አዲስ አበባዬ የልዕልት ሉሲዬ ዬድንቅነሽም ናት!


እንኳን ደህና መጡልኝ።

አዲስ አበባዬ የልዕልት 
ሉሲዬ ዬድንቅነሽም ናት!
„አንተን ማወቅ ፍጹም ክብር ናትና፤
አንተንም ማወቅ የነፍስ ክብር ናትና።“
መጽሐፈ ጥበብ ምዕራፍ ፲፭ ቁጥር ፫
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
19.03.2019
ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።
ጠላትም ወዳጅም እንዲያውቀው አይለያዩም!


ቅኖቹ ታዳሚዎቼ እንዴት ቆያችሁልኝ? ሰሞኑን የሉሲ ጉዞ የሚል አንድ ቡድን በመላ ኢትዮጵያ ይንቀሳቀሳል። የተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች በማይገኙበት ሁሉ ይለፍ ተስጥቶት ተልዕኮው ከተሳካ እዬሞከረ ነው … ለህሊና አጠባ ፕሮፖጋንዳ ሳይሆን መሬት የያዝ ተቋም ያስፈልገዋል።

በዓዋጅ የሰው ህሊና አይታጠብም። በመሆን ውስጥ በተገኜ ቃል እና ተግባር ብቻ ነው ህሊና ሊጸዳ የሚችለው። የስሞታ ፖለቲካ በበቀል በሚጋገርበት በዚህ ወቅት አፍሶ መልቀም፤ ለቅሞ ማፍሰስ ከመሆን የዘለለ ነገር አይኖርም።

በሳቢያ ላይ አትኩሮት ዘላቂ መፍትሄ አያስገኝም፤ በምክንያታዊ ችግሮች ከራስ የጀመረ ለውጥ ነው የውስጥ ሰላም ማምጣት የሚቻለው። መጀመሪያ የየትኛወም ሰላም የጉዞው አባልተኛው እራሱ በሰላሙ ውስጥ ስለመሆኑ ራሱን ያቻለ ሞጋች አመክንዮ ነው።

 ኢትዮጵያዊነት ሳይቀበሉ በዕምነት ደረጃ፤ የኢትዮጵያን ሰላም ማስከበር አይቻልም።
ልክ እንደ በዓዋጅ እንደተቋቋመው የእርቅና ኮሚሽን እና ማበርተኞቹ አይነት ማለት ነው። እነሱ እራሳቸው ከራሳቸው እና ከተልዕኮው እንብርት ከ ኢትዮጵያዊነት ጋር ምን ያህል እንደታረቁ ልብ እና ኩላሊት የሚመረምረው ፈጣሪ ያውቀዋል።

ኢትዮጵያ በጎርፍ ፖለቲካ ስታታመስ ባጅታ አሁንም አዋጁም፤ ኮሚቴውም፤ ቡድኑም የሚመሰረተው በዛው በሸፈተ ልብ መንፈስ ነው። በዛ ላይ የተቆለለው ዕዳ እያለ መውጣት በሚገባው እና አትራፊው በሆነው መንገድ ከማተኮር ታይታ ተኮር ክንውን ለዘላቂ ስኬት ፈጽሞ አያበቃም። 

መጀመሪያ መሪው ኢህአዴግ ሆነ ገዢው ድርጅት ኦዴፓ ከ ኢትዮጵያዊነት ጋር ይታረቅ። የሚያቅደው፤ የሚያስወስነው፤ የሚያቋቁመው፤ የሚሾመው የሚሸለመው በሸፈተ ልቦና ከሆነ መፍረክረኩ አይቀሬ ነው። የህግ ተቋማት እውነትን ደፍረው ከውሳኔ ሳይደረሱ በቀጠሮ ዶሴ የኩሬ ውሃ የተሆነበትም ለዚህ ነው። ደመ ከልብ ዜጎች ነገር ተረስቶ፤ ወይንም ተዘሎ ማለት ነው። ከነዛ ሰማዕታት የሚፈጠሩት ልጆች ወላጆቻቸው ሲገደሉ ዜግነታቸው ተሰርዘዟለኝ። 

ለ እኔ እንዲያውም ይህን „ጉዙ ሉሲን“ „ከጣና ኬኛ“ ግብዕት ለይቼ አላዬውም።  ኦነግን ዓላማ በመንግሥት ደረጃ ለማስፈጸም አፍዝ አደንዝዝ ነው ብዬ ነው እማስበው። ይልቅ ጉዞ አድዋ ልቤን ይገዛዋል። አዲስ ትውልድ አድን ፍልስፍናም ነው። ሥያሜው ግን „ሉሲ ጉዞ“ መባሉ ያው ከሚቃረኑት የኢትዮጵያ ታሪክ ጋር ሳይወዱ እያጓጓጠቸውም ኦዴፓዎች እንዲውጡት የሚያደርጋቸው ሃቅ ነው።

ለአንድ መቶ ዓመት ባለታሪኮች ጉዞ ሉሲ የጨዋታ ማሟያ ከመሆን በስተቀር ምናቸው ናት - ወደ ዕውነቱ ማህለቅ ሲመጣ? ቡድኑን ያደራጀውም የሚመራውም በዚህው ኢትዮጵያን ከመኮነን ጨርሶ ለማፍለስ በመፎካካር ላይ ካለ መንፈስ መርሃ መንግሥት የወጣ ነው። የ አትላንታው ቻፕተር ነው እዬተፈጸመ የሚገኘው ከልብ ሆኖ ላስተዋለው።

ለዛውም „በ ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው“ በተገኜ የምልዕት የድጋፍ መዋለ መንፈስ … ይህን ሲያስቡት ከግፍም በላይ ነው … ከበደልም በላይ ነው፤ እያንዳንዳችን አፈሰሰስነው መዋለ መንፈስ ለኦነግ አገር ምሰረታ ሂደት ስኬት መደላድልነት ነበር። ራስን ለማፈረስ ያን ያህል ቀን ከሌት ተጋን … ማፈሪያዎች ነን። እነ አቶ ሌንጮ ለታ፤ እነ አቶ ዳውድ ኢብሳ እኛ ባፈሰሰነው የመንፈስ ሃብት እነሱ ተንፈራሰሱበት …

