ልጥፎች

ከማርች 19, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አዲስ አበባዬ የልዕልት ሉሲዬ ዬድንቅነሽም ናት!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  አዲስ አበባዬ የልዕልት  ሉሲዬ ዬድንቅነሽም ናት! „አንተን ማወቅ ፍጹም ክብር ናትና፤ አንተንም ማወቅ የነፍስ ክብር ናትና።“ መጽሐፈ ጥበብ ምዕራፍ ፲፭ ቁጥር ፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19.03.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ጠላትም ወዳጅም እንዲያውቀው አይለያዩም! ቅኖቹ ታዳሚዎቼ እንዴት ቆያችሁልኝ? ሰሞኑን የሉሲ ጉዞ የሚል አንድ ቡድን በመላ ኢትዮጵያ ይንቀሳቀሳል። የተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች በማይገኙበት ሁሉ ይለፍ ተስጥቶት ተልዕኮው ከተሳካ እዬሞከረ ነው … ለህሊና አጠባ ፕሮፖጋንዳ ሳይሆን መሬት የያዝ ተቋም ያስፈልገዋል። በዓዋጅ የሰው ህሊና አይታጠብም። በመሆን ውስጥ በተገኜ ቃል እና ተግባር ብቻ ነው ህሊና ሊጸዳ የሚችለው። የስሞታ ፖለቲካ በበቀል በሚጋገርበት በዚህ ወቅት አፍሶ መልቀም፤ ለቅሞ ማፍሰስ ከመሆን የዘለለ ነገር አይኖርም። በሳቢያ ላይ አትኩሮት ዘላቂ መፍትሄ አያስገኝም፤ በምክንያታዊ ችግሮች ከራስ የጀመረ ለውጥ ነው የውስጥ ሰላም ማምጣት የሚቻለው። መጀመሪያ የየትኛወም ሰላም የጉዞው አባልተኛው እራሱ በሰላሙ ውስጥ ስለመሆኑ ራሱን ያቻለ ሞጋች አመክንዮ ነው።  ኢትዮጵያዊነት ሳይቀበሉ በዕምነት ደረጃ፤ የኢትዮጵያን ሰላም ማስከበር አይቻልም። ልክ እንደ በዓዋጅ እንደተቋቋመው የእርቅና ኮሚሽን እና ማበርተኞቹ አይነት ማለት ነው። እነሱ እራሳቸው ከራሳቸው እና ከተልዕኮው እንብርት ከ ኢትዮጵያዊነት ጋር ምን ያህል እንደታረቁ ልብ እና ኩላሊት የሚመረምረው ፈጣሪ ያውቀዋል። ኢትዮጵያ በጎርፍ ፖለቲካ ስታታመስ ባጅታ አሁንም አዋጁም፤ ኮሚቴውም፤ ቡድኑም የሚመሰረተው በዛው በሸፈተ ልብ መንፈስ ነ...