እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

 

እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።

„የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል። እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል። ምሳሌ 16 ቁጥር 9“

 

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች። 




ለእኔ ሰማዓት ናት አጊቱ! ጀግናዬም!

„A cheese making business in the Alps is the project of Ethiopian entrepreneur, Agitu Ideo Gudeta. Forced to flee Ethiopia, she has built a new life in Italy.“

 

·       እፍታ።

የተወሰናችሁት እንደሚቆርጣችሁ፤ እንደሚፈልጣችሁ፤ እንደሚጨንቃችሁ፤ እንደሚያናዳችሁ አውቃለሁኝ ይህ መጣጥፌ። ዛር ካለም ጉሬያ ይፈቀዳል።  

 

በፓን አፍሪካኒስቱ ብላቴ ጌታ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን መታሰቢያ ድህረ ገፅ፤ የራዲዮ ፕሮግራም ምስረታ እና ዝግጅት ስጀምረው እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ በጣም ብዙ ተዘርዝሮ የማያልቅ መከራን ተቀብዬበታለሁኝ። እዬተቀበልኩበትም ነው። በዬትኛውም ሁኔታ ታግቻለሁኝ። የእኔን ሥም መጥራት እኔን ማድነቅ ማመስገን ውግዝ ከአርዮስ ነው።

 

ተዘርዣለሁኝ። ሥሜ ጠፍቷል። ተወግዣለሁኝ። ሁሉንም መከራ ፈቅጄ እና ወድጄ አስተናግደዋለሁኝ። ወደፊትም። ዕምነቴ ዕውነት እና መርህ ነው። መንገዴ ተፈጥሯዊነት፤ ሰዋዊነት፤ እኛነት ነው። ከዚህ ፈቅ የለም። የራሴ ጌታ እራሴ፤ የራሴ እንደራሴ እኔው እራሴ ነኝ። እኔ „እኔን“ መሆን ከተሳነው እኔ „እኔን“ ያሰነባተዋል። ይህ ደግሞ አይፈቀድለትም።

 

ዛሬ እንዲህ ልትክደን በወት ብርቱካን ሚዲቅሳም ዕወቅና ላይ በመትጋቴ እንዲሁ አሳሬን በልቸበታለሁኝ። በብላቴውም፤ በብርቴም፤ በተዋህዶ ዕምነቴም ሦስቱም ተከስሼ ነበር። አክራሪ ኦሮሞ፤ አክራሪ ተዋህዶ ተብዬ። ራዲዮ ጣቢያዬን ለማዘጋት ሙከራ ተደርጓል። ድህረ ገጼን ቦርዱን በትነውታል።

 

ራዲዮ ጣቢያው ግን አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ሙሁር የዩንቨርስቲ መምህር ድህረ ገጼን እና ራዲዮዬን አዳምጠው ምንም ዓይነት የ አክራሪ ኦሮሞነት፤ ምንም ዓይነት የተዋህዶ አክራሪነት እንጥፍጣፊ እንደሌለው ስለ ፍትህ፤ ስለ ነጻነት፤ ስለ እኩልነት የሚታገል መሆኑን ስለመሰከሩ ይህን የራዲዮ ሎራ ኮሚሽን ተቀበለው።

 

መልስ የተሰጠበት ሰነዱም ከእጄ ይገኛል። እኔ እኮ ጎንደር ከተማ ከታወቁ ባላባቶች ነው የተፈጠርኩት። ምንም ዓይነት ብጣቂ የ ኦሮሞ ዘርነት የለንም። በ ኢትዮጵያዊነት ማንነት ውስጥ ከተሰላ ብቻ እንደዛ ሊሆን ይችላል። እንጂ እኔን በ ኦነግ ፖለቲካ የሚያስከስስ ምንም ነገር አልነበረም። ግን አቅም የለሹ አቅም ብቅ ሲል ይርዳል። ከንቱን።

 

ይኸው የብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ራዲዮ ነፍሴ እስካለች ድረስ በወር ሁለት ጊዜ በዕለተ ሃሙስ ከ15.00 እስከ 16.00 ሰዓት ይተላለፋል። ሥሙ እንደ አሰብኩት አለ። ጊዜው ያላችሁ ላይፍ ላይ ቀጣዩ ፕሮግራም 14/01/2021 ከ15.00/16. 00 መከታተል ትችላላችሁ።

 