አሁን የሚታዬው ሁሉ እሷን ለማፍረስ ነው በሜጫ ሱናሜ ተጥለቅለቁ እዬተባልን ያለነው፤ አይደለም ወይ ? ነው እንጂ የምን ዳር ዳር ነው። አሁን አሁን ደግሞ ድፍረቱ እዬሸሼ እንደተለመደው የተያዘ የተረዘዘው ሁሉ ማስፈራሪያ፤ ማስጠንቃቂያ ማሸማቀቂያ እዬተሰጠው ነው።

ሞግቱኝ ያለው ሃያሉ የአብይ መንፈስ አሁን የስሞታ ቤተኛ ሆኖ እያዬነው ነው። ያጣ የነጣ ቢል ምንም አልነበረም፤ ያለው የነበረው ደግሞ እንደገና የምሾ ተጠዋሪ መሆን ግን አለመታደል እንጂ ሌላ ምን ይባላል … ሚዲያ እንደጦር እዬተፈራ ነው።

ሰው ሃሳቡን ለመግለጽ እዬተሸማቀቀ ነው። ለምን? እውነት ክህደት ስለተፈረደባት፤ መታምን ክህደት ስለተፈጸመበት፤ ቃል ስለተነነ … „ኢትዮጵያ ታድጋለች፤ ትበለጽጋላች፤ ትለወጣለችም፤ ከዚህም ታልፎ የቦረና እና የዋልድባ ምህዋራዊ ቅርስ ያደነቀ፤ የመሰከረ ድምጽ ዛሬ ደግሞ ለአንድ ኮንዲኒዬም ቤት ልጆቹን አሰልፎ ሜጫን ጥግ አስደርጓል። ቄሮ ድረሰኝል ሆኗል ለውሳኔዬ ጉዝጓዝ ሁንልኝ አስፈራራልኝ ሉሲንም ጨምርህ መንፈሳን አናውጣልኝ ሆኗል። በሌላ በኩል ደግሞ „ጉዞ ሉሲ“ ተጀምሯል …

የሆነ ሆኖ ሉሲም መናህሪያ ከተማ ያስፈልጋታል። አዲስ አባባ የሉሲም መናህሪያ ናት። የእናት ሉሲ ድንቅነሽ ድንቅም ናት አዲስ አበባ። ይህም ማለት ሉሲ እናት እማትሆነው የዓለም ዜጋ ስሌለ አዲስ አባባ የዓለም ዜጋ ሁሉ መናህሪያቸው ናት ማለት ነው። ስለሆነም ከከፋ ከከፋ ግሎባል አላይንስ ይፈጠርበታል።

አዲስ አባባ የሉሲ ቅርስም ውርስም መናህሪያ መዲና ናት እና። ዝም የሚባለው እዮባዊነት ስለተዋጠ ነው እንጂ በቀደመው መልክ ኢህአዴግ ይሁን ማንም ደፍጣጭ ሃይል አና ካለ የሚገድ አይኖርም።

የራስ ወገን ስለምንለው ፍሬ ነገር ባያደምጥ፤ ሌላው ስለሰው ጭንቅ የሚለው፤ ስለሴቶች ጭንቀት የሚገደው አለን። ጥሪት አይጠፋም - ለመደመጥ። እርሾም አለ። ሉሲን / ድንቅነሽን ያህል እናት አስቀምጦ ስለ ኮንደኒዬም ቤት ትርኪምርኪነት ነው … አሁን እኔ እማዬው።  

አለቃዬ አቶ አንድርያ ጋሰር „እኔ የተፈጠሩት ከሉሲ ነው“ ይለኝ ነበር። ሲዊዛዊ ነው። እና በህይወቱ ኢትዮጵያ ቢሄድ ሊይ የሚፈለገውም የሉሲን ዕትብት ባዕት አፋርንና አዲስ አበባን ስለመሆኑ ገልፆልኛል። ይህን ያህል የዓለም ህዝብ የእኔ የሚላትን ኢትዮጵያን ዛሬ ደግሞ እሷን ለማፈረስ የሚንጫ ሱናሜ በህግ ተፈቅዷለኝ።  

ስለሆነም የጹሁፌ ጭብጥ ልዕልት ሉሲን ድንቅነሽን ሜንጫ ይዞ የተነሳው ይሰብሰብ ነው ቁም ነገሩ። እሱ ከመፈጠሩ በፊት ሉሲ ተፈጥራለች እና። ሉሲ እንደተጀመረው ዘር የማፍለስ ሂደት ርዕሰ መዲናውና ማጣት ፈጽሞ አይገባትም።

ይህ ደግሞ ለዓለሙ መንግሥትም አቤት የሚባልበት ቁንጮ ጉዳይ ስለመሆኑም ልብ ሊባል ይገባል። ይህ መሠረታዊ ነገር በአጀንዳ በውጩ ከተነሳ የተካበው ሁሉ፤ ሁላችንም ፈቅደን ቁንጮ ያደረግነው፤ ሁላችንም በቻልነው መልክ የገነባንለት የኦዴፓ ተክለ ሰውነት ሁሉ ይናዳል። አሁን ተጋድሎው የ እርስ በ እርስ ነው ቤት ለቤት ጉልቻ እና ጉልቻ ላቅ ሲል ግን የከፋ ይሆናል።

ከባድ የነበረው ከ ኦሮሞ የወጡ ሊሂቃን ያቀነቀኑትን ኢትዮጵያዊነት በህዝብ መንፈስ ማስረጽ ነበር እንጂ መናድ፤ ማፍረስ እማ ምን ሲከብድ ነው። 6 ወር የፈጀ ህንጻ በአንድ ግሪደር እንደ ለገጣፎ ለገዳዲ የ21ኛው ምዕተ ዓመት ፋሽስታዊ ኢ - ሰብዕዊ ተግባር የዶግ አመድ ማድረግ ይቻላል። የሚያሳዝነው ግፉን አትዘገቡ፤ አትጻፉበት የእኛን ተክለ ሰውነት ስለሚያበላሽ መባሉ በራሱ ነው አስተዛዛቢው።

