ልጥፎች

ከኦገስት 26, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ዛሬ አብያዊ መንፈስ ከሱባኤ ማግስት በመነኩሲት ባዕት!

ምስል
ትርጉም ገብ ማዕልት። „እግዚአብሄርን መፍራት ውደ ህይወት ይመራል፤ የሚፈራውም ጠግቦ ይኖራል፤ ክፉ ነገርም አያገኘውም።“ ምሳሌ ምዕራፍ ፲፱ ቁጥር ፳፫    ከሥርጉተ ©ሥላሴ 26.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ይህ የዶር አብይ አህመድ ፍላጎት የዛሬ አይደለም የቀደመ ነው።  እንዴት ናችሁ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ። ትናንትና ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በርከት ላሉ አገር ውስጥ ለሚገኙ ጋዜጠኞች የመጀመሪያውን የጋዜጠኞች እና የጠ/ሚሩን የመጠይቅ እና የመልስ ሂደት ሁላችንም ተከታትለናል።  በጤናቸው ዙሪያ ለተነሳው ጥያቄ ምንም አልደረሰብኝም፤ ታምሜም አላውቅም ሲሉ ቅልብጭ ያለ መልስ ሰጥተዋል።  ያም ቢሆን እንደ እኔ መሰል የቀደመውን አብይ ፍለጋ ለነበርን ሰዎች ብዙም አጥጋቢ አልነበረም።  ይህ ሲባል ደህንነታቸውን መስማት አያስደስትም ማለት ግን አይደለም። የአብይ መንፈስን ባወቅነው ልክ አለመግኘታችን ነበር ጭንቀታችን። በሌላ በኩል ተራ ወሬ ብቻ ተደርጎ መወሰዱም ብዙም ያልተመቸኝ ነበር። ሰዉ ልዩ ፍቅር፤ ልዩ አክብሮት፤ ልዩ ተስፋ ስላለው ነው ጭንቁ መጠበቡ የነበረው። ዕንባ አልቃሽ በገንዘብ የተገዛበትም ታሪክ እኮ እናውቃለን። ከሚዲያ መጥፋት ብቻ ሳይሆን የሚዲያዎች ሂደት እና አቀራረባቸው፤ ምስል ቀረጻው እና ሁኔታው በፍጹም ወደ ውስጥ ሊገባ የሚቸል አልነበረም። ዛሬ ሳይሆን ቀደም ባለው ጊዜም ጭምር በጥልቀት ጉዳያችን ብለን አብያዊ መንፈስን ለምንከታተለው ሰዎች ወሬው ከመወራቱ ቀድሞም ያሉትን ክንዋኔዎች በባለቤትን ስንከታተል መቆዬታችን ለኢትዮጵያ ተስፋ ካለን ቀናዕይነት ነበር።  ልብ አምላክ ዳዊት „የቤትህ ቅናት በላኝ“ እንዳለው ማለት ነው። በዚህ ዘርፍ የጠላት እና የወረኞች ወይንም በጎ የማያስ