ባያደናቅፉኝ የግንቦት 7 አረሞች ይህ ራዲዮ ጣቢያና ሆም ፔጅ ሲዊዝ ውስጥ ካለው ኮሚኒቲ ሚዲያ ተመርጦ „ሚዲያ ራሱን ይሰራል“ በሚል የጀርመን ተናጋሪ ክ/አገራት ብሄራዊ ጉባኤ  በፓናል ዲስከሽኑ ላይ ስብሰባ ላይ የፓናል አቅራቢ ሆኖ ነበር። ሌላም ሌላም። ያን ጊዜ ለዛውም ስደተኛ ካንፕ ውስጥ ሆኜ ነው ራዲዮውም ድህረ ገጹም የተጀመረው።

 

·       የአውሮፓ ስደት መከራ ነው።

የሚቀላቸው ትዳር መስርተው ኑሮን መግፋት ይችላሉ። ይህን ለማይሹ ግን ውሃ ያዘለ ተራራ መሸከም ማለት ነው። አንዲት ሴት ይህን ሁሉ መከራ ችላ ትልቅ አውሮፓያዊ ተቋም ከፍታ በ አጭር ጊዜ በ10 ዓመት ውስጥ እዚህ ደርሳ ማዬት ለኢትዮጵያ ኩራት፤ ክብር፤ ሞገስ ነው።

 

ሳቂታዋ አጊቱ ራሷ ተቋም ናት። ሊቅ ናት። የፈጠራ ባለቤትም ናት። እንሰሳ የሚወድ ሩህሩህም ነው። እኛ ለሰው እንኳን የለንም። ነጥፈናል። ለብትን አፈር እንቀናለን። ከሞት በኋላ ላለ ክብርም እርር ድብን እንላለን። እናሳዝናለን።

 

አሁን ሰማዕቷ አለፈች። ከዚህ በፊት ማንም አያወቃትም። አውሮፓ ግን ጠንቅቆ ያውቃታል። የአውሮፓ ግብይቱም፤ ኑሮውም ሉላዊ ነውና። የኦሮሞ ሚዲያዎች ለነፍስ ማጥፋት፤ ለግጭት ሌት ተቀን ይተጋሉ። ቅማንት እያሉ ሲያላዝኑ ውለው ያድራሉ። OMN ሆነ OBN ይህችን ጀግና ግን አያውቋትም። ውርዴት ነው። ሃፍረት። ቢሞቱ ይሻላቸዋል።

 

የመደመር አጤው ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አውሮፓ ነበሩ፤ ጣሊያንም ነበሩ። ሥሟን አያውቋትም። ቢያውቁ ካወደሷቸው‘ ከሾሟቸው ከሸለሟቸው አንስት የዞጋቸው ሰዎች ማህል ትሆን ነበር። ቢያንስ ለኖቤል ሽልማት የክብር እንግዳቸው አድርገው ኖሮይ እንድትገኝ ያደርጉ ነበር።

 

ነገር ግን ትዝም አትላቸውም። እነ ኦሞ ፈርስቱ አቶ ሌንጮ ለታ ኖሮይ ነበሩ ለረጅም ጊዜ ፌስታላቸውን ተሸክመው፤ የሜጫው ንጉሥ ጃዋር መሃመድ አውሮፓ ለእረፍ ሲጓጓዝ ነበር። አያውቃትም።

 

የዴሞግራፊ ማህንዲሱ አቶ ለማ መገርሳ አውሮፓም አሜሪካም ተዘዋውረው ፖለቲከኞችን ሲያገኙ ይህቺ ዕንቁ ሴት ትዝ አላለቻቸውም። ለንደንም በኦነጋዊነት የሚሠሩ ነበሩ እነሱም ትዝ ብላቸው አታውቅም። እነ የ300ሺህ ንግሥና ምኞተኛ ዲታው አቶ ሌንጮ ባቲ የ አውሮፓ ከግንቦት 7 ጋር የአውሮፓ ሙሽራ ነበሩ በዘመነ አገራዊ ንቅናቄ ዶር ዲማ ነግዖን ጨምሮ። ስለ ኦሮሞ ተቆርቋሪነት ከታሰብ ይህቺ ብርቱ ወጣት አስታውሰዋት አያውቁም። ከነመፈጠሯም። ማህበረ - ማፈሪያ።

 

ኢንባሲው በመክሊቷ ልክ አያውቃትም። ሌሎችም ሚዲያዎች አያውቋትም እንዲሁ። አንድ ቀን ትዝ ብላቸው አታውቅም። ዛሬ ደግሞ የፖለቲካ ሸቀጥ ለማሟሟቅ ሁሉም ይፈልጓታል። ይህ ያስተዛዝባል። ውርዴትም ነው። ይልቅ የጣሊያን መንግሥት እና ህዝብ ሊመሰግን፤ ሊከበር ይገባል።