በሌላ በኩል አዲስ አባባ የፓን አፍሪካም መዲና ናት እንጂ የአንድ ብሄር መለያ ምልክት አይደለችም። ለአፍሪካ ህብረትም ቢሆን ይህን በይፋ ማቅረብ ይቻላል። በሌላ በኩል አገር ምድሩን የኔነው የሚለው ስግብግቡ የኦነጋውያን መንፈስ ተግ ብሎ ሊያስበው የሚገባው ሌላው ጉዳይ እሱም የሉሲ ባላባት ባለርስት መሆኑ ነው።

ለነገሩ አንድ ነፍስ ያለው ተፎካካሪ ሊሂቅ ማግኘት አይቻልም፤ አንዱ ስሜ ባሬያ ሆነብኝ እያለ መንታ መንታውን ያነባል፤ ሌላው እምታገለው ለኦሮሞ የበላይነት ነው ይላል፤ ሌላው ደግሞ ዝም ብላችሁ አዲስ አባባን የእናንተ ናት ማለት ቀላል ነው ይላል፤ ሌላው ጣሊያን ቢሆን መጥቶ ከንቲባ ይሁን ይላል፤

 ሌላው ደግሞ አገር እዬመራ የሰባታ ውሃ ለምትጠጣው ግብር ለእኔ አስገባልኝ ይላል፤ ሌላው ደግሞ ርዕሰ መዴና ላይ ሆኖ ጦርነት ያውጃለኝ አገር ለመሆን ባንኩንም ዘርፎ ጠያቂ የለውም፤ ለማ ፊቱ ኦሮሞ ይመስላል ይላል፤ ሌላው ኢሚንት ተባልኩኝ ብሎ ድንኳን ይጥላል መሪ ጠ/ሚር ለመሆን ተራራ ላይ ነፍሱን ያስዘመጠው፤ ሌላው ደግሞ የከተማ ፖለቲካ ለመለወጥ ዴሞግራፊ ወሳኝ ስለሆነ ያልፈቀዱ ወገኖችን አምጥቼ በውዣለሁኝ ብሎ ራሱ ይመሰክራል፤ ሌላው ትግራዋይ ታስፈልጉኛላችሁ ይላል፤ ሌላው ሦስት ነፍሶችን አሰልፈናል አብይወለማታከለዋዩማ አዲስ አባባን ወደ ባለቤትነት ለመሸጋጋር ተተግቶ እዬተሠራ ነው ይላል፤  መቼም እንደዚህ ዘመን የኦሮሞ ሊሂቃን ሆድ ዕቃቸውን ዝርግፍግፍ ብሎ ያዬነበት ዘመን የለም። አዲስ ራዲዮሊጂ ግዝት አድርገው ሰጡን።

ድሮ ድሮ ወልብልቢቱ ነበር አሁን ግን ከራስ ጸጉር እስከ እግር ጥፍር ለዛውም የዳግማዊ ሚኒሊክ ቤተመንግሥት በመዳፍ ላይ ተቀምጦ … እዬዬ ነው ምሾ ነው … ልጆቻችን ወንጀል ቢሰሩም አይነገርብን … ገመናችን እኛው እንዳፈን ክድን ይበልልን አይውጣብን … ይስተባበልልን እኛ የገዳ፤ የጉደፊቻ የሞጋሳ ባላባቶች ነን … 

ንጉሥ ተሁኖ የለ፤ መቻል ነው በንግሥናው ልክ ህግን ማክበርም ማስከበርም ካልተቻለ። አቅሙም ከኢትዮጵያዊነት ጋር ሊመጣጠን ሊዋዋጥም ካልተቻለ … እንሆ አንድ ዓመት ሊሞላ ምን ቀረው … ከ እንግዲህ የአብይወለማታከለወኡማ ሌጋሲ እስኪበቃው ይጠረባል

 … ኢትዮጵያዊነት ከ አብይ ሌጋሲ በላይ ሊሆን አይችልም!ኢትዮጵያዊነት ድንቅነሽነትም ነውና ለዚህ ይተጋል! በዚህ የልቅና አቅም መሆን ግድ ይላል፤ ሌት እና ቀን መግለጫ በመግለጫ ህዝብን ስጋት ላይ ከመጣል አቅምን መገንባት በኢትዮጵያዊነት በድንቅነሽ ልክ መሆን መቻል። አቅሙ፤ ክህሎቱ ካለ ... 100 ሚሊዮን ህዝብ መምራት የገብያ ውሎ ወይንም የ አዳራሽ ቻቻታ አረንሻታ አይደለም።

የአንድ ሰው ልቅና ብቻ የሁሉም ሊሆን አይችልም። ከአንድ ሰው በስተቀር ወጥቶ ሞግቶ የሚረታ የለም ራሱ በግንባሩ ውስጥ ሳይቀር። ለዚህ ነው በሁሉም ቦታ እና ሥፍራ ጠ/ሚሩ የሚገኙት። በሌላ በኩል ከኦዴፓ የካቢኔ አባላት ውጭ የሌላውም አቅም እንዲታይ አይፈቀደም። በኮሜቴ ሲገለባባጡ የሚታዩት ደግሞ ክብርት የሰላም ሚ/ሯ ናቸው። 

እርዳታ የገዴኦ ቢመለከት በ አዲሱ ፍልስፍና ህወሃት እና ኦዴፓ በጥምረት የተሰለፉበት ይመስላል፤ ሰባዕዊነቱ መልካም ቢሆንም ከመጉዳት በፊት የሚቀድመውን ማስቀደም መልካም ነው። ኦዴፓ ሰውን ማዕከል ያድርግ። ያው ንጉሥ ስለሆነ አሁን።

የገቢ ሚ/ር፤ አዲስ አባባ ከንቲባ፤ የኦዴፓ መንፈሶች ናቸው። ምን ታስቦ ይህ ቅንጅት ከህወሃት ጋር ግንባር እንደተፈጠረም በድርቡ እንመዝነዋለን … መከላከያ 7ኛ በዓሉን ሲከበር፤ የዓድዋ ባዕል በአዲስ አባባ ሲከበር፤ የአዬር መንገዱ የተርሚናል ምረቃት ማንን ለማግለል እንደሆነም ከልብ ሆነን እናስበዋለን። ሱባኤም ካሰኘው ይገባለታል ... ምን ሲቸግር ... 

