ከባዱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ፖለቲካ ነው። ቢፈራም፤ ጠላት ቢበዛበትም መንግሥት እስከ ሠራዊቱ ቢሰለፍበትም ያልተበገረው በዚህው ነው።

 

ባዱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ፖለቲካ ነው። ቢፈራም፤ ጠላት ቢበዛበትም መንግሥት እስከ ሠራዊቱ ቢሰለፍበትም ያልተበገረው በዚህው ነው።

 

"የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፦

እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ይጠይቃል።

(ምሳሌ ፲፮ )

 

 May be an image of 1 person and smiling

#አድማጭነት

#ዝቃታ

#ታዛዥነት

#ተመሪነትን

#ርህርህና

#አጽናኝነት

#አይዟችሁባይነት

#ሰዋዊነት መፍቀድ መርህ ይሁን። መዳኛም መከበሪያም መመረቂያም መበራከቻም። ዘለግ ያለ ነው ለታጋሽ ቅናውያን የተጣፈ ነው። ሸበላ የመደማመጥ ጊዜ ይሁንልን። አሜን።

ንዴት አደራችሁ ክብራት እና ክብሯን ወዳጆቼ። እንዴት ነን? ከምን ነን? የት ላይ ነን። የፋኖ ንቅናቄ ገዝፎ መነቃነቅ ከጀመረ ወዲህ በአማራ ፖለቲካ ላይ በግል በጓዳ ከምሟገታቸው ውጪ ትግሉን ሊያለዝ ወይንም ግብታዊ ሊያደርገው ይችላል በማለት እስኪሰክን ታግሼ ቆይቻለሁ። ወደፊትም በትዕግሥት ማዬቱ እና መጠበቁ በቂ ይመስለኛል።

እስክንድር ነጋንም ፋኖን እመራለሁ እንዳትል ብዬ ከእስር እንደተፈታ በስፋት ስጋቶቼን ዘርዝሬ ጽፌ ነበር። የጓዳው ሙግትንም እመክት ነበር። የሆነ ሆኖ በጥዋቱ የፈሩት ጠሚር አብይ አህመድ አሊ መሠረታዊ አመክንዮ የአማራን ፖለቲካ ነበር። ምክንያታቸው የገዘፈም ቢሆን በተለይ 100 ቀናት ትጋታቸው ስውሩን ዬማንነታቸውን መጋረጃ የበጠረቀው የቅኔው ጎጃም ሙግት በጥዋቱ ድንብርብራቸውን አውጥቶት ነበር። ከዛ ባህርዳር ላይ ያልተካሄደ አዝለኝ ጉባኤ አልነበረም።

ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እጅግ ግዙፋ በክብደቱ የአማራ ፖለቲካ ነው። የሚደፈር፤ የሚጨበጥ በመዳፍ አስገብቸዋለሁም የማይባል። ጦማሪ በፈቃዱ ሲያጣጥለው፤ ሲያቃለው በብራና ራዲዮም ሞግቼው ነበር። መክሰምም፤ መትነንም እንደማይችል፤ ሚሊዮን ዓይኖች እና ህሊናወች ዘብ አደሩ እንደሆኑ በወቅቱ ገልጬ ጽፌም ነበር።

 ግልጥ ከሚካሄደው አደባባይ ተጋድሎ ይልቅ ድምጣቸውን አጥፍተው በዝምታ ሰክነው በእርጋታ፤ ባለሞንቦጅቦጅከውስጣቸው የሚታገሉ፤ ለዝና ለሽልማት የማይተጉ፤ ግጭት ላይም ጊዜ የማያጠፋ ሙያ በልብ ሁነኛወች አሉት። እዩኝ እዩኝ የለም። በዝምታ በስክነት ሙያ በልብን ምራኝ ያሉ እንደማለት።