 

ይህን የመሰለ ዕድል ሰጥቶ እዚህ እርከን ላይ ያደረሳት። የት ነሽ፤ ወዴት ነሽ ሳትባል። ክድን ብላ በመታተሯ ተቀናቃኝም ብዙ ሳይኖርባት እዚህ ደረጃ ደርሳ ነበር። አሁን በአጭሩ ብትቀጭም። ሲዊዝ ብትሆን አንዲት ስንዝር አያራምዷትም ነበር እነ ማህበረ ደራጎን። የዛሬ የ ኦዳ ሥርዕዎ ምንግሥት የቤተ - መንግሥት ግብረኛ እና አሸብሻቢዎች።

 

·       እም።  

 

ማህበረ ኦነግ ሆነ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር እንደምን ቀና ብለው ተፍተፍ እንደሚሉ ማዬት ነው የማያዋቅቷን ዜጋቸውን። ገመናው ብዙ ነው። ለነገሩ ኢትዮጵያ እኳ ከዓለም ተለይታ ዜጋ የሌለባት አገር ናት። እፈረት ያልሰራላቸው፤ ዓይናቸውን በጥሬጨው ዬታጠቡ ዛሬ ዜጋችን ብለው የሃዘን መግለጫም ሴሪሞኒም ያሰናዳሉ።  

 

እዛው አዲስ አበባ ላይ ቤታቸው ፈርሶ ስቃይ ውስጥ ያሉ የጀግና አብዲሳ አጋ ቤተሰቦች አሉ። የቤተ መንግሥቱ ግብረ ሰላም አስቦቸው አያውቅም። ጹሑፍ ሁሉ ጽፌ አሳስቤም ነበር። ትዝ ብለዋቸው አያውቁም። ኢትዮጵያዊነት በጥርስ የተያዘ፤ እንዲጠፋ የሚፈለግ ተፈሪ ተደሞ ነውና።

 

ያው እነሱ በጥብቆ ስለሚያስቡ ቢያንስ ይህችን የትጋት እመቤት እንደምን አረስተዋት ኖሩ? ብሄራዊ፤ ሉላዊ ጀግና ትዝ ብሎት አያውቅም ከንቱው ማህበረ - ኦነግ። እንዲያውም ላፒስ ይዞ ሲፍቅ፤ ሲፈግፍግ ውሎ ያድራል።

 

ይህች ጀግና ለኮሚኒቲው እጅግ አስፈላጊ፤ እጅግ ተግባቢ፤ እጅግ ወሳኝ ሰው እንደ ነበረች ዘገባው ያመለክታል። ዶቼቤሌ በአንድ ወቅት ከዘገበው እንደተረዳሁት። የገሬዎችን የቴሌቪዥን ፕሮግራም እዚህ ስለምከታተል እጅግ አድካሚ መሆኑን አውቃለሁኝ። ለሴት፤ በባዕድ አገር፤ ለስደተኛ፤ ብቻ ተሁኖ። እውነት እህት አጊቱ ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራች ጀግና ሴት ነበረች።

 

·       የቀብር ሥርዓት እሰጣ ገባ።  

·        

ስለቀብር ሥርዓቷ በወጣው ትልም ላይ ላይ ኢትዮጵያውያን እዬተወያዩበትን ነው በአዎንታዊም፤ በአሉታዊም። አሉታዊው የግፉ ጠረን አውሬያዊ ስለሆነ ከዛ በመነሳት ነው። ይህ ይገባኛል። ለክፉነት ፉክክር አያስፈልገውም። እንደምን አጣናት መባል ሲገባ ላይ ታች በሚዘል አመክንዮ አቅም ማፍሰስ አለመታደል ነው።

 

 ሊቀ - ትጉኃን አጊቱ ኦነጋዊው ኦህዴድ ለሚፈጽመው የጭካኔ በደል በደል ማካካሻ፤ መደጎሚያ ልትሆን አይገባም። እሷ ዓራት ዓይናማ ድንግል ገበሬ ነበረች። ከዚህ ከዝንቁ፤ ከአውሬው እሰጣ ገባ አልነበረችም። ለዛውም በሰው አገር ለፍቶ አዳሪ ባተሌ ሴት ናት። የፍዬል እርባታን የምትመራ ንጹህ ገበሬ ናት። ምኑን እና ምኑን እንደምታገናኙት ግራ ይገባኛል። እንዲገባኝም አልፈቅድለትም። እነሱ ሰው መሆን ሲሳናቸው ሌላው ሰው መሆኑን ሲረሳ ትውልድ ዬት ይጠጋ? ምንስ የተሻለ ተስፋ ይናፍቀው? እንዲህ የተሻለ አስተሳሰብ ድጥ እና ልጥ ሲሆን።