ህወሃት ደጅ እዬተጠና ነው። ኦዴፓን ለመታደግ ድል ላይ ስለመሆኑ እያስተዋል ነው። የተገለለውን አንገትም መጎመዱን እያስተዋልን ነው አቤቱ ግርባው ብአዴን። በኦሮማራ ጋብቻ ኦሮሞትግራዋይ ተተክቷል። ለነገሩ እነሱ ለኦሮማራ ያልሆኑ ለማንም አይሆኑም። ምክንያቱም መሰረታዊ መነሻቸው ኦሮሞ የሚባል አገርን  በኢትዮጵያዊነት መናጆ መመስረት ነውና።  

ወደ ብአዴን ምለስት ሳደርግ ለነገሩ ትናንትም ለሄሮድስ መለስ ዜናዊ ማንፌስቶ ግርባነት ዛሬም ሥም ወራሽነቱ ጨምሮ ለኦሮማማ ግርባነት ሲሆን ዓላማ ድርጅቱ ሲመሰረትም ትናንት አልነበረውም፤ ዛሬ ደግሞ የሚሰጠውን የዶር ለማ መገርሳን ምህንድስና ስልቅጥ ማደረግ ግድ ይለዋል። 

ስለምን ቢባል? እንደ ድርጅት ብአዴን አልተመሰረተም እና ተጠሪ ነኝ በሚለው ማህበረሰብ ዓላማ ውስጥ አልነበረም። ለዚህ ነው አሁን የሌላ ሃሳብ ተጠዋሪ ሆኖ በአጃቢነት የሚገኘው … ለዚህም ነው ትግላችን ለፖለቲካ ሥልጣን አይደለም ብሎ ልቡን፤ ኩላሊቱን፤ ህሊናው አሳልፎ ፈቅዶ የሰጠው… ነገረ ሉሲም እምትታዬው ተዚህ አንጣር ነው።  

ብቻ ግን ግርድፍ መንገድ ማምሻ ነው እንጂ ማንጊያ አይሆንም ለራሱ ለገዢው  ለአጤው ለኦዴፓ። ዕውነትን በመድፈር በቃል ውስጥ መገኘት ብቻ ነው ማግስትን ማደራጀትም ማዝለቅም የሚገኘው። 

ስለዚህም በዚህ ጉዳይ ከፍ ባለ ሁኔታ ዓለም ይመክርበት፤ ይዘክርበት ዘንድ ጉዳዩን ሰፋ አድርጎ መያዝ የሚያስፈልግ ይሆናል። የሉሲ የድንቅነሽ ጉዳይ መናህሪያ ማጣት በመንፈስ ደረጃ ራሱ እንቅልፍ የሚነሳ ነውና።

ይህን የምለው ዛሬ ጭልፋ ይዘው ለሚባክኑት መንፈሶች ነው። አንድ ምሳሌ ከሰሞኑ ጠ/ሚር አብይ አንስተው ነበር። ኔውዝላንድ አንድ በመንፈስ ያበደ ሰው የሰራውን ወንጀል እና የህግ ጥሰት ከሳቸው ድርጅት አማራር እና ስፍስፍ ከሚሉላቸው ወንጀለኛ አክቲቢስቶቻቸው ሆነ የሜንጫ ማህበርተኛ ጋር ለማመሳሰል ሞክረዋል። 


Ethiopia: የጌድዮዋ እናት ጥያቄና የዶ/ አብይ አህመድ ምላሽ | Dr Abiy Ahmed | Gedeo


ምን እና ምን። ኒዎዝላንድ ላይ እኮ ብሄራዊ አገራዊ ጉዳይ የመተንፈሻ ቧንቧ እንጂ እንደ ኢትጵያ መንግሥት ማባጨያ፤ እንደ ጥንቸል ሙከራ የሚደረግበት አይደለም። ይህም ሆኖ ወንጀል የፈጸሙት በመንግሥት ሽፋን ተሰጣቸው ወይ? ወንጀል አይደለም እብድ ሰለሆነ ነው ተባላቸውን? መሰከረም የሆነው ዘግናኝ ነገር ሁሉ እንዴት ይረሳል የቡራዩ እና የ አዲስ አባባ ተከታታይ ተደራራቢ መከራ፤ በተደራጀ ሁኔታ የሆነው መከራ ሁሉ?

ለመሆኑ ኔውይዝላንድ ከህግ በላይ እንደ እናንተ አደረገው ወይ? ቀድሞ ነገር በ ኦዴፒ ዘመን ወንጀል የሠሩ ግድፈት የፈጸሙ የዞጉ አባላት ይከሰሳሉ ወይ? ይጠዬቃሉ ወይ? ለመሆኑ እነሱን መናገር ይቻላል ወይ? 

መከሰሱ ቀርቶ በከፋ ፊት ይታያሉን? በደህንነት ጠባቂ እኮ ነው የሉሲን መንፈስ በፋስ እንዲተረትሩ የሚፈቀድላቸው፤ በመገልጫ እኮ ነው ሜጫ እና ገዠራ የጸደቀላቸው። አገር እንዲመሰርቱ ጃሉ እንዲሉ የሚፈቀድላቸው እኮ በይፋ በ አደባባይ ነው፤ ሲገሉ፤ ሲዘርፉ 18 ባንክ ማን ጠያቂ አላቸውና፤ 

በዓለም ለተጎዱ ነፍሶች እርዳታ የሚከለክል ድርጅት ቢኖር አሁን በዘመነ አብይ ነው። ይህን በቡራዩ ላይ አይተናል። በለገዳዲ ለገጣፎ ለገዳዲ ላይ አይተናል? ምን ዓይነት ዕምነት እራሱ እንደሚከተሉ አይታወቅም?የገዴኦኑንም ሰምተናል። 