አማራ ተጋድሎ ሁለት የገዘፋ ጉዳዮቹ ወሳኝ ናቸው። አንዱ የማንነት፤ ሁለተኛው የህልውና። ሁለቱም ተደጋጋፊ እና ተዋዳጅ የትግል መስኮች ናቸው። ማህበራዊ መሠረቱን ያጣውም፤ የፋይናንስ አቅሙን ለማደለብ የሚያስበውም፤ ክብር እና ዝና የጣመውም፤ በአማራ ማገዶነት ኢትዮጵያን ማዳን ይቻላል ብሎ አድብቶ የሚታገለውም በር አልቦሹን የአማራ ተጋድሎ በአሻው መጠን ይተምበታል።

 አማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ማህበረ ዘውታወችን በጊዜ ያሰናብታቸዋል። በአቅሙ ልክ ያልሆኑት በራሳቸው ጊዜ ተዱለው በራሳቸው ጊዜ ይስፈነጠራሉ። ለምን? የሚስጢር ውህደት ስለማይኖር። በአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ዝናን የተጎናፀፋትም ዝናቸው አይቆይም። ይሸበሸባል። ምክንያቱም ከሚስጢሩ ህግጋት ጋር ስለሚተላለፋ።

ሌላ በኩል ደግሞ ደራሾች ጥድፊያ ላይ ስለሚሆኑ ከባቡሩ ይንጠባጠባሉ። ግልቢያ፤ ግርግር፤ ያልተገባ እሰጣ ገባ ለትግሉ ወላፈን ክፍሉም ልኩም አይደሉም። የአማራ የህልውና እና የማንነት ተጋድሎ ቤቢ ሲተር አያስፈልገውም። ጥገኝነት ይሁን ቅጥልጥ ሁነት አያስፈልገውም።

 ምክንያቱም እራሱን ችሎ ለመታገል፤ ይሁን ትግሉን ለመምራት መከራው ጥንካሬ እና ብርታት፤ ብልህነት እና ጥበብ አያጣምና። ተጋድሎው ክብደት ያመጣው አፍላ እና ወረት የማይሻ በመሆኑ ነው። ሰሞንኛ አይደለም። የትርታ እና የትውልድ ቀጣይ ባለአገርነት ዕውቅና የሚጠይቅ የነፃነት ተጋድሎ ነው። ተጋድሎው ሰባዕዊ መሆኑ እናም ኢትዮጵያን መስጥሮ ማያዙ ተጋድሎው ብረት መዝጊያ የሆኑ መሪወች፤ የማይናወጽ ትዕግሥት እና እርጋታ ያላቸው አስተዋይ ልጆች መሻቱ ነው።

ጋድሎው የኢቤንት መሰናዶ ዓይነት አይደለም። ተጋድሎ የገብያ ግርግር አይደለም። በአንድ ጉዳይ መክሮ የሚፈታ። ተጋድሎው ጥልቅ እናፍፁም ታጋሽነት እና ሰባዊነትን በተፈጥሮው ልክ ማስከበርን ይጠይቃል። ሞት ብቻ አይደለም ያለው። የሥነ ልቦና ትግልም፤ የመነቀል አደጋም ያንዣበበት በመሆኑ ቀበቶን ሆነ መቀነትን በሁለት ዙር ማጥበቅን ይጠይቃል።

ጋድሎው በለት ተለት ፕሮፖጋንዳ የሚበስል አመክንዮ የለውም። ዕውነት የፕሮፖጋንዳ ሠራዊት ስለማያስፈልጋት። የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ዕውነታዊ የሆነ የተጋድሎ ዓይነት ነው። ቤቱ መቃብር የሆነ ህዝብ የሚያደርገው ትግል ነውና። ይህን ንፁኃን ሰዋዊ የዓለም ዜጎች በጥልቀት ይረዱታል። ሰውነት ከጠፋ ማንነትም ህልውናም አይኖርም። አማራ ሰው ሆነህ አልተፈጠርክም። ሰው ተፈጥረህ የከወንካቸው የሥልጣኔ በረከቶችም የአንተ አይደሉም። በስውር ዝውውር ይደረግባቸዋል ነው ሚስጢሩ።

