናትን #መብት #አስከባሪ፤ ሞጋች የሲቢክስ ተቋም ይከፍቱ ዘንድ ተማጽኛቸው ነበር። በተለይም ዘግናኙ የአማራ ልጆች ሰቆቃ በመተከል፤ በወለጋ #እዬመረረ ሲመጣ። አሁንም የሚችሉ ቢያስቡበት ጥሩ ነው። 
 
በሌላ በኩል የህግ ክፍተት አለ ስለሚባል፦ ክፍተቱን የሚሞሉ ድንጋጌወች ብቻ መጨመር ብቻ ሳይሆን በዚህ #አስገድዶ #በመድፈር ክስተት ዙሪያ ትውልድን ከጥቃት እንደምን መጠበቅ እንደሚቻል #ተጨማሪ ህግ አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁኝ። ስለሆነም ቢታሰብበት መልካም ይሆናል። ለነገሩ ለህፃናት የሚያስብ አንድም የፖለቲካ ድርጅት ማኒፌስቶ እኔ አላውቅም።
 
#በፍርድ እና መሰናዶ ሂደቱ ልዑክ ቢገኝ። 
 
1) ሂደቱ በሚዲያ #በቀጥታ ቢተላለፍ መልካም ነው።
2) አግባብ ያላቸው በህግ አፈፃፀም ጉዳይ የሚሠሩ ባለሙያወችም በቦታው ቢገኙ ምኞቴ ነው።
3) ከተመራቂ የህግ ባለሙያወችም የተወሰኑ እጩወች ቢታደሙ መልካም ይሆናል።
4) ይህን የሚያመቻች ኃላፊነት ያለው አካልም የኢትዮጵያ የፍትህ አካላት ቢያስቡበት ጥሩ ይመስለኛል።
5) በሴቶች፤ በህፃናት እና በወጣቶች ዙሪያ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትም በቀጠሮው ዕለት ቢገኙ መልካም ይሆናል።
6) መምህራንም በሂደቱ ቢሳተፋበት መልካም ይመስለኛል።
7) የሥነ - ልቦና ባለሙያወች በቀጥታ ጉዳዩ ስለሚመለከታቸው ቢካተቱበት ጠቀሜታው ዝቀሽ ነው።
8) የህፃናት ሃኪሞችም በፍርድ ሂደቱ ላይ ቢታደሙ ሸጋ ነው።
9) በህሊና ግንባት ላይ የሚታትሩ ወጣቶች ቢኖሩም ምርጫዬ ነው።
 
1) ከችግሩ ግዝፈት አንፃር፤
2) የጥቃቱ #ተከታታይነት፦ ትናንትም ጥቃት ነበር፤ ዛሬም ጥቃቱ አለ ህልው ነው፤ ነገም ሊቀጥል ይችላል።
3) #ግሎባል ባህሬው፦
4) የክስተቱ #ተጽዕኖ ፈጣሪነት፥
 
… ዐይቶ በዕድሉ መጠቀም ብልህነት ስለሆነ ችግሩን ተረዳድቶ ፈር ለማስያዝ #አቅምን #ማማከል የሚያስችል ሁኔታም መፍጠር ይገባል ብዬ አምናለሁኝ። የኢትዮጵያ መንግሥት #የህዝብ #አገልጋይነት #አቅም ከኖረው? ልጆች የማህበረሰቡ ብቻ ሳይሆኑ የመምህራንም ናቸው እና የእነሱን ተሳትፎ በአግባቡ መጠቀም ይገባል።
 
 እርግጥ ነው በመምህራን የመኖር ዋስትና ላይም መጠነ ሰፊ ችግር እንዳለ እረዳለሁኝ። የሆነ ሆኖ በዚህ ክስተት መነሻ የተገኜውን የህዝብ ቁጣ እና ጥልቅ ሃዘን ዕድሉን በአግባቡ ለመጠቀም አንድ ትልቅ ልዑክ ያስፈልጋል የፍርድ ሂደቱን በአካል ተገኝቶ የሚመለከት።
#ጋብቻ እና ልጆች፦
 
ጥንዶች ልጅ ከወለዱ በኋላ መለያዬቱ የሚያመጣው መከራ የገዘፈ ነው። በዚህ ዙሪያ እኔ የመነሻ ሃሳቦችን የያዘ መፀሐፍ "ርግብ በር" በሚል ጽፌ ነበር። ትዳር ሲኖር እና ትዳሩ ሲፈርስ የቀጥታ ተጠቂወች ልጆች ናቸውና። የሚበደሉም የሚጎዱም ልጆች ናቸው።
 
የፆታዊ ጥቃት እንሰሳዊነት ነው። በዘርፋ በቂ አትኩሮት ሰጥቶ ተከታታይነት እና ቋሚ ጥረት ይጠይቃል። በውነቱ የተደራጀ ተቋምም ያስፈልገዋል። አደራዬ "የብልጽግና ካድሬወች" ስብስብ እንዳይሆን። ይህ ክስተት ከፖለቲካ ድርጅቶ ፍላጎት በላይ ተፈጥሯዊ የሆነ ሰብዕናን ስለሚጠይቅ። 
 
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Slassie
26/08/024
 
የፆታ ጥቃት ይቁም!
ልጆች የሁላችንም ልጆች ናቸው።
የህፃናት መብት አስከባሪ ተቋም በኢትዮጵያ ይቋቋም።
ችግር መፍትሄ አፍላቂ ይሆን ዘንድ ዕድሉን መጠቀም ብልህነት ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።