ይህ እንግዲህ ሚዲያ የደረሰበት ነው ያልደረሰበት ከኦሮምያ ጋር የሚዋሰኑ በዛ ውስጥ የሚኖሩ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ እዬር ብቻ ነው የሚያውቀው። ወደ እንሳሳነት የተለወጠነበት አሳፈሪ ዘመን ነው። እዳውም፤ እፍረቱም የሁሉም ነው እንደ ዜጋ። ዘር መበወዝ እኮ ዓለም አቀፍ ህግጋትን ማፋለስ ነው ... ተቻለ እኮ፤ ግን ገላማን። 

ዕውነቱን የገለጹዩት እኮ ነው በበቀል የተጨፈጨፉት አዲስ አበባ ላይ ነው። ጭካኔ የፈጸሙት ቀርቶ ጭካኔ ለተፈጸመባቸው እርዳታ ያቀረቡት እኮ ናቸው ካቴና የታዘዘላቸው … ምንም እና ምን እንደሚያገናኙት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከቶውንም አይገባኝም።

ወንጀሉን አታጋኑት ሁሉ ይላሉ እኔ በውነቱ የጤናቸው ሁሉ አልመስለኝ እስኪል ድረስ። እኔ እሳቸው ከሀምሌው ዝምታ ጀምሮ ጠፍተውበኛል ብለው ይሻለኛል። መንግሥት እኮ የወንጀለኛ የማስተባበያ ማዕከል አይደለም። አቅም አነሰኝ ሌላ ነገር ነው …

እሳቸው እኮ የኦሮሞ ማህበረሰብ መሪ ብቻ ሳይሆኑ የኢትዮጵያ መሪ ናቸው፤ ለዛውም ለመካከለኛው አፍሪካም እንደ አብነት እዬታዩ ያሉ … ታሪኩ በጭካኔ መበላሸቱን እኮ መቀበል ነው በዘመነ ጠ/ሚር አብይ አህመድ። በቃ። 

መልካም ሲደረግ የኦዴፓ የባለቅኔው ሙሴ ታሪክ እንደሆነ ሁሉ፤ ይህ በዬጊዜው የሚታዬው አረመኔነት ደግሞ የታሪኩ አካል ነው። ሰው ተገድሎ ተዘቅዝቆ የተገደለበት፤ በርሃ ለበረሃ ለተከላተም መከረኛ በአደባባይ ተረሽኖ ህግ አቤት እዬር ያለበት -ዘመን። ቀባሪ የተከለከበት … አራስ በግሪደር የታረሰበት? 

የሆነ ሆኖ ሆድ ለባሳቸው ተቆርቋሪ ሁነኛ ላጡ ለቅሶ ላይ ላሉ፤ በበዛ መከራ ውስጥ ላለፉ፤ ብትን አፈር ለተነፈጉ ተገፊዎች የጊዲኦ ምንዱባን አዛኝነት፤ ርህርህና፤ ቅርበት በውነቱ ሳሳብኝ። ይልቅ የደልደላዋ የቀዳማዊት እመቤት የወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው መመሰጥ እና እራሱ አለበባሳቸው መንፈሴን እርጋታ ሰጥቶታል።


Ethiopia: የጌድዮዋ እናት ጥያቄና የዶ/ አብይ አህመድ ምላሽ | Dr Abiy Ahmed | Gedeo


ሌላው አትወቅሱን አትንኩን የሚባለው አዲስ አበባ ርዕሰ መዲና የኦነግ ዓርማ አሸብርቆ የሚሊዬነም አዳራሽ በዛ ተውቦ የኦዴፓ ምክትል ሊቀመንበር ዶር ለማ መገርሳ ፍንድቅድቅ ብለው ተገኝተዋል? ኦነግ እኮ ዓለማው ይሕው በህግ ተፈቅዶለት እዬተዘባነነ ነው … 

በዛ በኦነግ አርማ ሠርግና መልስ የኢህአዴግ የግንባሩ ሥ/አ/ ኮሜቴ አባል ናቸው እኮ ዶር ለማ መገርሳ። ተከሰሱ> ተጠዬቁ? የጠ/ሚር አብይ የወቅቱ የሴክራትርያት ጽ/ቤት ሃላፊም ተገኝተዋል፤ እንዲያውም ተሾሙ፤ ተሸለሙ። ይህስ ምን ሊባል ይሆን? ኢህዴግ እኮ የፈረሰው ያን እለት ነው። ህወሃት ህገ መንግሥቴ  የሚለው ሰነዱ የተሰረዘው በዚህ ቀን ነበር። ኢትዮጵያም የተደፈረችው ያን ዕለት ነው።  

መንግሥት ነው ይህን የመራው። አይደለም ወይ? ግብዣ ያደረገውም መንግሥት ነው። የአሁኑ የሉሲ ጉዞ እና የኦነግ ዓርማ በሚሊዬነም፤ በአዲስ አባባ አደባባይ መታዬት መመዘን ያለበት ከዚህ አንጻር ነው። ኢትዮጵያን የሚያፈረስ ቡድን ጋር ኢትዮጵያዊነትን በዝንቅ ማስኬድ አይቻልም። የነጠራ የጠራ መንገድ ይኑር!