ማራ የመሠረታቸው ከተሞች፤ ተቋማት የታሪክ፤ የባህል፤ የትውፊት የበረከት፤ የሳይንስ እና የምርምር ስኬቶች ሁሉ በጠራ ፀሐይይወረሳሉ፤ ነገም የአንተ ትውልድ ጭንቅላት የሚፈጥራቸውግሎባል ታሳቢ፤ ታላሚ የፈጠራ አኗኗሪ ኩነቶች ሁሉ ገደብ ሊጣልባቸው ይገባል ነውፍልሚያው። ለዚህም ነው አንዱን ይዞ አንዱን አንጠልጥሎ ጉዞ ለተጋድሎው ልኩ አይደለም ብዬ ደፍሬ ስሞግት የቆዬሁት።

 

አማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ እንመራለን የሚሉ ቅን ዜጎች ሁሉ አማራን ከሞት፤ ከስጋት፤ ከጭንቀት መታደግ የመጀመሪያ ረድፍ መርሃቸው ሊሆን ይገባል።

 

ዬዘመናቱ አማራ ያለፈበት የመከራ ዓይነት በፍፁም በቃልም በምግባርም ሊደገም አይገባም። ለተጋድሎው የጭካኔ ውስኔ አረመኔነት ነው። በቃው ይህ ህዝብ። አታስፈራሩት። አትዋዋሉበት።

አማራ የማንነት እና የህልውናው ተጋድሎ ሚስጢር ላልገባቸው ወገኖች በርጋታ እና በስክነት ማስተማር ይገባል። እንጂ ሞት ሊፈረድባቸው ወይንም ስጋት ሊጣልባቸው አይገባም። የሚያጠፋ የአማራ ልጆች ቢኖሩ ማስተማር፤ መንገር እንጂ አንድም አማራ በራሱ ነፃ አውጪ ዛቻ ሊደርስበት፤ ይወገድ ተብሎ ሊወሰንበት አይገባም።

 

ህን የምትሉ መሪወች ወይንም ማህበራዊ አንቂወች ጥሞና ውሰዱ፤ ሱባኤ ግቡ። ያትግሉ መንፈስም ልካችሁ አለመሆኑን አውቃችሁ ፈቅዳችሁ በአቅማችሁ ልታገለግሉ የምትችሉበትን መስክ መምረጥ ግድ ይላል። እኔ እንዲህ አይነት ጨካኝ ሃሳብ ስሰማ መተኛትም መመገብም አልችልም። በራሱ አረመኔወች አማራ ሲሰቃይ ከማይ ሞቴን እመርጣለሁኝ። "ሸኙት፤ እንሸኜዋለን፤ እናጫውተዋለን፤ ይረሸን፤ ይወገድ።" ይህ የግራ ፖለቲካ ጦስ ከአማራ ፖለቲካ ፍፁም በሆነ ሆኔታ አክ ሊባል ይገባዋል።

 

አማራ ፖለቲካ አይደለም ለአማራ ህዝብ፤ ለኢትዮጵያ፤ ለመካከለኛው አፍሪካ ለዓለም ህዝብም ተስፋ መሆን የሚችለው ተፈጥሯዊ፤፦ሰባዕዊ፤ ሥርዓታዊ፤ ሞራላዊ፤ ስክነታዊ መሆን ሲችል ብቻ ነው። የአማራ ህዝብን ብታውቁት ሲፈጠር አምላኩን እና ሰውነቱን ፈርቶ አዳሪ ነው።

 

 ህግ አምላክ አንበል ነው የአማራ ህዝብ። በሬውን ሆይ! እያለ አክብሮ የሚይዝ ድንቅ ፍጥረት ነው የአማራ ህዝብ። አማራን ለመምራት በአማራ ህዝብ ተፈጥሮ እና ሞራል ልክ እራስን አርሞ መገኜትን ይጠይቃል።

 