አቀበት -  ቁልቁለት -  ወርዳ፤ ጣሻ ጥሳ፤ ዳጡን፤ ብርዱን በረዶውን ተቋቁማ፤ በሴት ክንድ ወጥታ ወርዳ ልጆቿን ታሳድጋለች። እጅግ አድካሚ መስክ ነው የመረጠቸው ግብርና ለሴት ልጅ። እርግጥ ነው ልጆቿ ወተት ይሰጧታላል። ክፉ ነገር ተናግረው አያስከፋትም። ወተት ብቻ ይሰቷታል። ያን ወደ ችዝ ትቀይር እና ለገብያ ታውላለች። የመንገድ ላይ ገብያ የገበሬዎች አለ እዚህ አውሮፓ።

እኔ ከምኖርበት ከተማ ቪንተርቱር ማክሰኞ ጥዋት አለ። ፍሬሽ የገበሬ ምርት በቀጥታ ለማግኜት እዛ መሄድ ይቻላል። ልክ እንደ ሲዊዝ ጣሊያንም አለ። እንደዛም ትሰራለች። የመንገድ ላይ ሱቅም አላት። ትልቅ ፕሮጀክት ነው የምትመራው። እህት አጊቱ ተፈጥሯዊ ናት። ተፈጥሯዊነቷ እነሰሶችን እንድታፈቀር አድርጓታል።

ጠረናቸው ያጓጓታል፤ ጠረናቸውን ምጥጥ አድርጋ ጠጥታ ትረካለች። ልጆቿን አቅፍ አድርጋ ትስማቸዋለች። ህይወቷ ናቸው። ይህ ሰብዕናዋ ዓለም ከሚተራመሰብት ኳኳቴ እና ጓጓቴ ውጭ አድርጓታል። ለእሷ አለሟ ፍዬሎቿ ነበሩ። አሁን ፍዬሎቿ ተበትናዋል። እናታቸውን፤ ከብካቢያቸውን አጥተዋል። ያሳዝናሉ። እንዲህ በግፍ እናታቸውን ሲነጠቁ።

 

ያን እጅግ አድካሚ ሥራ በፍቅር፤ በትጋት፤ በብርታት የምትሠራ ፍልቅልቋ አጊቱ እጅግ ልዩ ዕጹብ ድንቅ አብነት እህት ናት። የኦህዴድ ፖለቲካ ተውት እና ይህቺ ታታሪ እህት እንዲህ በአጭር ጊዜ እዚህ ደረጃ ደርሳ ግን ቅጥፍ ስትል አታሳዝንም ወይ? ግን እኛ ምንድን ነን? እኛስ ማን ነን? አዬ የኢትዮጵያዊነት ፈተና። አጊቱ እኮ አዲስ አበቤ ናት። በቃ።

የማዝነው በሙሉ ዕድሜ ያለው ሁሉ ከኦሮሙማ ፖለቲካ ጋር ፉክክር ገብቷል። የእነሱ ጭካኔ ለመጸዬፍ መጀመሪያ ሰው መሆን ይጠይቃል። የአጊቱ አሰቃቂ አገዳደል ሊቆጨን፤ ሊያንገበግበን፤ ጥቃቷን የእኔ ልንለው ይገባል። ስለ ፍርድ ሂደቱም ልንከታተልላት ይገባል። እርግጥ የፍትህ አገር ላይ ስለነበረች እውነተኛውን ፍትህ ታገኛለች።

 

አለፈች እኮ። ደግምን አናያትም። ደግመን አናገኛትም። የትም የማናውቃት ሞቷ ክብር ሊያገኝ ነው፤ ሥጋዋ በባዕቷ ሊያርፍ ነው ብሎ እሰጣ ገባ መግባት መታመም ነው። ሰውነት እንዲህ የከሰለበት ዘመን እኔ በዘመኔ አይቼ አላውቅም። እያፈርኩ ነው እኔ እራሴ። ነጮች ቢሰሙ ምን ይሉን ይሆን? አብረን እንፈር።  

 

·       እኛ ኩፍትርትር ነው ያልነው። ጭብጦ!