አትንኩኝ አንባል! እስኪበቃ ድረስ ይሞገታል የአብይ መንግሥት ሆነ ሌጋሲው። ስናወደስው፤ ስንድቀድሰው፤ ስናሸበሽበለት፤ ስንሟገትለት፤ ከረመጥ ገብተን ስንርመጠምጥለት፤ ስንመሰከርለት እዬሳቀ ፍንሽንሽ እንዳለው ሁሉ አሁን ደግሞ  በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያዊነት ላለው የገዘፈ ግድፈት እና የሸፍጥ ጉዞ ወቀሳ አይደለም ሌላም ቢቀጥል መቀበል ነው። ህዝብ እዬተበወዘ እኮ ነው ያለው። ወንጀል እኮ ነው ይሄ። 

ሌላው ሺ ሚሊዮን ጊዜ „ገዳ ገዳ“ ይባላል። ገዳን እራሱ የኢትዮጵያ ህዝብ ከተቀበለው ብቻ ነው ብሄራዊ ገዢ ማዋዋጫ ወይንም ማጣፈጫ የሚሆነው። በስተቀር ስለተመኙት የሚሆን ነገር የለም። 

ቀድሞ ነገር በገዳ ሥርዓት ላደገ አንድ ማህበረሰብ ሰው ማዕከሉ ሊሆን ይገባል እንጂ ሰውን በማሰቃዬት ሥራዬ ብሎ ለተጠመደ አይመጥንም፤ ለአብሮ አደጎቹ ለገዲኦ እናኳን አልሆነም ገዳ እንኳንስ ለሌላው …     

ቡራዩ ጭፍጫፋ አማርኛ ተናገራችሁ ነበር ጌዲኦም እንዲሁ ነው የተጠመደው፤ የ ኦሮምኛ የፌድራል ቋንቋነት ራሱ ከዚህ አንጻር በጥልቀት መታየዬት አለበት፤ ምን እንደተሰናዳለት ...ቢሆንማ ሥርጉተ እኮ ከ300 በላይ ጹሑፍ ጽፋላች ለ እሷ ክብሯ ነበር በመሰከረችው ልክ ቢሆን እኔ ለ ኦነግ መንፈስ ድል አድራጊነት አልታገልኩኝም። 

ነፍሴ ከሚጸዬፋቸው ድርጅቶች አንዱ ቢኖር ኦነግን ነው። የፖለቲካ አቅምም የለውም አጀንዳ ቢስ በሌላ ትክሻ ተንጠልጥሎ ማመስ እና ማተራመስ፤ ምን አልባት ይህ ዘመን ግብዕቱን ይፈጽመው ይሆናል አንድዬ!ለውጥ መጣ በተባለ ቁጥር እንቅፋት ... 

የሆነ ሆኖ ሉሲን ድንቅነሽን መዲና አልባ ለማድረግ ያለው ሁኔታ ኦነጋውያን ቅጥ ሊይዙ ይገባቸዋል። ልካቸውን ሊያውቁ ይገባል። በዚህ ዙሪያ ግሎባል የሆነ እንቅስቃሴም መጀመር አለበት ብዬ በጽኑ አምናለሁኝ።

የሰው መገኛ የሆነችው ኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ የሜንጫ እና የገጀራ ውል መፈጸሚያ አንኩቶ መሆን የለባትም። ትእግስቱ የቀደመ ግንዛቤ ስለነበር በዛ መንፈስ ውስጥ ሰውኛ የሆነ እንጥፍጣፊ ከአብይ ሌጋሲ አይጠፋም በሚል ብቻ ነው።
·       ራዕይ በነነ ወይንስ ተነነ?! ! ?! ?ይህ በሉሲ ውስጥ የጸደቀው መንፈስ ነው ግን የነበረ።

Ethiopia - Dr Abiy እንዴት ሰዉ 1% ልዩነት ይሰቃያል?!
Ethiopia - ….ኢትዮጵያ ትበለጽጋለች! ትለወጣለች!
እድልን በታማኝነት መጠቀም ያስፈልጋል!
Ethiopia - Dr Abiy ፈረንጆቹን አሸማቆ መለሳቸዉ!!

የሆነ ሆኖ ከሁሉ አሁን ባለው ሁኔታ „ለተባረከች አገር የተባረከ ትውልድን“ እኔን መንፈሴን የገዛው ሞቶ ስለሆነም ጭምር ነው እዮባዊነቱን የቀጠልኩበት። አሁን የሰሞኑን የጌዲኦ አናቶች „ እኛ ሰው አንደሌለን እናውቃለን፤ ፈጣሪ ግን አለን"  እንቅልፍ ይሰጣልን?

ጠ/ሚር አብይ አህመድ ጎጂዎቹ የጉርጂ ኦሮሞ አመራሮች እንደሆኑ ነው የተገለጸው፤ ጠ/ሚሩ ደግሞ ከዚህው የኦሮሞ ድርጅት የወጡ ስለሆነ ሊያፍሩ ይገባል እንጂ አትንኩኝ አያዋጣም! ቅስም ሰባሪ ድርጊት ነው። ተጎጂን መርዳት በህግ የተከለከለበት ዘመን? ይሰቀጥጣል ... በዚህ ውስጥ ኢትዮጵያዊነት ሲታሰብ ጥቁር ለብሷል።


Ethiopia: / አብይ በተገኙበት ስብሰባ በምስጢር የተቀረጸ ድምጽ

… ሰው ሆኖ በማሰብም ቢሆን ከባድ ነው። እኔ ቅዳሜ ገብያ የጎንደሩ ሲቃጠል፤ የሬቻ ጭፍጨፋ የተሰማኝን ያህል ነው የተሰማኝ፤ ዓለምን ባለመደው እርምጃ ነበር ያፋተጥኩት። ተቀባይነት ብቻ ሳይሆን ሙሉ የአቋም ለውጥ ነበር የተደረገው። 

… እንደ ድሮው ቢሆን ዛሬ አሁን ፓስታ ቤት ነበርኩኝ። በትእግስት ይህን ያህል ተሸከምነም፤  ይህም ሆኖ አትንኩኝ የሹም ዶሮ ነኝ ሊሉ አይገባም ጠ/ሚር አብይ አህመድ፤ ብዙ ታግሰናቸዋል። እሳቸው የሚመሩት ድርጅት ቀርቶ ሚዲያው እራሱ በራሳቸው ቅኝት ሥር የወደቀ ነው፤ ካቢኔው እራሱም እንዲሁ።

 አሁን ክብርት ወ/ሮ ሙፍርያት ካሜል ልብ ተገጥሟላቸዋል። "አታጋንኑት ይላሉ?የሆነ ቡድን ይላሉ" ስንት ሚሊዮን ሲፈናቀል ይሆን ሰው መስሎ የሚታዬቸው? የተፈነቃለው ብቻ አንድ አገር ይሆናል። የሰውም ግፍ አለው።