አማራ ህዝብ ሰላም በራሱ ልጆች መታወክ የለበትም። በሌላ በኩል የአማራ ተጋድሎ ለዲሞክራሲም ቀና አሳቢ የሆነ ትግል ነው። ስለዚህ ገዢውን ይሁን፤ ገዢውን የዞግ ፓርቲ ብልጥግናን እንታገላለን የሚሉ ተጠዋሪ፤ ተቀላች፤ ተጠማኝ፤ ተቀናቃኝ፤ ተፎካካሪ፤ ተቃዋሚ ድርጅቶችን ፈቅዶ አባል፤ አካል ለሆኑትም መብታቸው መሆኑን መቀበል መርሃዊ ነው። የተሻለ ሃሳብ አፍልቆ የራስን ወገን ለራሱ ህልውና እንዲተጋ ማስቻል ብልህነትን፤ የአመራር ዊዝደምን ይጠይቃል። አበቶቻችን ምርቃታቸው ነበር። ፋኖ እኮ ከአባት የተወረሰ የህሊና ርስት የአማራ ቀይ የደም ሴል ነው።

 

ወንድም አቤ ቶክቻው ፋኖን ተውልን፤ ብሄራዊ ሰንደቅዓላማውን ተውልን ሲል በደጋጋሚ እሰማዋለሁኝ። ይህ የማይሆን ነው። አማራ አይደለህም፤ አማራም አትሁን ዓይነት ምልከታ ነው። የአማራ ህዝብ ብዙ በጣም ብዙ ረቂቅ አበርክቶች ለኢትዮጵያ አድርጓል። ከዛ ውስጥ አንዱ ፋኖ ነው።

 

ላው ብሄራዊ ሰንድቅዓላማን በሚመለከትም የአቤቾ መንግሥት ከማበሻ ጨርቅ ባላነስ ክብር የነፈገው ከመሆኑም በላይ የጠሚ አብይ አህመድ አንድም ፕሮጀክት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ጋር የተያያዘ አይደለም። በጣም ነው የሚጠዬፋት እራሱን አስችዬም ለአቤዋ ሙግት እሰራበታለሁ። እሱ ውስጡን አግኝቶ ደግፎ መታገሉ መብቱ ነው። ግን የእኛንውስጥነት ጀልሙን አይሆኑ የሆነ ምኞት ነው። የአማራን ፖለቲካ የሚከብደውም ኢትዮጵያን በመስጠሩ ነው። ሲመሰጥርም በሐሴት ነው አማራዬ። እና አቶ ወንድም አቤቾ በምንምታምር አማራዬ ፋኖን ሆነ ብሄራዊ ሰንድቅ ዓላማን አልቦሽ ትግል አንገት የሌለው ሰብዕና ይሆናል እና አያስበው ለማለት እሻለሁኝ። የኢህዴግ ዓርማየአማራ ሊሆን አይችልም። የኢትዮጵያም።

 

ሐምሌ 5 የጎንደር የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ በዛ ቋያ ዘመን ደፍሮ ይዞ የወጣውም ሚስጢሩን ነው። ሚስጢር ሲሳት ምርቃት ይነሳል። ምርቃት ሲነሳ ዊዝደም ይተናል። ይህን ፀረ አማራ፤ ፀረ ኢትዮጵያ፤ ፀረ አማርኛ ቋንቋ፦ ፀረ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ፤ ፀረ ከተማ ድርጅቶች ህወሃት እና ማህበረ ኦነግ ሙሉ50 ዓመት ዳክረውበታል። አማራ እና ሚስጢሩ ዛሬም ወደፊትም እንደተዋህዱ ይኖራሉ። የፈቀደ አብሮነቱ ይከበርለታል፦ በስተቀር ግን እኛነት ለበለሃሰብ አይተውም።

 

