ልጥፎች

ከኦክቶበር 8, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#አለቀ! አበቃ! #መራራ ስንብት። በዲሞሽን ሽኝት። #አናርኪዝም #እራሱን #ያራባል።

  #አለቀ ! አበቃ! #መራራ ስንብት። በዲሞሽን ሽኝት።   "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል፦ ሰው ግን አያስተውለውም።"   አናርኪዝም እራሱን ቢያራባ እንጂ እራሱን የሚቀጣ ክስተት አይደለም። የፕሬዚዳንትነት ሽኝት እና ስንብት ፕሮስጄራሊ እና ለትውልድ አትራፊነቱ ወይንም ኪሳራውን ለመዳሰስ እሻለሁኝ። ምዕራፍ ፲፬ በዚህ መልኩ ይቀጥላል። ከበረገገው ጋር መበርገግ፤ ከቆዘመው ጋር መቆዘም፤ ከሚርገበገበው ጋር መርገብገብ፤ ከዘበጠው ጋር አብሮ መነከር ፈቃድ አይሰጠውም።    #ሰሞናቱ እና ትዝብቴ።    የክብርት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን የሥራ ዘመን ቀድሞ መጠናቀቅ አስተዋልኩኝ። በብዙ ውስብስብ የፖለቲካ ዕድምታወች የተተበተበ ነው። ወደዛ የመግባት ፈቃድ የለኝም። እኔ እማነሳው ሥርዓታዊ አፈፃፀሙ ወይንም ፕሮስጂራሊ የተጠያቂነት እና የኃላፊነት ጣሪያ እና ግድግዳ በአስተውሎት መግለጽ ነው።    ሥልጣን ላለው መንግሥትም፤ በለስ ቀንቶት ለሚተካውም አስፈላጊ ስለሆነ። ስለሆነም የአንድ አገር ሥነ መንግሥታዊ ሥርዓት ለአገር ክብር፤ ሞገስ እና ፀጋ ተክሊል ነው። ስለሆነም አካሄዱ ላይ ማተኮር ነው የምሻው። ኦ! መራራ ስንብትን ካነሳሁ ዘንዳ ፕ/ በዬነ ጴጥሮስ የሚፈቅዱት ኃላፊነት የነበረ ይመስለኛል የአገር ፕሬዚዳንትነት። በነበር ቀረ እንጂ። የሆነ ሆኖ ጓዘ ቀላል ጥያቄ ላንሳ። ጥያቄ ህሊና ላለው #ቅን እና #ቀና ዜጋ በሙሉ ነው።    1) ክብርት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ ሲሰናበቱ ከቀናቸው ቀድሞ ነው። ይፋዊ ዘመናቸው አልተጠናቀቀም። ይህ ለምን ሆነ? ጥድፊያው ስለምን ይሆን? ይህም ይሁን አምስት ዓመት ተሳስቼ አይደለም አምስት ዓመት ያልኩት፤ በሥራ ዘመናቸው ...

#የአማራ #እናት #ስትፈጠርም፦ #ስትፈጥርም ዕጣ ፈንታዋ በኢትዮጵያ ፖለቲካ #ቀራኒዮ!

  #የአማራ #እናት #ስትፈጠርም ፦ #ስትፈጥርም ዕጣ ፈንታዋ በኢትዮጵያ ፖለቲካ #ቀራኒዮ ! "የቤትህ ቅናት በላኝ።'   የአማራ እናት አሳረኛ ናት። የአማራ እናት መከረኛ ናት። የአማራ እናት ፍደኛ ናት። የአማራ እናት ስቃዬኛ ናት። የአማራ እናት ስትፈጠር ለቀራኒዮ ነው። የአማራ እናት ስትፈጥርም ለቀራኒዮ ነው።   የአማራ እናት ተስፋዋን ነጣቂው ተስፋዋን ሲፀነስ ነው የሚነጥቀው። የአማራ እናት ተስፋዋ ገና በቀንበጡ ለፖለቲካ ማገዶ ነው። የአማራ እናት በብዙ መከራ ያሳደገችው ቡቃያ ለኢትዮጵያ የሴራ ፖለቲካ ማገዶ ነው። አንድ ፔና ያልገዛ ፖለቲካውን አህዱ ሲለው ሁለመናውን የሚበጅተው በአማራ እናት ቡቃያ ነው።    ይህ ለ50 ዓመት የዘለቀ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ትልም ነው። አሳካነም፦ ወደቅንም፤ አተረፍንም ከሰርንም የሚሉ ፖለቲከኞች መነሻ መድረሻቸው ጥሬ ምርቱ የአማራ እናት ቀንበጥ እና ሸበላ ፍሬ ዘር ናቸው።    የአማራ እናት ተፀንሳ፤ ተወልዳ ስታድግ መንፈሷ እዬተዘረፈ፤ ሐሤቷን እዬተነጠቀች ነው። ሳቋን በግፍ ተቀምታም ነው። ልጆቿ በህይወት ቢኖሩ እንኳን በአሻት ሰዓት አታገኛቸውም። መኖሯ በስጋት የተጥለፈለፈ ነውና። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ለአማራ እናት ቀራኒዮ ነው።   በኢትዮጵያ ፖለቲካ የአማራ እናት የሳቀችበት፤ ወህ ያለችበት፤ የተመሰገነችበት፤ የተሞገሰችበት የታሪክ አጋጣሚ አላውቅም። ይህን ህመም የሚጋሩ የኢትዮጵያ እናቶች መኖራቸውንም እረዳለሁ። ተግቼላቸውምአለሁ።   በዚህ በስድስት ዓመት በአዬሁት፤ በታዘብኩት ልክ በአማራ እናት ተስፋ ላይ ምሳሩ ጠንቷል። ከዛም በፊት ቢሆን ያው ነው። የአማራ እናት ተሰፋ የተገኜ "ለውጥ" ለእሷ ምጣቷ እንሆ ሆነ። የጠሚር አብይ አህመድ መንግሥት ...