ጠ/ሚር አብይም አህመድም ቢሆኑ እንደ አገር መሪ እኛ እንዳከበርናቸው ነው ግን  መላዕክ ነኝ እና ወንጀልም ድርጅቴ የወጣሁበት ሲሳራ ዝም በሉት አይሠራም። እንኳንስ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችል ከሐምሌ 19 ቀን 2010 ጀምሮ ያላቋረጠ መከራ ቀርቶ ሰውኛ ግድፈትም ቢሆን ቦታውን እስከያዙ ድርስ ወቀሳውን፤ ጠረባውን መቻል ነው የሥነ - ጥበብ ቤተኛ እኮ ናቸው … 

"ሲሞላ ሲሞላ ጨዋታችን ሌላ፤ ሲጎድል ሲጎድል አንቄ ልገድል" እንደሚሉት ጎንደሬዎች መሆን አይኑርባቸውም እሳቸውም ሆኑ ድርጃታቸው፤ አቅም አለው መባልን በማስጠንቀቂያ ወይንም በመግለጫ ወይንም አና ብለው በያዙት በማስፈራራት እና በክስ አይደለም ለ100 ሚሊዮን ህዝብ አብልቶ፤ አስጠልሎ፤ ዋስትና ሰጥቶ ህግ አስክብሮ ነው ... ምን አጎደለን የሚባለው .. 

በሌላ በኩል ዓመቱን ሙሉ የለውጥ ጊዜም መባሉ አግባብ አይደለም። ለውጥ 3 ሚሊዬን ህዝብ ለመፈናቀል፤ ለመራብ፤ ለመጠማት፤ ለመሰደድ፤ ህክምና ለማጣት፤ በስጋት ነጋ መሼ ለመናጥ፤ በግሪደር ለመታረስ፤ በሳንጀ ለመፈተን አይደለም ... 

እንዲያውም ያልተጀመረ ነገር እኮ አለ? በውጭ ግንኙነት ረገድ ከኦዴፓ ውጪ ሁሉም ባይተዋር ነው፤ ምን እና ምን እዬሆነ እንደሆነ የሚታወቅ ጉዳይ የለም። እንዲህ መታመን በተሰፈረው ልክ ወንፊት ከሆነ እያንዳንዳንዱ እንቅስቃሴ ዜጋው ያገባዋል እና አንቴናውን ዘርግቶ መከታተል ይኖርበታል አቅም ያለው ሁሉ። ይህ ደግሞ መብት ነው።

ዜግነትን ድሮም ይሁን ዛሬ ከማንም በችሮታ የምንለምነው አይደለም ጭብጨባ እና አታሞ ለማያስፈልገን የኢጎ አርበኛ ላልሆን ፍጡራን። ወይንም በሞቀ ቁጥር ሰልፍ ለማናሳምር  የዕውነት ማህበርተኞች። ትናንት ድጋፋችን በእውነታዊ በቀደመ አብያዊ ራዕይ ነበር … ዛሬ ደግሞ ያ ራዕዬ ለአቶ ሌንጮ ለታ እና ለአቶ ዳውድ ኢብሳ ዝቅ ሲል ከፍ ሲል ደግሞ ለግራኝ መሃመድ መንፈስ ድሎት ሲባል ዝም አይባልም።

„ጨዋታን ጨዋታ ያነሳዋል“ ይላል የጎንደር ሰው … አሁን ንግግር ሆኖ ነው የቃል ኪዳን ሰነድ ፍርርሙ ዕለት? ማን ነበር የተቀጠቀጠው? የማን ቅስም እንዲሰበር? ማን ድጋፍ እንዲያጣ? ማንን በመወገን? በአንደበትም ህወሃት ይቅርታ የተጠዬቀበት ሁሉ ነበር፤ አክብሩትም አለበት። እንኳን ለዚህ አበቃችሁ¡ አቅም አንሷችሁ አቦይ ስብሃት ነጋን ተንበርክኮ ለመለመን … "የቀን ጅብ ብላችሁ ስንት ዘግናኝ ጉድ እንዳልዘረጋገፋችሁ"

እዛው እናንተ እንደፍጥርጥራችሁ „መቀሌ ኬኛ“ በሉና እንደተለመደው ይዘፈን … እኛን ተወት … ለነገሩ በንጉሥ¡ ታከለ ኡማ በአዲስ ዜማ „ታስፈልጉናለችሁ“ ተገልብጦ ቀርቧለኝ። እንደለመደባችሁ። ብልሃት የሌለው ቅላት ነው ስልቱም ምህንድስናውም የተባላ ቁብ ቁሞቀር ነው የሆነው … ወንጀለኛን የተባበረ ሁሉ ወንጀለኛ ነው ይላል ህጉ … እግዜሩን ፍሩ … መጋቢት ልደታንም እስቡ … 737 ማክስ 8 አስቡት ... 


Ethiopia: / አብይ በተገኙበት ስብሰባ በምስጢር የተቀረጸ ድምጽ

 እኔ የእናቶችን ዕንባ አዳምጬ ዝም የምል ሰው አልነበርኩኝም። ሰቅጣጭ ነው። ህዝብ በወል እንዲህ እያለቀሰ … በታሪክ እራሱ የመጀመሪያ ነው።  ሌላው ተቃርኖው ነው፤ ም/ጠ/ ሚሩ/ የሰላም ሚ/ር ተልኮ ነበር፤ እርዳታ አላተቋረጠም ይባል እና በመጋቢት 1/2011 ነው የሰማሁት፤ በማግስቱ ቡድን ተደራጀ፤ ተላከ፤ ዛሬ እኔ መጣሁ ደግሞ ይመጣል … ኧረ በህግ! ምን አዚም እንደሆን አላውቅም? የአብይ መንፈስ እንዲህ እኔ የማላውቀው የሆነ፤ ከቶም አላውቅም? ፈጽሞ … እንደ ሌሰን ነበር ያጠናሁት።