ሆነ ሆኖ የአማራ ፖለቲካ የመጀመሪያ የተጋድሎ ዘርፍ የግራ ፖለቲካ እና ሸቀጣሸቀጦቹ ሊሆን ይገባል። ወደ ተፈጥሯችን ወደ ርህርህና፤ ወደ ለጋሥነት፤ ወደ አይዟችሁ ባይነት፤ ወደ አጽናኝነት፤ ወደ ፈርኃ አላህ እና ወደ ፈርኃ እግዚአብሄርነት፤ ወደ ቤተሰብ አክባሪነት እና ረጂነት፤ ወደ ህብራዊ አብሮነት፤ ወደ አክባሪነት እና አድማጭነት፤ ወደ ፊደል ገበታነትአናባቢነት እና ተነባቢነት መመለስ ግድ ይላል። የአማራ ህዝብ በራሱ ልጆች ምን ይደርስብኛል ብሎ መፍራት አይኖርበትም። መስጋትም አይገባውም። ሙሉ ዓመት እኮ ስንት ፈላስፋ እና ሳይንቲስት፤ ስንት ሊቃውንት ገበረ???

 

ማዳን ይጀመር ትግሉ። ከማረጋጋት ይጀመር ትግሉ። ከአይዟችሁ ባይ ይጀመር ትግሉ። ከአጽናኝነት ይጀመር ትግሉ። ችኮላን ይጠዬፍ ትግሉ፦ ታጋሽነትን ይቀፍ ትግሉ። የአማራ ተጋድሎ የፋንታዚ ተጋድሎ አይደለም። ፍቱንነቱን በምግባሩ እና በግብሩ ሊያሳይ ይገባል። የትግሉ ህይወት ለዘመኑ መምህር ሊሆን ይገባል።

 

#መከወኛ

አቅም አታባክኑ። በአንድ ሃሳብ የማይመስልህ በሌላ ሊመስልህ ይችላል። ጊዜ ሰጥቶ፤ ማስተዋልን ውጦ፤ ቅንነትን ምራኝ ብሎ መራመድ ይገባል። መሪነት ብቻ ሳይሆን ተመሪነትም ይጠጣ። የስልክ፤ የማህበራዊ ግንኙነት ጥንቃቃቄ ይደረግበት። ዘለፋ፤ ስድብ፤ ንቀት፤ ማቃለል ለትግሉ ትንኝ ያደርጋል። የሰው ልጅክቡር ነው። አክብሮት ለአማራ ታጋዮች መርህ ሊሆን ይገባል።

መጨረሻ አበባው ፋኖ ቆሞ የመዋጋት አቅም የለውም ሲሉ አዳምጫለሁኝ። ከመቼ ወዲህ ይሆን ሽምቅ መደበኛ የውጊያ መስመር ገብቶ ታግሎ የሚያውቀው? ሽምቅን ከባድ የሚያደርገው ሚስጢርም ይህ ነው።

 

ላው ፋኖነትን ውስጡ ያደረገ ሁሉ መሳሪያ ያልታጠቀ ግን ተፈጥሯዊ ማንነቱን አክብሮ ልጠፋ አይገባም ብሎ በፆም በፀሎት በሰጊድ በሱባኤም የሚተጋ ይኖራል። እና ለመጠነ ሰፊው ጥቃት መጠነ ሰፊ የመከላከያ መስመሮች መኖራቸው ተፈጥሯዊ ነውና የጠሚ አብይ አህመድ ከፍተኛ መኮንኖች ሳያቃልሉ፤ ሳያገዝፋም በልኩ ዘመኑን ለማንበብ ቢሞክሩ ጥሩ ነው።

 

አማራ ታጋዮች መስዋዕትነት መቀነስ ብልህነት መሆኑን፤ መሪን ብቃቱን እና ሰብዕናው በሚፈቅደው ልክ መቀበል እና ለመመራትም መፍቀድ ይገባል።

የኔ ውዶች ዘለግካለው ፁሁፌ ጋር መሸቢያ ጊዜ። ደህና ሁኑልኝ። አሜን።

 

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

27/04/2024

 

ፍቅር ሲያልቅ ትዕግሥት ይሰደዳል።

ትዕግሥት ሲያልቅም ፍቅር ይሰደዳል።

ዕውነት ጋራጅ አትሻም።

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።