ልጥፎች

ከኤፕሪል 27, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ከባዱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ፖለቲካ ነው። ቢፈራም፤ ጠላት ቢበዛበትም መንግሥት እስከ ሠራዊቱ ቢሰለፍበትም ያልተበገረው በዚህው ነው።

ምስል
  ከ ባዱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ፖለቲካ ነው። ቢፈራም፤ ጠላት ቢበዛበትም መንግሥት እስከ ሠራዊቱ ቢሰለፍበትም ያልተበገረው በዚህው ነው።   " የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፦ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ይጠይቃል። ( ምሳሌ ፲፮ ቁ ፱ )     # አድማጭነት # ዝቃታ # ታዛዥነት # ተመሪነትን # ርህርህና # አጽናኝነት # አይዟችሁባይነት # ሰዋዊነት መፍቀድ መርህ ይሁን። መዳኛም መከበሪያም መመረቂያም መበራከቻም። ዘለግ ያለ ነው ለታጋሽ ቅናውያን የተጣፈ ነው። ሸበላ የመደማመጥ ጊዜ ይሁንልን። አሜን። እ ንዴት አደራችሁ ክብራት እና ክብሯን ወዳጆቼ። እንዴት ነን ? ከምን ነን ? የት ላይ ነን። የፋኖ ንቅናቄ ገዝፎ መነቃነቅ ከጀመረ ወዲህ በአማራ ፖለቲካ ላይ በግል በጓዳ ከምሟገታቸው ውጪ ትግሉን ሊያለዝ ወይንም ግብታዊ ሊያደርገው ይችላል በማለት እስኪሰክን ታግሼ ቆይቻለሁ። ወደፊትም በትዕግሥት ማዬቱ እና መጠበቁ በቂ ይመስለኛል። አ ቶ እስክንድር ነጋንም ፋኖን እመራለሁ እንዳትል ብዬ ከእስር እንደተፈታ በስፋት ስጋቶቼን ዘርዝሬ ጽፌ ነበር። የጓዳው ሙግትንም እመክት ነበር። የሆነ ሆኖ በጥዋቱ የፈሩት ጠሚር አብይ አህመድ አሊ መሠረታዊ አመክንዮ የአማራን ፖለቲካ ነበር። ምክንያታቸው የገዘፈም ቢሆን በተለይ በ 100 ቀናት ትጋታቸው ስውሩን ዬማንነታቸውን መጋረጃ የበጠረቀው የቅኔው ጎጃም ሙግት በጥዋቱ ድንብርብራቸውን አውጥቶት ነበር። ከ...