Ethiopia: የጌድዮዋ እናት ጥያቄና የዶ/ አብይ አህመድ ምላሽ | Dr Abiy Ahmed | Gedeo

 ወደ ቀደመው ምልስት ስናደርግ በጥልቅት ብናዬው አዲስ አበባ የማይመለከተው አንድም የዓለም ዜጋ የለም እንኳንስ ኢትዮጵያዊው፤ ስለምን? ሉሲ ድንቅነሽ መዲናዋ አዲስ አባባ ነው እና። ይህን ርዕሰ ጉዳይ በብልህነት እና በማስተዋል አይቶ ዳር ለማድረስ ከእያንዳንዱ በግል ከሁሉም በጋራ የወል ተግባር መፈጸም ግድ ይላል። ወደ ልቦናችን እንመለስ። ኢትዮጵያ ከሃሳብ በላይ ናትና። 

ውዶቼ ... ቅኖቹ 

ስለ ልዕልት ድንቅነሽ ሉሲ፤ ወይንም ስለ ንግስት ሉሲ ድንቅነሽ በዬአገሩ ወደ የሚገኙት ከወደ ቤተ መጻህፍት ጎራ ቢባል ብዙ ዝክረ ትውፊት ይገኛል። ክብሯ፤ ልቅናዋ፤ ልዕልናዋ እንዲህ እንዳይመስላችሁ። በሁሉም መምሪያ ነገረ ሉሲ አለች።

አቶ አንድርያስ ጋሰር አለቃዬ የቤተ መጻህፍት ማናጀር ነበር። ቤተ መጻህፍቱ የዛሬ 15 ዓመት በቀን ወደ ሁለት ሺህ ሰው በቀን ያስተናግድ ነበር። ዛሬ ከዚህ እንደሚልቅ እገምታለሁኝ።

እኔ ከዛ ለልምምድ ስቀጠር የመጀመሪያ የጋበዘኝ ነገር የሉሲን ድርሳን የያዙ መዘክሮችን ነበር። እሱ ነበር እራሱ ተቀብሎ ቤተ መጻህፍቱን መጀመሪያ ያስጎበኜኝ። አጠቃላይ ገለጻም ያደረገለኝ። ይህ ያልተለመደ ጉዳይ ነበር።

ስለምን እንደሆን እኔ ሳስበው የልዕልት ሉሲ ክብር እና ልዕልና ነው ብዬ አምናለሁኝ። እጅግ በልዕልት ሉሲ ጉዳይ የተመሰጠ ነበር አለቃዬ … ቦታውን ሄዶ የማዬትም የመሄድም ዕቅድ እንደነበረው አውቃለሁኝ …

እንግዲህ ሲዊዞች እጅግ ቁጥቦች ከመሆናቸው በላይ ፍላጎታቸውን እና እምነታቸውን ለመግለጽም እንዲሁ የሚቸገሩ ናቸው፤ አብዝተው አደብ የገዙ አቅል ያላቸው ናቸው።
ሜንታሊታቸው ለነገሮች ድንቀትም ኩሰትም ብዙም የማይክለፈለፍ የረጋ መንፈስ ነው ያለው። ይህም ሆኖ በልዕልት ድንቅነሽ ግን አቶ አንድርያስ ግልጽ የሆነ አቋም ነበረው። እኔም ከኢትዮጵያ እወለዳለሁኝ፤ ዘር አለኝ ይለኝ ነበር በድፍረት እና በኩራት፤

… እሱ አለቃ በነበረበት ዘመን በቤተመጻህፍቱ ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምስራቅ ጋር ተዳብላ ነው የነበረችው፤ ከዛ ኢትዮጵያ ራሷን ያቻለ ክፍል እንዲኖራት ተደርጓለኝ። ኢትዮጵያን በሚመለከት በፍጹም ሁኔታ የባለቤትነት ስሜት ነበረው አቶ አንድርያስ ጋሰር።

የእኛዎች ዘመነኛ ባለ ሜንጫዎች ደግሞ „ኢትዮጵያ ካልፈረሰች ኦሮምያ ሰላም አታገኝም“ ባዮች ናቸው። እራሳቸውን የገፉ፤ ራሳቸውን የተጸዬፉ እና እራሳቸውን የሚቀናቀኑ አሳዛኞች …

የሆነ ሆኖ ሉላዊ የሆነ የህልውና ተጋድሎ ያስፈልጋል አሁን ባለው ሁኔታ። ዘመቻ ስለ ሉሲ ህልዋናም። ምክንያቱም እዬፈረስን ስለሆነ … ለዚህም ይመስላል ትንቢተኛው ኢትዮጵያ ከሚፈርሱ አገሮች ተርታ ያሰለፏት …

ድንቅዬ እመቤት
የሁለመና ቁርባን - የአብነት መሠረት
የጸሐይ ምህዋር  - የሰው ልጅ ግማዳት።

የቀለም ህብርነት የዕውነት አውራት
የእኛነት ልዕልና የግሎባል እናት!
የሁሉም አናትነሽ የፍቅር ጥቁራት።

የትርፉት መቅረ የትውፊትም ብሥራት
የአዲስዬ አወታር የሳይንሱም አንብርት
የገናና ታሪክ የዝልት መስታውት።

እባክሽ? እባክሽ? እምዬ የታሪክ ቅኝት
የመደድ ማህለቅ የጥልቅ ሚስጢር ንባብ
ስለ ሰለአንቺ መስክሪ …
እውነትን ንገሪ
ግርዶሹን ተጋፍጠሽ
ሃቅን እስመርኩዢ።

የትጋት ሰናይት የመሆን ትንግርቱ
ባለማረግ መሆን የትናንት ህብስቱ።

የጥልቅት መለኪያ የዘመን ፊዳላት
የሁሉዬ እናት …
የቅምረተ ቀናነት -  የእትብት ቀለበት።

የፍልስፍና አንባ የልቅና ቀለም
ምስክር ጠየሐይ ነሽ የሆንሽለት ለላለም!

የአብሮነቷ ማማ
ድንቅነሽ እማ!

በሚሰጥራት ዝማም የምዕት አበ
ህመምን ፈውሽ ልክም እንደጣዝማ፤
ሰላምን አውርጂ እርግብ በዘንባባ…።

በርሰ መዲናሽ ኑሪ ለዘላለም!
የዓለሙ ደማም!

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።

የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።