ጭብጥብጥ ነው ያልነው። ሰብዕናችን ኩፍትርትር ነው ያለው። ሰው ለመሆን ለአቅመ አዳም ሆነ ለአቅመ ህይዋን አልደረስንም። ባለቅኔው ጎንደሬ ሲቃኝ „ሸማ በዬዘርፉ ይለበሳል“ ይላል።

አጊቱ እና የኦሮሙማ የዘር ማጽዳት፤ የዘር ጭፍጨፋ፤ የመታበይ ዳንኪራ፤ የአማራሩ አቅለቢስነት እና ጭካኔ ከአጊቱ የሉላዊ የክብር ልዕልና ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም። አጊቱ ለአውሮፓ የሥነ ምግብ ፍልስፍና ልዕልት ናት።

 

ጥቁር ጥቁር ቀለም ነው፤ ነጭም ነጭ ቀለም ነው። ብዙው ሰው የደላው ነው። የአውሮፓ ስደት ቀላል የስደት ዓይነት አይደለም። ጣሊያን ውስጥ ብዙ ኢትዮጵውያን መንገድ ላይ እንዳሉ እዛ ደርሰው የመጡ ወገኖቼ ነግረውኛል ለአውሮፓው የ እግር ኳስ ውድድር ሄደው የነበሩ።

 

ከዛ ወጥታ እዚህ መድረስ የሰማይ ታምር ነው። ድንቅ - ብርቱ - ትጉህ - ታታሪ - ወጣት - ሳቂተኛ - ቅኔ እህት ማጣቴ እኔ አሳዝኖኛል። ወስጤ እርር ብሏል። ጥቃቱም ይቆጠቁጠኛል። ጥቃት አልወድም። ነፍስ ይማር እማክብርሽ እህቴ አጊቱ።   

·       ብትክትኮች።

ምን አለበት ቢያንስ ሃዘንን እንኳን ከፖለቲካ ኳኳቴ እረፈት ብንሰጠው። ያልታደልን ብኩኖች። ብትክትኮች ነን።

 

አንድ ግራጫማ ጸጉር፤ አንድ ተፈሪ ተው የሚል አበው የጠፋበት አገር። ከበቀል፤ ከቂም፤ ከቁርሾ ጋር ሳይፋቱ አገርም ሃይማኖትም የለም። የሚኖረው ምድረ በዳነት።

ቢያንስ ነፍሷን ስለምን እረፈት እንነሳዋለን? ቢያንስ? እሷ ከምኑም አልነበረችም። ወደፊትም አትኖርም። አበቃ። አለፈች እኮ።

 

ባለፈው አሜሪካን አገር አንድ ጥቁር በግፍ ተገደለ ብለን አዝነን አልነበረም ወይ? ፎቶውን ሁሉ ለጥፈን ነበር። ለመሆኑ ስንት ጊዜ የውሸት ሰዎች ሆነን እንዘልቀው ይሆን? የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቋቅ እያለኝ ነው። ድሪቶው ዝክንትሉም በዛበት።

 

·       ምርኩዝ አጫጭር ቪዲዮዎች።

https://www.youtube.com/watch?v=2gu2tnijq5E

Il richiamo delle capre felici

Aug 30, 2015

3618SHARESAVE

https://www.youtube.com/watch?v=fMOjAh11P3g

Dall'Etiopia al Trentino, la battaglia di Agi per la capra locale

Nov 6, 2014

1K36SHARESAVE

https://www.youtube.com/watch?v=3YGmcH_t868

Aggressioni razziste ad allevatrice etiope in Trentino. La sua testimonianza

Aug 28, 2018

https://www.youtube.com/watch?v=CF0nQXrEJ30

Making cheese in the Alps - a story of integration | DW Documentary

Mar 8, 2019

8.5K311SHARESAVE

ግልጽ እና ቀጥተኛ ለኮሚኒቲው ወሳኝ የሆነች ሴት ናት ሳቂተኛ አጊቱ

A cheese making business in the Alps is the project of Ethiopian entrepreneur, Agitu Ideo Gudeta. Forced to flee Ethiopia, she has built a new life in Italy.

https://www.youtube.com/watch?v=4x0AtV4zWF4

Alemneh Wase BeZehabesha - (አለምነህ ዋሴ በዘ-ሐበሻ) - እኔን እህቴ! - ኢትዮጵያዊት በአልፕስ

Dec 31, 2020

1.9K65SHARESAVE

https://zehabesha.com/amharic/archives/114050

ነብስ ይማር አጊቱ ጉደታ ሰመረ አለሙ

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

ለእኔስ ሰው መሆን ይበቃኛል!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

አብይ ኬኛ መቅድም።